*************************
የጥመት ተጣሪዎች ባጢላቸውን "የሀቅ" ቅብ ለመቀባት፣ የሃቅ ተጣሪዎችን ባጢል ላይ ያሉ ለማስመሰል ከሚጠቀሙባቸው ማምታቻዎች ውስጥ
"አኽላቅ፣ አኽላቅ፣ አኽላቅ" እያሉ ይጮሀሉ።
ነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ከነብይነት በፊትም ይሁን ከነብይነት በኀላ የመልካም ስነምግባር ባለቤት፣ ታማኝ ከመሆን አልተወገዱም።
የመካ ሙሽሪኮች ነብዩ ሙሐመድን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ከነብይነታቸው በፊት "ታማኙ ሙሐመድ" እያሉ ነበር የሚጠሯቸው።
ታማኝነታቸው ሳይቀየር ያውም መልክተኝነታቸውን የፍጡራን ሁሉ ፈጣሪ አላህ "ሙሐመድ የአላህ መልክተኛ ነው" ብሎ መስክሮ ሲያበቃ፣
እሳቸው የመካ አጋርያንን ታማኝ መካሪ ስለሆኑ
"ህዝቦቼ ሆይ! ላኢላሃ ኢለላህ (ከአላህ በስተቀር በሀቅ የሚመለክ የለም) በሉ ትድናላችሁ።" ስላሉ ብቻ የሚከተለው የስድብ፣ የአካል ጉዳት በሳቸውም በተከታዮቻቸው ላይ ደረሰ
1) "እብድ፣ ገጣሚ፣ ደጋሚ፣ በታታኝ––––"
2) ጥርሳቸው ተሰበረ፣ ተደበደቡ፣ ማእቀብ ተደረገባቸው፣
3) ምግባቸው ላይ መርዝ ተጨመረ፣
4) ሴት ልጆቻቸው ተፈቱ (ትዳራቸው ተበተነ)፣
5) ሰሀባዎቻቸው መካ ላይ ተገደሉባቸው የአማር ረድየላሁ አንሁ ቤተሰቦችን ይመስል፣
6) ሰሀባዎች መቀመጫ አጥተው ውዷን ከተማ መካን ትተው ተሰደዱ
አረ ስንትና ስንት ደርሶባቸዋል።
አኢሻ ረድየላሁ አንሀ ስለ ረሱል አኽላቅ ስትጠየቅ፣ "አኽላቃቸው ቁርአን ነበር" ብላለች።
ማለትም
1) ቁርአን የወደደውን ይወዳሉ፣
2) ቁርአን ያወገዘውን ያወግዛሉ፣
3) ቁርአን ቅድሚያ የሰጠውን ይሰጣሉ፣
4) ቁርአን የጠላውን ይጠላሉ፣
5) ቁርአን ትኩረት የሰጠውን ይሰጣሉ
------------
ታድያ ለምን ይሆን መንገድ የሳቱ ሰዎች ሽርክና ቢድአ ሲወገዙ "አኽላቅ" ብለው የሚጮሁት?
እውነት ከሽርክና ቢድአው በላይ ተውሂድ ተጣሪዎች ላይ የስነምግባር ጉድለት ታይቶ ነውን?
በፍፁም
የተውሂድ ተጣሪዎች ታማኞች ስለሆኑ፣ አታላዮች ስላልሆኑ፣ የነብያትን ፈለግ ተከትለው ተውሂድን ያስተምራሉ፣ ከምንም በፊት ከሽርክና ቢድአ ያስጠነቅቃሉ በዚህም ላይ ይዘወትራሉ የወደደ ቢወድ የከፋው ቢከፋው።
ነብያትን ያስቀደሙትን አርስት ሳያስቀድም አያፍርም የነብያትን ፈለግ የሚከተሉትን "አኽላቅ" እያለ ሰዎችን ከነሱ ያስጠነቅቃል።
ኡማው ከእንዲህ አይነቱ ሰዎች ነው ሊጠነቀቅ የሚገባው።
አላህ የነብያትን መንገድ ከሚከተሉት ያድርገን።