Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

አርካኑል ኢስላም(የኢስላም ማእዘናት) ሺዓዎች ዘንድ!


አርካኑል ኢስላም(የኢስላም ማእዘናት) ሺዓዎች ዘንድ!
ለአላህ ከዚያም ለታሪክ (http://bit.ly/29Ymu33)
አንብበው ሲጨርሱ SHARE ማድረግ አይርሱ!
ሺዓዎች በአይሁዳዊው መስራቻቸው (https://goo.gl/nJstr3 ) እምነታቸው ከተፈለሰፈ በኋላ ብዙ ነገሮችን እየጨመሩ እና እየቀነሱ እራሳቸውን በኢስላም ጥላ ስር ለማቆየት ቢታትሩም እምነቶቻቸው ግን በተቃራኒ ኢስላምን ከመሰረቱ የሚፃረሩ እና የሚንዱ ሁነው ይታያሉ። ቀደም ብለን እንደገለፅነው (https://goo.gl/PnBPv5 ) ሺዓዎች በሀሰት ላይ በተመረኮዙ ዘገባዎቻቸው ትክክለኛው ኢስላም ካስቀመጠው ውጪ መሰረታዊ እና ቅርንጫፋዊ ጉዳዮችን እንዳሻቸው ቀያይረው አስቀምጠዋል። ሺዓዎች ብዙ ነገሮችን የቀጠፉ መሆናቸውን ወደፊት የምናይ ቢሆንም ዛሬ ግን ሁሉም ሙስሊም ሙስሊምነቱ በሚረጋገጥባቸው የኢስላም እና የኢማን ማእዘናት ላይ ያላቸውን ተቃርኖ እናያለን።
ሺዓዎች ዘንድ ታማኝ በሚባለው የኩለይኒ አል-ካፊ መፅሀፍ ከአቢ-ጀዕፈር ተወራ ብሎ የሚከተለውን አስፍሯል ...
"እስልምና በአምስት ነገሮች ላይ ተገንብቷል፦ ሶላት፣ ዘካ፣ ፆም፣ ሐጅ እና ዊላያ ናቸው" ኡሱል አል-ካፊ 2/15
እንደሚመለከቱት ነቢያችን(ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ያስተማሩን ከኢስላም መሰረቶች ቀንደኛውና ዋናው ላኢላሀኢለላህ እና በመልእክተኛው ማመን ሺዓዎች አንድ አይገኝም። ይልቁኑ በርሱ ምትክ በልብወለድ ያስቀመጡት 'ዊላያ' ዋና ማእዘን ሆኖ ተቀምጧል። በሌላ የቅጥፈት ዘገባቸው ላይ እንዲህ ይላል ...
"እስልምና በአምስት ነገሮች ላይ ተገንብቷል፦ በሶላት፣ በዘካ፣ በፆም፣ በሐጅ እና በዊላያ" ከነዚህ በላጩ የትኛው ነው ተብሎ ሲጠየቅም "ዊላያ በላጭ ነው" ሲል ይመልሳል። ቀጠል አድርጎም አንድ ሰው ለሊቱን በሶላት ቢቆም፣ አመት ሙሉ ቢፆም፣ ያለውን ገንዘብ ሁሉ ምፅዋት ቢሰጥ፣ ሁሉንም አመት ሐጅ ቢያደርግበት 'ዊላያን' ካላወቀ ስራው ሁሉ ብኩን እንደሆነ እና ከአላህም ምንዳ እንደማያገኝ ሰውየውም አማኝ እንዳልሆነ ይጠቅሳል። አል-ካፊ 2/16
እንግዲህ ሸሀደተይንን አስወግደው በቦታው ያስቀመጡት እንርሱ ድንበር እያለፉ ለሚመፃደቁበት የአህለልበይት(የነቢዩ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ቤተሰቦች) ውዴታ ወይም በእነርሱ አጠራር 'ዊላያ' ነው። ይህ ነው እንግዲህ እነርሱ ዘንድ ሙስሊም ወይም ካፊር የመሆኛው ማእዘን ይህ ነው እንግዲህ በአላህ እና በነቢያችን(ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) በማመን ምትክ የተቀመጠው ማእዘን።
አጠር አድርገን ስናስቀምጠው ሺዓዎች ዘንድ የኢስላም ማእዘናት ብለው ያስቀመጡት ...
1. ዊላያ
2. ሶላት
3. ፃም
4. ዘካ እና
5. ሐጅ ናቸው።
ሌሎች ሺዓዎች ደግሞ የኢስላም ማእዘናት ማለት ...
1. ተውሂድ(በእነርሱ ትርጓሜ)
2. አድል(ፍትሀዊነት)
3. ኑቡዋ (በነብይ ማመን)
4. ኢማማ (የነቢይ ተተኪ በሚሉት ማመን)
5. ሚዓድ (በሚገልፁት የቂያም ቀን ማመን)
ናቸው በማለት ይጠቅሳሉ። ሌሎችም ሺዓዎች የኢስላም ማእዘናት ናቸው እያሉ የሚቀጡፉትን ለመጥቀስ ቢቻልም ፅሁፉ እንዳይረዝም ሲባል በዚሁ አሳጥረነዋል።
በሰሂህ ሙስሊም እንደተዘገበው በጂብሪል ሐዲስ እና በሌሎችም ትክክለኛ ዘገባዎች ነቢያችን (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ያስተማሩን የኢስላም ማእዘናት ግን ...
1. ከአላህ ሌላ በእውነት የሚገዙት አምላክ እንደሌለ እና ነቢያችን(ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) የአላህ መልእክተኛ መሆናቸውን ማመን
2. ሶላት በአግባቡ መስገድ
3. ዘካን ማውጣት
4. አቅሙ ለሚችል ሰው ሐጅ ማድረግ እና
5. የረመዳን ወርን መፆም ናቸው።
አላህ በትክክለኛው ኢስላም ላይ ያፅናን!