Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ሰልፍ እና አመጽ ሰይጣናዊ ቢድዐዎች ናቸው!! አሽሸይኹል ዐላማህ ዘይድ ቢን ሃዲ አልመድኸሊይ (ረሒመሁላህ)

«ሰልፍ እና አመጽ ሰይጣናዊ ቢድዐዎች ናቸው!!»
አሽሸይኹል ዐላማህ ዘይድ ቢን ሃዲ አልመድኸሊይ (ረሒመሁላህ) ፦
« ሰልፍና አመጽ በዲን ላይ አዲስ የመጡ ፈጠራዎች ናቸው። በዲን ላይ አዲስ የመጣ ፈጠራ ሁሉ ደግሞ ቢድዐህ ነው። ሁሉም ቢድዐህ ደግሞ ጥመት ነው። ሁሉም ጥመት ደግሞ የእሳት ነው። የአላህ ዲን ምሉእ እና ጭማሪ የማያስፈልገው ነው። ቁርኣን እና ሱንናህ ነው። ከቁርኣን እና ከሱንናህ ውስጥ ደግሞ የሆኑ ሰዎች ተሰብስበው ተቃውሞ ሰልፍ እንዲያካሂዱ የሚፈቅድ በመረጃ መልኩ አንድንም አናውቅም። የሰዎችን ሰላም የሚነሳ፤ ጊዜን የሚገድል፤ የሚብሰው ደግሞ ሶላት የሚተውበት፤ ግድያ የሚከሰትበት ነው።
አንድ ነጠላ ሙስሊም በዚህ ተቃውሞ ሰልፍ ላይ ቢሞት ሰልፉን የጠራው ግለሰብም ይሁን ቡድን ወይንም ተሳታፊ ወንጀሉን ይሸከማል!!
ሶሒሕ በሆነው ሐዲሥ እንደተነገረው.. «የአንድ ሙስሊም ነፍስ ያለአግባብ ከሚጠፋ ዱኒያ ሙሉዋን ብትወገድ አላህ ዘንድ ተመራጭ ነው።»
እነዚህ ተቃውሞ ሰልፎች በእኩይ ነፍሳትና በስሜት የሚመራ ብሎም በሸይጣን የሚታገዝ ቢድዐህ እንጂ ሌላ አይደሉም። እነዚህ ጠላቶች ደግሞ ዲን እና ዱኒያ ካልጠፉ በቀር በትብብር በአንድነት አይመጡም። ልክ ተቃውም ሰልፍ እና አመጽ ላይ እንደምናየው። »

[الأفنان وتوحيد ابن خزيمة وحديث عن المظاهرات]