ጠያቂው እንዲህ ሲል ይጠይቃል ...
«በዛሬው እለት ቱርኪያ ውስጥ ኤርዶጛን ላይ በተፈጸመው መፈንቅለ መንግስት የሙስሊም አቋም ምንድን ነው? »
ሸይኽ ሙሐመድ አልዐንጀሪ (ሐፊዘሁላህ) ፡
« ኤርዶጛን አላህ ይጠብቀውና ሙስሊም መሪ ነው። በወንጀል ሲቀር ለርሱ መስማትና መታዘዝ የሚገባው ነው። እርሱ የቱርክ መሪ ነው። ይህን ከዚህም ቀደም በርካታ ጊዜያት በብዙ ቦታዎች ላይ ሙሃደራዎቻችን ላይ የምንናገረውና በካሴቶቻችን ቅጂም ላይ የሚገኝ ነው።
መፈንቅለ መንግስት "ኹሩጅ" (በኢስላም የተወገዘው በሙስሊም መሪ ላይ አምጾ መውጣት) ነው። ይህ በኸዋሪጆች በ"ማስተካከል" ስም የሚፈጸም ተግባር ነው።
ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ኸዋሪጆችን በገለጹበት ንግግር
«ከእሳት ውሾች» ብለዋቸዋል። (የሚገባቸውን) ሐቃቸውን ደግሞ ሲናገሩ «የዐድ ሕዝቦችን ግድያ ግደሏቸው። ሙታኖቻቸውም ከሰማይ በታች እጅግ የከፉ ናቸው።» ብለዋል።
ኹሩጅ ብዙ አይነት ነው ...
ከነርሱም ውስጥ የጦር ኹሩጅ አለ፤ ከነርሱም ውስጥ መንግስቱን በአደባባይ መቃወም፤ ሰላማዊ ሰልፍ፤ ተሰብስቦ የመቀመጥ ፣ መሪን በመተቸት (በማሕበራዊ ድረ ገጾችም ይሁን በጋዜጣ) ገጾች ላይ መጻፍም፤ እርሱን፣ መንግስቱን፣ ተወካዮቹን፥ ሚኒስቴሮቹን በመተቸት ህዝብን ለአመጽ ማነሳሳትም ይህ ሁሉ የኸዋሪጅ መንገድ ነው አላህ ይጠብቀንና። ይህ በ"ማስተካከል" ስም ይህን (የኸዋሪጆች) መንገድ መፈጸም የሚሻ ከምእራባውያን መድረሳ የመጣ አካሄድ ነው።
ይህ ደግሞ የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እና ባልደረቦቻቸው ከነበሩበት (ቀጥተኛው) መንገድ የሚጻረር አካሄድ ነው።
የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሙስሊም መሪዎችን ወይንም የስልጣን ባለቤቶችን እና በማስተካከልና በመምከር ዙሪያ ሲናገሩ እንዲህ ብለዋል...
«ማንም ሰው ሙስሊም መሪውን መምከር ሲፈልግ በግልጽ (በአደባባይ) አያድርገው። በድብቅ (በሚስጥር) ይንገረው። ከተቀበለውም [መልካም] ካልተቀበለውም በርሱ ላይ ያለበትን ሃላፊነት ተወጥቷል።»
እንደዚህ ነው የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሙስሊሞ ሙስሊም መሪዎቻቸውን ማስተካከልና መምከር እንዳለባቸው የመሩት። ነገር ግን በልቡ ላይ በሽታ ያለበት ወይንም በምእራባውያን መድረሳ ተጽዕኖ ያደረበት ይህንን (ነቢያዊ መመሪያ) ጉዳይ አይቀበልም።
የአምልኮን (ጥፍጥና) የተጎነጨና ለላቀውና ከፍ ላለው አላህ ትእዛዝ ያደረ ሙስሊም ግን ይታዘዛል።
ፍርድ ሁሉ ከፍ ላለው አላህ ብቻ ነው።
فَلاَ وَرَبِّكَ لاَ يُؤْمِنُونَ حَتَّىَ يُحَكِّمُوكَ فِيمَا شَجَرَ بَيْنَهُمْ ثُمَّ لاَ يَجِدُواْ فِي أَنفُسِهِمْ حَرَجًا مِّمَّا قَضَيْتَ وَيُسَلِّمُواْ تَسْلِيمًا
በጭራሽ! በጌታህ እምላለሁ! በመካከላቸው በተነታረኩበት ነገር ፍርድ እስከሚያስፈርዱህ ከዚያም በፈረድከው ነገር በነፍሶቻቸው ውስጥ ቅሬታን እስከማያገኙ እና ፍጹም መታዘዝንም እስከሚታዘዙ ድረስ አያምኑም። [ቁርኣን ሱረቱል ኒሳእ 65]
እንደዚህ ነው ሙስሊም። እንደዚህ ነው በዚህች ሕይወት ላይ ሐቅን የሚፈልግ ሰው ።
ሙስሊም መሪው ላይ ግን በግልጽ በመምከርም ሆነ ሰዎችን በመሪያቸው ላይ በማሳመጽ አሊያም ጣልቃ በመግባት አመጽ ማካሄድ ሙሐመድ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እና ባልደረቦቻቸው ከነበሩበት መንገድ የወጣ (አካሄድ) ነው። ይህ ከቁርኣንና ከሱና የተጻረረ ነው።
"ሓኪም" (መሪ ማለት) ሙስሊም የሆነ የስልጣን፣ የኃይል፣ የጉልበት ባለቤት የሆነው ነው። ይህ ነው ለእርሱ መስማትና መታዘዝ ያለው። ልክ እንደ ኤርዶጛን።
ማንም በአፈንጋጭ ኸዋሪጆች መልኩ "ማስተካከልን" የሚሻ የሙስሊሙን ኡማ ሰልፍ ለመቁረጥና ደም ለማፋሰስ የሚፈልግ ነው።
ቱርኪያን ከኸዋሪጅና ከተክፊር አስተሳሰብ እንዲጠብቃት አላህን እንለምነዋለን።
መሪዋን እና ህዝቦቿን ለሙስሊሙና ለኢስላም የሚበጅን ነገር እንዲተገብሩ የላቀው አላህ ተውፊቁን እንዲሰጣቸው እንለምነዋለን።
ወአኺሩ ዳዕዋና አኒል ሐምዱ ሊላህ ረቢል ዐለሚን ...»
[ሸዋል11 / 1437 ዓመተ ሂጅሪ]