ጀምዒይ ወይስ ጀህሚይ?
የፊቅህ ጠበብቶች (الوسائل لها حكم المقاصد) በሚል መርህ ይስማማሉ። ለአንድ ነገር መዳረሻ (ወሳኢል) የሆኑ ነገሮች “የሚያደርሱበትን ግብ” ሁክም ወይም ብይን ይይዛሉ ማለት ነው። እነዚህ መዳረሻዎች ሀላል ወደሆነ ነገር ካደረሱ ሀላል፤ ሀራም ወደሆነ ነገር ካደረሱ ደግሞ ሀራም ይሆናሉ።
በቢድን ከመሳሊህ ሙርሰላህ ወይም ካልተገደቡ መዳረሻዎች መለየት ያቃታቸው አህባሾች፤ ለመውሊድ እና መሰል
ቢድዓዎች እንደመረጃ የቁርአንን በአንድ ጥራዝ መሰብሰብ፣ ቁርአን ላይ አናባቢ ምልክቶች መቀመጥ እና መሰል
ነገሮችን ያቀርባሉ። እነዚህ ነገሮች ለመልካም ነገር መዳረሻ እንጂ ኢባዳ ተፈልጎባቸውና ግብ ተደርገው የተፈፀሙ
አይደሉም። በዚህ መልኩ በመውሊድ ሰሞን ለተነሱ ውዥንብሮች የሁለቱን ልዩነት በማሳየት ግልፅ ምላሽ ሰጥተን
አልፈናል። ትክክለኛ ግንዛቤንም የሚያስጨብጡ መሰረታዊ መርሆዎችን ቃኝተናል።
ይሁንና ብዙዉን ጊዜ የሀቅ ጎዳና ሁለት ጠርዞች አሉት፤ ከላይ እንዳየነው አህባሾች በቢድዓና በ አልመሳሊህ አልሙርሰላህ መካከል ያለውን ልዩነት ባለመገንዘባቸው ቢድዓ ይፈቀዳል የሚል የጥፋት መደምደሚያ ላይ ደርሰዋል።
በተቃራኒው ሌሎች ደግሞ መዳረሻዎችን ከቢድዓ ባለመለየታቸው ቢድዓ ሁሉ ክልክል ነውና መዳረሻዎችም ክልክል ናቸው ብለዋል። እነዚህ ወገኖችም በተመሳሳይ በሽታ ተለክፈው በውጤቱ ሌላኛውን ጠርዝ ረገጡና መዳረሻ የሆኑ ነገሮችን እንደ ቢድዓ ቆጠሩ። ሰዎችንም አለአግባብ የቢድአ አራማጆች ብለው ፈረጁ!!
ከአመታት በፊት ከዚህ መሰል የተምታታ ግንዛቤ በመነሳት ፊትና ያቀጣጠሉ አንዳንድ ወጣቶች ብዙ በዳእዋና ማህበራዊ አገልግሎት ጉልህ ሚና የሚጫወቱ ሰዎችን ጊዜና ጉልበት ያባከኑበት አጋጣሚ ነበር።
የሱናን ሰውና የቢድዓን ሰው የሚለዩበት ታላቅ አጀንዳ በማድረግ ካቀረቧቸው መዳረሻዎች መካከል፤ ለልማታዊ ተልእኮ አለያም ለዳእዋ አላማ ማህበራትን ማቋቋም ይገኝበታል። አንዳንድ ወንድሞች ከህጋዊ አካሄድ አንፃር አስፈላጊ ሆኖ በተገኘ ጊዜ አንዳንድ ማህበራትን በማቋቋም እንቅስቃሴ አድርገዋል። ነገር ግን ይህንን መዳረሻ ተግባር ቢድዓ ነው በማለት የሱና ወንድሞቻቸውን ኢላማ አድርገዋል። ጀምኢዮች በማለትም ጥንታዊ ፊርቃ አስመስለው በማቅረብ የዋሆችን ሸንግለዋል።
አዎን! እነዚህ ሰዎች ዘንድ ይህ "ጀምኢይ" የሚለው መጤ ስያሜ ከመደጋገሙ የተነሳ አንዳንዶች ዘንድ "ጀህሚይ" ከሚለው የጃህም ኢብኑ ሰፍዋን ተከታይነት ጋር ተምታቶ ሲራገብ ተስተውሏል። ይህም መጤ አካሄድ ብዙ የፊትናና የልዩነት በሮችን ከፍቷል፤ ብዙ ጥፋትም አስከትሏል።
አላማዮ ስለነዚህ ሰዎች ማንነትና ግድፈቶች ዝርዝር ትንታኔ መስጠት ስላልሆነ፤ ከታች ያስቀመጥኩትን የሙሀደራ ሊንክ በመከተል ዝርዝር ምላሽ ያዳምጡ ዘንድ እየጋበዝኩ ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ አላህ ይማራቸውና ቢድዓ ያልሆነን አመለካከት ወይም አቋም የወዳጅና የጠላት መለያ አድርጎ ማቅረብ በራሱ የቢድዓና የስሜት ተከታዮች አካሄድ መሆኑን ያስረዱበትን ንግግር አስተላልፌ ሀሳቤን እቋጫለው።
ታላቁ አሊም ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ እንዲህ ብለዋል፤
«وليس لأحد أن ينصب للأمة.... كلاماً يوالي عليه ويعادي غير كلام الله ورسوله وما اجتمعت عليه الأمة، بل هذا من فعل أهل البدع الذين ينصبون لهم شخصاً أو كلاماً يفرقون به بين الأمة، يوالون به على ذلك الكلام أو تلك النسبة ويعادون»
«ማንም ቢሆን፤ ከአላህና ከመልእክተኛው ንግግር እንዲሁም ከሙስሊሞች ስምምነት (ኢጅማዕ) ዉጪ አንድን ንግግር (አቋም) የመውደድና የመጥላት መሰረት በማድረግ ኡማው ላይ መጫን አይችልም። እንደውም ይህ የቢድዓ ሰዎች ተግባር ነው። እነርሱ አንድን ሰው ወይም አንድን አቋም እንደ መሰረት በመቁጠር ኡማውን ይከፋፍላሉ። ይህንን አቋም ወይም መጠሪያ የወላእና በራእ መሰረት ያደርጉታል!»
መጅሙዕ አልፈታዋ 20/164
Abujunaid march 2015
በተጨማሪ ተከታዩን የሸይኽ ኢልያስ ማባራሪያ ያድምጡ
"ጀምዒያ (ማህበር) ማቋቋም በሸሪዓ እይታ"
https://www.youtube.com/watch…