Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ረመዳንና የስድስቱ የሸዋል ቀናት ምንዳ

ረመዳንና የስድስቱ የሸዋል ቀናት ምንዳ
ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ይላሉ፡-
"مَنْ صَامَ رَمَضَانَ ثُمَّ أَتْبَعَهُ سِتًّا مِنْ شَوَّالٍ كَانَ كَصِيَامِ الدَّهْرِ"
“ረመዳንን ፆሞ ከሸዋል ስድስት ቀን ያስከተለ ልክ አመት እንደፆመ ነው፡፡” [ሙስሊም፡ 1160]
30 የረመዳን ቀናት + 6 የሸዋል ቀናት = 36 ቀናት
36 x 10 = 360
አላህ በቁርኣን እንዲህ ይላል፡-
﴿من جاء بالحسنة فله عشر أمثالها﴾ الأنعام : 160
“በመልካም ስራ የመጣ ሰው ለእርሱ አስር ብጤዎቿ አሉት፡፡” [አልአንዓም፡ 160]
አላህ ለሻለት ሰው የመልካም ስራ ሽልማት ከዚህም በላይ እስከ
- 700 እጥፍ ወይም
- ከዚያም በላይ
ሊሆን ይችላል፡፡ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ይላሉ፡-
)كُلُّ عَمَلِ ابْنِ آدَمَ يُضَاعَفُ ، الْحَسَنَةُ عَشْرُ أَمْثَالِهَا إِلَى سَبْعمِائَة ضِعْفٍ ، قَالَ اللهُ عَزَّ وَجَلَّ : إِلَّا الصَّوْمَ ، فَإِنَّهُ لِي ، وَأَنَا أَجْزِي بِهِ ، يَدَعُ شَهْوَتَهُ وَطَعَامَهُ مِنْ أَجْلِي ) رواه مسلم (1151 .
“እያንዳንዱ የአደም ልጅ (መልካም) ስራ ይታጠፋል፡፡ መልካም ስራ በአስር አምሳያዎቿ ነው (የምትታሰበው)፣ እስከ 700 እጥፍ ድረስ፡፡ አሸናፊውና የላቀው አላህ እንዲህ ብሏል፡ “ፆም ሲቀር፡፡ እሱ ለኔ ነው፡፡ እኔ (በተለየ) እመነዳበታለሁ፡፡ ስሜቱንና ምግቡን ለኔ ሲል ስለተወ፡፡” [ሙስሊም፡ 1151]
ፆም የሶብር ክፍል ነው፡፡ ታጋሾችን በተመለከተ ደግሞ አላህ እንዲህ ይላል፡-
( إنما يوفى الصابرون أجرهم بغير حساب )
“ታጋሾቹ ምንዳቸውን የሚስሰጡት ያለ ሂሳብ ነው፡፡” [አዝዙመር፡ 10]
ማሳሰቢያ፡-
የሸዋል ስድስቱን ቀናት ከዒድ አልፊጥር በኋላ አስከትሎ መፆሙ በላጭ ቢሆንም እስከ ወሩ መጨረሻ ድረስ መፆም እንደሚቻል በርካታ ዐሊሞች ይገልፃሉ፡፡
(ኢብኑ ሙነወር፣ ረመዳን 29/1437)