ሸይኽ ሙቅቢል ኢብኑ ሃዲ አልዋዲዒ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡-
“እኛ ወደ አብዮትና መፈንቅለ-መንግስት አንጣራም፡፡ ምክንያቱም ጦሱ ለሙስሊሞች ነውና፡፡” [ፈዳኢሕ ወነሳኢሕ፡ 105]
መፈንቅለ መንግስት ቱርክም፣ ግብፅም፣ ሊቢያም፣ … በኢኽዋንም፣ ኢኽዋንም ላይ … ቢፈፀም የተወገዘ ነው፡፡ በመሪ
ላይ መውጣት የሚከለክሉ ሸሪዐዊ ማስረጃዎችን ቡድናዊ ጥላቻም ቡድናዊ ወገንተኝነትም ሳይዝህ ተቀበል፣ እመንም፡፡
ከቀደምት ዑለማዎች አንዱ እንዲህ ብለው ነበር፡- “የቢድዐ ሰዎች የሚደግፋቸውን ይወስዳሉ፡፡ የሚነቅፋቸውን ግን
ይተዋሉ፡፡ የሱንና ሰዎች ግን የሚደግፋቸውንም የሚነቅፋቸውንም ይወስዳሉ፡፡” ወንድም እህቶች መንገዳችንን የሱንና
መንገድ እናድርግ፡፡ በሌላውም ላይ በራሳችንም ላይ ሚዛናዊነት መታወቂያችን ይሁን፡፡ ጌታችን እንዲህ ይላል፡-
يَاأَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا كُونُوا قَوَّامِينَ بِالْقِسْطِ شُهَدَاءَ
لِلَّهِ وَلَوْ عَلَى أَنْفُسِكُمْ أَوِ الْوَالِدَيْنِ وَالْأَقْرَبِينَ
... النساء: ١٣٥
“እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በትክክል (በፍትሕ) ቋሚዎች፣ በነፍሶቻችሁ ወይም በወላጆችና በቅርብ ዘመዶች ላይ ቢሆን እንኳን ለአላህ መስካሪዎች ሁኑ፡፡” [አንኒሳእ፡ 135]