በዘረጋው መረብ በስሜት ወጥመዱ
በተንኮል ተብትቦ በላከው ገመዱ
ቀልብህን ሊነጅስ በኢንተርኔት ጉዱ
ሰይፍ ሳይታጠቅ መጣብህ ጠላቱ
አንተን ሊያኮላሽህ ቆርጦ ባዲስ ስልቱ
ሴት ዝሙት በትኖ በየዌብ ሳይቱ
ምርኮኛ ሊያረግህ ለዛ ለክርፋቱ
በጨምላቃ ስራው ሰይጣናዊ ስልቱ
መጣብህ ጠላቱ!!
በርታ በል ወንድሜ ሳያሽመደምዱህ
ወደ ፊስቁ መንደር አፍዘው ሳይወስዱህ
ቤትህን ሳይወሩት በክፉ ጥሪያቸው
ሳይደበላልቁህ ወደ ብልግናቸው
ነቃ በል ወንድሜ ታጥቀህ ግጠማቸው
በርታ በይ እህቴ ከቶ አታንቀላፊ
በሰይጣኖች ሴራ እንዳትጠለፊ!