Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ዊላያ'


ዊላያ'
አንብበው ሲጨርሱ SHARE ማድረግ አይርሱ!
ቀደም ባለው ፓስት(http://bit.ly/29Ymu33) ሺዓዎች አምስቱን የኢስላም ማእዘናት በማዛባት ዋነኛውንና የሙስሊሞች አርማ የሆነውን 'ላኢላሀኢለላህ' በማንሳት በምትኩ 'ዊላያ' በማለት አዲስ ማእዘን ፈልስፈው ማስቀመጣቸውን አይተን ነበር።
ሺዓዎች 'ዊላያ' በማለት የሚፈልጉበት እነርሱ የነቢዩ(ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ቤተሰቦች (አህለል-በይት) ናቸው ብለው የሚዘረዝሯቸውን ብቻ መውደድ እና በተለያየ ምክንያት አህለል-በይት ጋር ያልተስማማን ሁሉ ያለልዩነት መጥላት ላይ ያተኮረ ነው።
አህሉሱናዎች ከነቢዩ(ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ቤተሰቦች ኢስላምን የተቀበሉትን (አህለል-በይት) እንደ የነቢዩ(ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ባለቤቶች፣ የሰለሙ አጎቶች እና ልጆቻቸው፣ እንዲሁም የነቢዩ(ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ልጆች የልጅ ልጆች እና ዝርያቸውን በሙሉ አህለል-በይት አድርገው ይቆጥራሉ። ታዲያ ሸሪዓችን ያዘዘን እነኝህን በሙሉ እንድንወድ እና እንድናግዝ ቢሆንም ሺዓዎች ግን ከአህለል-በይት የተወሰኑትን ብቻ ማለትም ዓሊይን፣ ፋጢማ(ረዲየላሁ ዓንሁማ) እና በነርሱ ዝርያ የመጣውን ብቻ በመነጠል እንወዳለን ብለው ሲሞግቱ በውዴታቸው ላይም ከታዘዝንበት ድንበር በማለፍ ሲሄዱና ይህንን በማድረጋቸው የማይተባበራቸውን ሁሉ ልክ እንደ አህለል-በይት ጠላት አድርጎ በመቁጠር ከባድ ስህተት ላይ ወድቀዋል።
በዚህ ብቻ አላበቃም ከላይ እንደጠቀስነው ሺዓዎች ይህን ድንበር ያለፈ አቋማቸውን ልክ እንደ አንድ የእስልምና ማእዘን በመቁጠር ሰዎችን ሙስሊም ወይም ካፊር የማድረጊያ ሚዛን አድርገው አርፈዋል። እናም ያለምንም ማስረጃ በልብ ወለድ በመነሳት ትልቁን የኢስላም ማእዘን 'ላኢላሀኢለላህን' ገርስሰው ያንን በከፊል አጓድለው በቀሪው ድንበር ያለፉበትን አቋማቸውን የሚያንፀባርቁበትን 'ዊላያ' የኢስላም ማእዘን አድርገው አስቀምጠዋል።
ዊላያ ሺዓዎች ዘንድ ሁላቸውም የሚያቀነቅኑት ዜማ ነው። እያጓደሉትና ድንበር እያለፉበት ከትክክለኛው ትእዛዝ ባፈነገጠ መልኩ የሚፈፅሙት የስህተቶቻቸው መሸከርከሪያ ዋልታም ነው። ዊላያ መስራቻቸው አይሁዳዊው ኡብን ሰበእ ( http://goo.gl/xDEoZk ) የፈጠረው ልዩ እምነታቸውም ነው።
ሺዓዎች ዊላያን ከኢስላም ማእዘናት አንዱ በማድረግ ብቻ አልታቀቡም ይልቁኑ ቅጥፈታቸውን በመቀጠል ከቁርአንም ጋር አቆራኝተውታል። ወደፊት በስፋት እንደምንገልፀው አንዳንድ ሺዓዎች ቁርአን ተጨምሮ እና ተቀንሶበታል የሚል እምነት ሲኖራቸው ይህንንም ጥቂቶቹ ግልፅ እስከማውጣት ደርሰዋል።
ለዛሬ ግን ሺዓዎች በዚሁ ድንበር በሚያልፉበት ዊላያ ዙሪያ የወረደ የቁርአን አንቀፅ እንደነበረ እና ሶሀባዎች እንደሰወሩት አድርገው ሲቀጥፉ ከርመዋል። ለመረጃ ያክል ከሺዓ ዓሊሞች ቀንደኛ የሆነው ሚራዝ ሁሴን አጡብሩሲ (1320ሂ) ቁርአን ተበርዟል የሚለው አቋማቸውን ለማስረገጥ በፃፈው 'ፈስሉል ኺጣብ ፊኢስባቲ ተህሪፊ ኪታብ ረቢ አልአርባብ' በተሰኘው ከመቶ በላይ የሺዓ ዓሊሞችን አቋም የገለፀበት ኪታቡ ላይ ቁርአን ጎዶሎ ነው ሲል ፅፏል። በዚሁ ኪታቡ ገፅ 180 ላይ ሺዓዎች ዘንድ የሚታመንበትን የዓሊይን ደረጃ ሊገልፅ የወረደ ነገር ግን በእጃችን ከሚገኘው ቁርአን የተቀነሰ አንድ ሱራ(ምዕራፍ) እንደነበረ ይገልፃል። ሱራው 'ሱራ አል-ዊላያ' እንደሚባል አስፍሮ ያካትታል የሚሏቸውን አናቅፅት ይዘረዝራል። (ሺዓዎች ከቁርአን ጎደለ የሚሉትን ሱራ በምስሉ ላይ ይመልከቱ)
ግን ግን ሺዓዎች ይህን የአላህ ቃል ምን ይሉት ይሆን?
" ﺇﻧﺎ ﻧﺤﻦ ﻧﺰﻟﻨﺎ ﺍﻟﺬﻛﺮ ﻭﺇﻧﺎ ﻟﻪ ﻟﺤﺎﻓﻈﻮﻥ" ﺍﻟﺤﺠﺮ 9
"እኛ ቁርኣንን እኛው አወረድነው፡፡ እኛም ለእርሱ ጠባቂዎቹ ነን" ሒጅር 9

[በሌላ ጊዜ በሰፊው ሺዓዎች ከቁርአን ጋር በተያያዘ የሚሉትን እንመጣበታለን]
ከላይ እንደተጠቀሰው ሺዓዎች ሱረቱል-ዊላያ ብለው የሚቀጥፉበት ልብወለድ ፅሁፍ ቁርአን ነው ብለው ከማመን አልፈው ለብቻው እያተሙ ያሰራጩም ነበር። እነዚህ ሺዓዎች ናቸው እንግዲህ ቁርአን ጎድሏል የሚል የኩፍር እምነት ደብቀው ነው ዛሬ ሀገራችን ድረስ በመምጣት በሺዓ እና በሱኒ መካከል ያለው ልዩነት የመዝሀብ ብቻ ነው፤ እኛ አንድ ነን እያሉን ያሉት!
እንዴት የነቢዩ(ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ዲንና በአይሁዳዊ መስራች የተቋቋመ እምነት አንድ ይሆናል?
ዱባና ቅል
ለየቅል!
አላህ ከእንዲህ ያለው ክህደት ይጠብቀን!
©ለአላህ ከዚያም ለታሪክ