Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ሰላተ ተራዊሕ ላይ ዱኣ ማብዛት እንዴት ይታያል? 【አሸይኽ ዑሰይሚን】

ሰላተ ተራዊሕ ላይ ዱኣ ማብዛት እንዴት ይታያል?
አንዳንድ የመስጂድ ኢማሞች ረመዳን ውስጥ ሰላተ ተራዊህ ላይ ዱዓ ሲያስረዝሙ አንዳንዶቹ ደግሞ በጣም ያሳጥራሉ።የትኛው ነው ትክክለኛ አካሄድ ?
መልስ፦"በዚህ ላይ ትክክለኛው አካሄድ በጣም አለማሰጠርና ከልክ በላይ አለማስረዘም ነው።
ሰዎች ላይ እንዲከበድ የሚያደርግ ከልክ በላይ ማስረዘም ተከልክሏል።
የአላህ መልክተኛ ሙዐዝ ኢብኑ ጀበል ሕዝቦቹ ላይ በጣም ማስረዘሙ ሲደርሳቸው እንደዛን ቀን ሲገስፁ ወይም ሲመክሩ ተቆጥተው አያውቁም።
ለሙዐዝም እንዲህ አሉት፦"አንተ ሙዑዝ ሆይ!ሰዎችን (በዲናቸው)ተፈታታኝ ነህን?
በዚህ ላይ ሰላማዊው አካሄድ ከሐዲስ የመጡትን ዱኣዎች ላይ መገታት ይኖርበታል።ትንሽ ቢጨምር ግን ችግር የለውም።
ቁኑት ማስረዘም ሰዎችን የሚያዳክምና የሚከብድ ለመሆኑ ምንም ጥርጥር የለውም።በተለይ በተለይ አቅመ ደካሞችን ።
አንዳንድ ሰው ለበኋላ ብሎ ያዘገየው ስራ ይኖረዋል፣ ኢማሙ ተራዊህን እሰካልጨረሰ ማቋረጥ አይወድም፣ይህ ከመሆኑ ጋር ከሱ ጋር መቀጠልም ይከብደዋል።
ስለዚህም ወንድሞቼ የመስጂድ ኢማሞች የምመክረው መሀከለኛ ቁኑት ያደርጉ ዘንድ ነው።እንደዚሁም ተራ የሆኑ ሰዎች (ከአሊም ምድብ የወጡ ሰዎች) ዱዓ ዋጂብ ነው ብለው እንደይገምቱ አንዳንዴ መተው ያስፈልጋል።
【አሸይኽ ዑሰይሚን】