Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

'ቃና' ሚሉት 'ሬት'



by: seada live
'ቃና' ሚሉት 'ሬት'
ማር ማር ያለህ ወገን
የጣፈጠህ 'እቤት'
እየፈረስክ ነው እየተፍረከረክ
ውሀ ሲወስድ አሉ እያሳሳቀ ነው
አፍዝዞ አደንዝዞ
ማንነት ገዝግዞ
እራስ አሳጥቶን
እንኳንስ ዘንቦብን
ድሮም ጤዛ ሳለን
ቃና መሳይ ጣዕም
ጎምዛዛ መጣብን
እንግዲ ከነቃን
በመስኮተ ድምፀት
ስልጣኔው እብለት
ከሆነብን ልማድ
ድብብቆሽ ቆሞ
አስቦና አልሞ
ትውልድህን አድን
ዘመቻ ካልገባን
እውነት ለመናገር
የእውነት እንከሽፋለን
ትውልድ አልቦ አገር
አገር አልቦ ትውልድ
በእቅፋችን አለን (አለን ሲጠብቅ)