Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ፆም ክፍል ስድስት (6)

ፆም📙
📩 ክፍል ስድስት (6)
ካለፈው የቀጠለ…
🌴 የፆም መጀመሪያ እና ማብቂያን በተመለከተ ~
👉አላህ ሱብሐነሁ ወተዓላ ምግብና መጠጥ አስከ ጎህ ድረስ ፈቅዷል።
ሰሑርን መብላት የተወደደ መሆኑ ከሚያመላክቱ ማስረጃዎች መካከል:–
👉 ቡኻሪና ሙስሊም ከአነስ ኢብኑ ማሊክ እንደዘገቡት ነቢዩ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም
"ስሑርን ተመገቡ ምክንያቱም ሰሑር በረካ (በረከት) አለውና" ብለዋል።
🔵 ሰሑርን መመገብ ተወዳጅ መሆኑ ብዙ ዘገባዎች መጥተዋል።
ውሃን በመጎንጨት እንኳ ቢሆን
ሰሑርን ጎህ ግልፅ አስኪል ድረስ ማቆየቱ ተወዳጅ ነው።
🔸ጎህ ከመውጣቱ በፊት አንድ ሰው ጀናባ (ከሕጋዊ ባለቤቱ ጾታዊ ግንኙነት ወይም በህልም የፍትወት ፈሳሽ ቢያፈስ) ሆኖ ቢነሳ ወይም የሴት ልጅ ከወር አበባ ወይም ከወሊድ ደም ብትፀዳ~
ቅድሚያ ሰሑር መብላት ይኖርባቸዋል።
ጾምን ይጾማሉ።
መታጠቡን ጎህ እስኪወጣ ድረስ ማቆየት ይችላሉ።
አንዳንድ ሰዎች ሌሊቱን ቁጭ ብለው ስለሚያመሹ ሰሑርን ቀደም ብለው በልተው ሱብሒ ሳይደርስ ቀድመው ይተኛሉ። እነዚህ ሰዎች ብዙ ስህተቶችን ፈጽመዋል። ከነዚህም:–
1ኛ· ቀድመው ጾም መጀመራቸው
2ኛ· አላህ ግዴታ ያደረገባቸውን ሱብሒ ሰላትን በጀማዓ ባለመስገድ አላህን ማመጻቸው
3ኛ· ሱብሒን ከወቅቱ አሳልፈው ጸሐይ ከወጣች በኋላ ሊሰግዱም ይችላሉ። ይህ ደግሞ ከታላላቅ ወንጀሎች እና ሀጢአቶች ነው።
ሰላት ከወቅቱ ማቆየትን በተመለከተ አላህ በቁርአን ውስጥ እንዲህ ይላል ~
"ወዮላቸው ለሰጋጆች ለእነዚያ እነርሱ ከስግደታቸው ዘንጊዎች ለኾኑት፤ (ሰጋጆች)፡፡" (አልማዑን 4–5)
🔸ግዴታዊ ጾም ከሆነ በሌሊት ኒያ (ቁርጠኛ ሐሳብ) ማድረግ ግዴታ ነው።
በሌሊት እጾማሉ ብሎ ነይቶ ነገርግን ለሰሑር ሳይነሳ ቢነጋበት ምንም ችግር የለውም ጾሙንም ሊቀጥል ይችላል። ጾሙ በአላህ ፈቃድ ትክክል ይሆናል።
📙ምንጭ:–
አልሙለኸስ አልፊቅህ –ሼኽ ሳሊሕ አልፈውዛን (194)