Amir Tebibu
አላህ ይወፍቀን
ጠለሃ ኢብኑ ዑበይደላህ ረድየላሁዐንሁ እንዳስተላለፉት፦
《ሁለት ሰዎች ወደ መልክተኛው ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ይመጡና በተመሳሳይ ሰዓት ኢስላምን ይቀበላሉ።
አንደኛው ዒባዳ ላይ በጣም የተበራታ ሲሆን ደግሞ ሌላኛው ደግሞ ጅሃድን አብዝቶ ይሳተፍ ነበር ፤ እናም አንድ ቀን ጅሀድ ላይ ይገደልና ሸሂድ ይሆናል ፤ አንደኛው እርሱ ሌላኛው ከሞተ ከአንድ ዓመት በኋላ ይሞታል።
ጠለሃ እንዲህ ይላል "አንድ ቀን በህልሜ ከነዚህ ሁለት ሰዎች ጋር በጀነት በር ላይ ቆሜ ነበር ፤ አንድ ነገር ከበሩ ይወጠና ከመጀመሪያው ሟች ቀጥሎ የሞተውን ሰው ግባ ይለዋል ፤ ከዚያም ድጋሚ ይመጣና መጀመሪያ የሞተውን ግባ ይለዋል ፤ ከዚያም ወደኔ ዞር ብሎ ‘ አንተ ሂድ ተመለስ ያንተ ጊዜ ገና ነው ’ ይለኛል"።
ጠለሃ ከዕንቅልፉ እንደተነሳ ስላየው ህልም ለሰዎች ይነግራቸውና ሰዎቹም ይገረማሉ ፤ እናም ይህ ወሬ መልክተኛው ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ጋር ይደርሳል ፤ እሳቸውም ሰዎቹን "ምንድ ነው ያሰደነቃቹ?" ብለው ይጠይቃሉ።
ሰዎቹም አንደኛው ጅሀድን አብዝቶ ይሳተፍ ነበር ሸሂድ ሆኗልም ነገር ግን ቅድሚያ ጀነትን እንዲገባ የተደረገው ቀጥሎ የሞተው ነው።"አሏቸው
የአላህ መልክተኛው ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ፤ " ቀድሞ ጀነትን የገባው ሰው ከመጀመሪያው አንድን ዓመት በሕይወት አልቆየምን?" ሰዎቹም አዎን ሲሉ መለሰ
የአላህ መልክተኛም ሰለላሁ አለህሂ ወሰለም ፡ " ረመዳንን አላገኘምን?
አልፆመምን? ፤
ይሄን ይሄን ያክል ሰላት አልሰገደምን ?"
ሰዎቹም አዎን አሉ።
የአላህ መልክተኛም ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ፦" ታዲያ በርሱና በዛኛው ሰውዬ መካከል የሰማይና የምድር ያክል በላይ ልዩነት አለ" አሏቸው።》

ኢብን ማጃህ (2/344,346)፤ ሸኽ አልባኒ በሲልሲላ አ‘ሰሂሃ ሰሂህ ብለውታል ።