Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

አላህ ከአርሽ በላይ ነው አላህ ከአርሽ በላይ ነው፤ አላህ ከፍጡራኑ ሁሉ ተነጥሎ የበላይ ነው ‹‹በዛቱ››፡፡

by Sadat Kemal Abu Nuh

ኢስራ ወል ሚዕራጅ፡፡ አህባሾች የሚከተሉትን መልስ እንዲመልሱ እንጠይቃቸዋለን
በአላህ ስም እጅግ በጣም አዛኝ እጅግ በጣም ሩህሩህ፡፡ የአላህ ሰላትና ሰላም በነብያት መደምደሚያ በሆኑት ነብዩና ሙሃሙድ፤ በቤተሰቦቻቸው፤ በሰሃባዎቻቸው እና የሳቸውን እና የሰሃባዎችን ፈለግ በተከተለ ሁሉ ላይ ይሁን፡፡ በመቀጠል
1. በለይለተል ኢስራ ወል ሚዕራጅ ያምናሉን?
ይህንን የነብያችን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ወደ አለማቱ ጌታ ሰላትን በትዕዛዝነት ለመቀበል፤ ከመስጂደል ሀረም ተነስተው መስጂደል አቅሷ ድረስ… በቡራቅ… ከዛም ጂብሪል (አለይሂ ሰላም) እሳቸውን ይዞ ወደ ሰማይ ያረገበትን ማመን ማንም ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው፡፡ አላህም እንዲህ ሲል ያስቀምጠዋል፡፡
سُبْحَانَ الَّذِى أَسْرَى بِعَبْدِهِ لَيْلاً مّنَ الْمَسْجِدِ الْحَرَامِ إِلَى الْمَسْجِدِ الاْقْصَى الَّذِى بَارَكْنَا حَوْلَهُ لِنُرِيَهُ مِنْ ءايَـتِنَآ إِنَّهُ هُوَ السَّمِيعُ البَصِيرُ
ያ ባሪያውን ከተከበረው መስጊድ ወደዚያ ዙሪያውን ወደ ባረክነው ወደ ሩቁ መስጊድ በሌሊት ውስጥ ያስኼደው (ጌታ) ጥራት ይገባው፡፡ ከተዓምራቶቻችን ልናሳየው (አስኼድነው)፡፡ እነሆ እርሱ (አላህ) ሰሚው ተመልካቺው ነው፡፡
ይህንን የተባረከ የነብያችን ጉዙ ወዴት ነው ብለው ይጠረጥራሉ፡፡ አማኞች ሁሉ እንደሚያምኑት ወደ አላሁ (ሱብሃነሁ ወተዓላ) ነው፡፡ ሰላትን ለመቀበል፡፡
2. ካመኑ ነብያችን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ጂብሪል የት ይዟቸው ሄደ?
ነብያችን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ይላሉ قَالَ: ثُمَّ عُرِجَ بِي إِلَى السَّمَاءِ الدُّنْيَا فَاسْتَفْتَحَ جِبْرِيلُ فَقِيلَ لَهُ: مَنْ أَنْتَ؟ قَالَ: جِبْرِيلُ. قِيلَ: وَمَنْ مَعَكَ؟ قَالَ: مُحَمَّدٌ. قِيلَ: وَقَدْ أُرْسِلَ إِلَيْهِ؟ قَالَ: قَدْ أُرْسِلَ إِلَيْهِ. فَفُتِحَ لَنَا
<<ወደ ቅርቢቱ አለም ሰማይ (ሰማዓ ዱንያ) አረግን፤ ጂብሪል እንዲከፈትለት ጠየቀ፤ (የመጀመሪያው ጀነት ጠባቂ) ማን ነህ አለ? ጂብሪል ነኝ አለ፡፡ ካንተ ጋር ማን አብሮህ አለ ተባለ? ሙሃመድ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) አለ፡፡ (የሰማይ ጠባቂው) ተፈቅዶለታልን? (ብሎ ጠየቀ)፤ (ጂብሪልም) አዎን ተፈቅዶለታል አለ፡፡ (ከዛም) ተከፈተልን (አሉ ነብያችን)……ከዛም አደም (አለይሂ ሰላምን) አገኘሁአሉ……..
በያንዳንዱ ሰማይ ላይ ይሀው ጥያቂ እያጋጠማቸው እናም ውስጡ ነብያትን እያገኙ ሰባቱን ሰማይ አቋርጠው ሄዱ (ፈሰለዋቱ ረቢ ወሰላሙ አለይሂ) ሲድረቱል ሙንተሃ እስኪደርሱ ድረስ
3. ከሲደረተል ሙንተሃ ቀጥሎ ምን አጋጠማቸው?
ነብያችን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ከሲደረተል ሙንተሃ በኋላ ምን እንዳጋጠማቸው ሲናገሩ
فَأَوْحَى اللهُ إِلَيَّ مَا أَوْحَى، وَقَدْ فَرَضَ عَلَيَّ فِي كُلِّ يَوْمٍ وَلَيْلَةٍ خَمْسِينَ صَلَاةً
አላሁ(ሱብሃነሁ ወተዓላ) ወደ እኔ የሚያወርደውን መለኮታዊ ራዕይ አወረደ፤ በቀን እና በሌሌት 50 ሰላት ግዴታ አደረገብኝ፡፡
4. አላህ በምን ወህይ አደረገላቸው?
አላህ ወህይ ያደረገላቸው በቀን እና በሌሌት 50 ሰላትን ግዴታ አደረገባቸው፡፡
5. ወደ 6ኛው ሰማይ ሲወርዱ (የወረዱት ከበላይ መሆኑን አይዘንጋ፤ አላህን አናግረው ነው የወረዱት) ማንን አገኙ ነብያችን ማንን አገኙ?
ይህንን የአላህ ድንጋጌ ይዘው ሲመለሱ፤ 6ኛው ሰማይ ላይ ነብየላህ ሙሳ (አለይሂ ሰላምን) አገኙዋቸው፡፡ ነብየላህ ሙሳም (አለይሂ ሰላም) እንዲህ ብለው ነብያችንን ጠየቋቸው
مَا فَرَضَ رَبُّك عَلَى أُمَّتِكَ؟ قُلْتُ: خَمْسِينَ صَلَاةً فِي كُلِّ يَوْمٍ وَلَيْلَةٍ
ጌታህ ኡመትህ ላይ ምንን ግዴታ ደነገገባቸው? ነብያችንም (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) 50 ሰላት በእያንዳንዱ ቀን እና ሌሌት ብለው መለሱ፡፡
6. ነብያችን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሙሳን ካናገሩ በኋላ ወዴት ተመለሱ?
ነብየላህ ሙሳ (አለይሂ ሰላም) እንዲህ አላቸው قَالَ:ارْجِعْ إِلَى رَبِّكَ فَاسْأَلْهُ التَّخْفِيفَ لِأُمَّتِكَ، فَإِنَّ أُمَّتَكَ لَا تُطِيقُ ذَلِكَ وَإِنِّي قَدْ بَلَوْتُ بَنِي إِسْرَائِيلَ وَخَبَرْتُهُمْ، قَالَ: فَرَجَعْتُ إِلَى رَبِّي فَقُلْتُ أَيْ رَبِّ خَفِّفْ عَنْ أُمَّتِي فَحَطَّ عَنِّي خَمْسًا، فَنَزَلَتُ حَتَّى انْتَهَيْتُ إِلَى مُوسَى فَقَالَ: مَا فَعَلْتَ؟ فَقُلْتُ: قَدْ حَطَّ عَنِّي خَمْسًا فَقَالَ: إِنَّ أُمَّتَكَ لَا تُطِيقُ ذَلِكَ فَارْجِعْ إِلَى رَبِّكَ فَاسْأَلْهُ التَّخْفِيفَ لِأُمَّتِكَ
ወደ ጌታህ ሂድና እንዲያቀልልህ ጠይቀው
(ሙሳም እንዲህ ሲሉ ጠቆሙ) ያንተ ኡመቶች ይህን አይችሉትም፤ እኔ በኒ ኢስራኤሎችን ………..
ነብያችን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ይላሉ ‹‹ወደ ጌታዬ ተመለስኩና፤ ጌታዬ ሆይ ቀንስልኝ ከኡመቲ ላይ አልኩት፤ 5 ቀነሰልኝ›› አሉ
ነብያችን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) አስቀንሰው ሲመለሱ አሁንም ነብየላህ ሙሳ (አለይሂ ሰላም) አገኙ፤ ሙሳም የቅድሙን ጥያቂ በድጋሚ ጠየቁ፤ ነብያችንም 5 ተቀነሰልኝ ሱሉ ተናገሩ፤ ሙሳም ደግመው ‹‹ኡመቶችህ አይችሉትም ወደ ጌታህ ተመለስና አስቀንስ›› አሉዋቸው…… ሰላት 5ስት ብቻ እስክትሆን ድረስ ነብያችን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ተመላለሱ (ወደላይ)
7. እነዚህን ጥያቄዎች አላህ ከፍጡራኑ ሁሉ፤ ከአርሽ በላይ መሆኑን ለማያረጋግጡ ይጠየቃሉ፡፡ ሰላትን የሚሰግዱት ማን ያዘዘውን ሰላት እና የት የታዘዘውን ሰላት ይሆን?