Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የሸይጧን ፉገራ ሰይጣን አዛኝ እና አሳቢ መስሎ ነው ጉድ የሚሰራው


******* ******* ******** ******* *******
በአላህ ስም እጅግ በጣም አዛኝ እጅግ በጣም ሩህ ሩህ፡፡ በመጨረሻው ነብይ፤ በአደም ልጆች አለቃ ላይ የአላህ ሰላትና ሰላም ይውረድ፤ በቤተሰቦቻቸው ላይ፤ በሰሃባዎቻቸው ላይ እና የእሳቸውን እና የሰሃባዎቻቸውን መንገድ እስከ ቂያማ ድረስ በተከተሉ ላይ ሁሉ ይሁን፡፡
በመቀጠል

እንደሚታወቀው ሸይጧን በ2 ይከፈላል፡፡ የሰው እና የጂን ሸይጧን፡፡ አላህም ይህን አስመልክቶ እንዲህ ይላል፡፡
ٱلَّذِى يُوَسْوِسُ فِى صُدُورِ ٱلنَّاسِ
«ከዚያ በሰዎች ልቦች ውስጥ የሚጎተጉት ከኾነው፡፡
مِنَ ٱلْجِنَّةِ وَٱلنَّاسِ
«ከጋኔኖችም ከሰዎችም (ሰይጣናት እጠበቃለሁ በል)፡፡»
አላሁ (ሱብሃነሁ ወተዓላ) የሰው ልጆችን እና ጂኖችን ለምን አላማ እንደፈጠራቸው ግልፅ ሆኖ ተቀምጧል እሱም
وَمَا خَلَقْتُ ٱلْجِنَّ وَٱلْإِنسَ إِلَّا لِيَعْبُدُونِ
ጋኔንንና ሰውንም (እኔን በብቸኝነት) እንዲያመልኩኝ እንጅ ለሌላ አልፈጠርኳቸውም፡፡

ሆኖም ሸይጧን ይህን ግልፅ አንቀፅ ለመጣስ ማታለያ እና ማፍዘዣ ሰበብ እና ምክንያት እንዲህ ሲል አስቀመጠ፡፡ የሚገርመው ግን ሁሌ አደም እና ሃዋን (አለይሂሙ ሰላምንም) ሲያሳስት አዛኝ እና አሳቢ መስሎ ነው፡፡

ኢኽላስን እና ሽርክን ለሰው ልጆች እንዲህ አድርጎ ሳለላቸው
1) ኢኽላስን፡- ሷሊሆችን (ደጋጎችን) ማዋረድ፤ የነሱን ሃቅ ማጓደል፡፡
2) ሽርክን (በአላህ ላይ ማጋራትን) ደግሞ ሷሊሆችን (ደጋጎችን) እና የነሱን ተከታዬች መውደድ፤ አድርጎ አሳያቸው፡፡
እነዚህን 2 ነጥቦች በምሳሌ ማብራራቱ ነገሩን የበለጠ ግልፅ ያደርገዋል፡፡

ለምሳሌ
የኑህ (አለይሂ ሰላም) ህዝቦች 5ቱን ደጋጎች ከፍ ከፍ አድርገው የአምላክነት ደረጃ ሁሉ ሰጧቸው፡፡ ሊረሳ የማይገባው አብደላህ ኢብን አባስ (ረድየላሁ አንሁም) እንዳሉት የኑህ ህዝቦችን ሸይጧን ነው በሰው ተመስሎ እዚህ ጉድ ውስጥ የከተታቸው፡፡

ነሳራዎች ነብየላህ ኢሳን (አለይሂ ሰላም) ከፍ ከፍ አድርገው ከሚገባው ቦታ እና ደረጃ ውጭ ወደ አምላክነት አደረሱት

የነብያችን ኡመት ውስጥም ነብያችንን ከሚገባቸው ቦታ በላይ ከፍ ከፍ አድርገው እሳቸው ላይ ሽርክ የፈፀሙ ብዛት አሉ፡፡ ተው ለነብያችን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) የሚገባቸውን ቦታ ብቻ ስጧቸው ሲባሉ ‹‹የነብያችን ውዴታ የላችሁም›› ይላሉ፤ አልፎም ሽርኩን ተውሂድ ተውዱን ሽርክ አድርገው ያዙት፡፡

ነብያችንን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ሲሉ የሚያወድሱ አሉ፤ ይህ ግን ውዳሴ ሳይሆን አላህ የጠላው ሽርክ ነው
‹‹አላሁመሰሌ አላ ሙሃመዴ
መገን ነቢ
የሁሉ ቀላቢ››
አላህ ደግሞ እንዲህ ይላል
۞ وَمَا مِن دَآبَّةٍ فِى ٱلْأَرْضِ إِلَّا عَلَى ٱللَّهِ رِزْقُهَا وَيَعْلَمُ مُسْتَقَرَّهَا وَمُسْتَوْدَعَهَا ۚ كُلٌّ فِى كِتَٰبٍ مُّبِينٍ
በምድርም ላይ ምንም ተንቀሳቃሽ የለችም ምግቧ በአላህ ላይ ያለ ቢኾን እንጂ፡፡ ማረፊያዋንም መርጊያዋንም ያውቃል፡፡ ሁሉም ግልጽ በሆነው መጽሐፍ ውስጥ ነው፡፡
አላህ ብቻ ነው የፍጡራኑ ብሎም የነብያችን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሲሳይ ለጋሽ፡፡

አልይ ኢብን አቢ ጣሊብ ላይ ድንበር አልፈው አላህ ነው የሚሉትም አሉ፡፡ ሲጀምሩ ግን የነብያችንን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ቤተሰብ እንከብራለን እንወዳለን ብለው ነበር የአልይ (ረድየላሁ አንሁም ) ልጆች የሆኑት ሀሰን እና ሁሴንም (ረድየላሁ አንሁማ) ላይ ሁሉ ለአላህ ብቻ የሚገባውን መብት አሳልፈው የሰጧቸው፡፡

አብድል ቃድር ጀይላኔ እና መሰሎችንም ሰዎች የሚያመልኳቸው እና የአላህን መብት የሚሰጧቸው ደጋጎችን አና ተከታዬቻቸውን እንከብራለን በሚል ስም ነው፡፡
በጣም የሚገርመው በዘመናችን እያየን እንዳለነው ሽርኩ ተውሂድ ተውሂዱ ሽርክ፤ ሱናው ቢድዓ ቢድዓው ሱና እየሆነ የእንግድነት ዘመን ላይ ደርሰናል፡፡

አላህ በብቸኝነት ይመለክ ከእርሱም ጋር መላኢካም ይሁን (ጂብሪልን፤ ሚካኢልን…..)፤ ነብይም ይሁን (ኡዘይር፤ ኢሳ፤ ሙሃመድ (ሰለላሁአለይሂ ወሰለም))፤ ሷሊሆችም ይሁኑ (አልይ፤ ፋጢማ፤ ሁሴን፤ ሀሰን፤ ዘይነብ (ረድየላሁ አንሁማ))

የነብያችንን እና የቅን መሪዎችን (አቡበክር፤ ኡመር፤ ኡስማን፤ አልይ (ረድየላሁ አንሁም)) ሱና እንያዝ ቢድዓ የተባለ ሁሉ በጠቅላላ እንራቅ ሲባል
ሸይጧኖች አዛኝ እና የሷሊሆችን መብት አስከባሪ እና ጠበቃ በመምሰል ሰውን ዘላለም እሳት ውስጥ
ወደሚያኖረው እሳት ውስጥ ይጠሩታል፡፡

አላህ ግን እንዲህ ቀጥተኛው መንገድ ምን እንደሆነ ሸይጧን ግን ግልፅ ጠላታችን መሆኑን እንዲህ ሲል አስቀምጦት ነበር
۞ أَلَمْ أَعْهَدْ إِلَيْكُمْ يَٰبَنِىٓ ءَادَمَ أَن لَّا تَعْبُدُوا۟ ٱلشَّيْطَٰنَ ۖ إِنَّهُۥ لَكُمْ عَدُوٌّ مُّبِينٌ
የአደም ልጆች ሆይ! ሰይጣንን አትገዙ፤ እርሱ ለእናንተ ግልጽ ጠላት ነውና በማለት ወደእናንተ አላዘዝኩምን?
وَأَنِ ٱعْبُدُونِى ۚ هَٰذَا صِرَٰطٌ مُّسْتَقِيمٌ
እኔን ተገዙኝም፤ ይህ ቀጥተኘ መንገድ ነው፤ (በማለትም)፡፡

ይህ ነው እውነታው፡፡ ሰዉ ያለውን ቢል አላህን በብቸኝነት ማምለክ ይህ ነው ቀጥተኛው መንገድ፡፡ ከዚህ ውጭ ያሉት ሸይጧን የሰውን ልጅ ወደ እሳት የሚጣራባቸው መንገዶች ናቸው፡፡
አላህ በትምህርቱ የምንጠቀም፤ እሱን በብቸኝነት የምናመልክ እና የመልክተኛውን ሱና ከሚከተሉት ያድርገን፡፡ ከአላህ ውጭ በሃሰት ከሚመለኩት እና ቢድዓ ከተባለ ሉላ እኛንም ዝርያዎቻችንም ይጠብቀን፡፡
የአላህ ሰላት እና ሰላም በመልክተኛው፤ በቤተሰባቸው፤ በሰሃባዎቻቸው እና ሱናቸውን ሁሉ በተከተለ ላይ ይሁን፡፡
በመቀጠል
እንደሚታወቀው ሸይጧን በ2 ይከፈላል፡፡ የሰው እና የጂን ሸይጧን፡፡ አላህም ይህን አስመልክቶ እንዲህ ይላል፡፡ ٱلَّذِى يُوَسْوِسُ فِى صُدُورِ ٱلنَّاسِ«ከዚያ በሰዎች ልቦች ውስጥ የሚጎተጉት ከኾነው፡፡مِنَ ٱلْجِنَّةِ وَٱلنَّاسِ«ከጋኔኖችም ከሰዎችም (ሰይጣናት እጠበቃለሁ በል)፡፡»አላሁ (ሱብሃነሁ ወተዓላ) የሰው ልጆችን እና ጂኖችን ለምን አላማ እንደፈጠራቸው ግልፅ ሆኖ ተቀምጧል እሱምوَمَا خَلَقْتُ ٱلْجِنَّ وَٱلْإِنسَ إِلَّا لِيَعْبُدُونِጋኔንንና ሰውንም (እኔን በብቸኝነት) እንዲያመልኩኝ እንጅ ለሌላ አልፈጠርኳቸውም፡፡
ሆኖም ሸይጧን ይህን ግልፅ አንቀፅ ለመጣስ ማታለያ እና ማፍዘዣ ሰበብ እና ምክንያት እንዲህ ሲል አስቀመጠ፡፡ የሚገርመው ግን ሁሌ አደም እና ሃዋን (አለይሂሙ ሰላምንም) ሲያሳስት አዛኝ እና አሳቢ መስሎ ነው፡፡
ኢኽላስን እና ሽርክን ለሰው ልጆች እንዲህ አድርጎ ሳለላቸው 1) ኢኽላስን፡- ሷሊሆችን (ደጋጎችን) ማዋረድ፤ የነሱን ሃቅ ማጓደል፡፡2) ሽርክን (በአላህ ላይ ማጋራትን) ደግሞ ሷሊሆችን (ደጋጎችን) እና የነሱን ተከታዬች መውደድ፤ አድርጎ አሳያቸው፡፡እነዚህን 2 ነጥቦች በምሳሌ ማብራራቱ ነገሩን የበለጠ ግልፅ ያደርገዋል፡፡
ለምሳሌ የኑህ (አለይሂ ሰላም) ህዝቦች 5ቱን ደጋጎች ከፍ ከፍ አድርገው የአምላክነት ደረጃ ሁሉ ሰጧቸው፡፡ ሊረሳ የማይገባው አብደላህ ኢብን አባስ (ረድየላሁ አንሁም) እንዳሉት የኑህ ህዝቦችን ሸይጧን ነው በሰው ተመስሎ እዚህ ጉድ ውስጥ የከተታቸው፡፡
ነሳራዎች ነብየላህ ኢሳን (አለይሂ ሰላም) ከፍ ከፍ አድርገው ከሚገባው ቦታ እና ደረጃ ውጭ ወደ አምላክነት አደረሱት
የነብያችን ኡመት ውስጥም ነብያችንን ከሚገባቸው ቦታ በላይ ከፍ ከፍ አድርገው እሳቸው ላይ ሽርክ የፈፀሙ ብዛት አሉ፡፡ ተው ለነብያችን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) የሚገባቸውን ቦታ ብቻ ስጧቸው ሲባሉ ‹‹የነብያችን ውዴታ የላችሁም›› ይላሉ፤ አልፎም ሽርኩን ተውሂድ ተውዱን ሽርክ አድርገው ያዙት፡፡ 
ነብያችንን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ሲሉ የሚያወድሱ አሉ፤ ይህ ግን ውዳሴ ሳይሆን አላህ የጠላው ሽርክ ነው‹‹አላሁመሰሌ አላ ሙሃመዴመገን ነቢ የሁሉ ቀላቢ››አላህ ደግሞ እንዲህ ይላል ۞ وَمَا مِن دَآبَّةٍ فِى ٱلْأَرْضِ إِلَّا عَلَى ٱللَّهِ رِزْقُهَا وَيَعْلَمُ مُسْتَقَرَّهَا وَمُسْتَوْدَعَهَا ۚ كُلٌّ فِى كِتَٰبٍ مُّبِينٍበምድርም ላይ ምንም ተንቀሳቃሽ የለችም ምግቧ በአላህ ላይ ያለ ቢኾን እንጂ፡፡ ማረፊያዋንም መርጊያዋንም ያውቃል፡፡ ሁሉም ግልጽ በሆነው መጽሐፍ ውስጥ ነው፡፡አላህ ብቻ ነው የፍጡራኑ ብሎም የነብያችን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሲሳይ ለጋሽ፡፡
አልይ ኢብን አቢ ጣሊብ ላይ ድንበር አልፈው አላህ ነው የሚሉትም አሉ፡፡ ሲጀምሩ ግን የነብያችንን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ቤተሰብ እንከብራለን እንወዳለን ብለው ነበር የአልይ (ረድየላሁ አንሁም ) ልጆች የሆኑት ሀሰን እና ሁሴንም (ረድየላሁ አንሁማ) ላይ ሁሉ ለአላህ ብቻ የሚገባውን መብት አሳልፈው የሰጧቸው፡፡
አብድል ቃድር ጀይላኔ እና መሰሎችንም ሰዎች የሚያመልኳቸው እና የአላህን መብት የሚሰጧቸው ደጋጎችን አና ተከታዬቻቸውን እንከብራለን በሚል ስም ነው፡፡በጣም የሚገርመው በዘመናችን እያየን እንዳለነው ሽርኩ ተውሂድ ተውሂዱ ሽርክ፤ ሱናው ቢድዓ ቢድዓው ሱና እየሆነ የእንግድነት ዘመን ላይ ደርሰናል፡፡ 
አላህ በብቸኝነት ይመለክ ከእርሱም ጋር መላኢካም ይሁን (ጂብሪልን፤ ሚካኢልን…..)፤ ነብይም ይሁን (ኡዘይር፤ ኢሳ፤ ሙሃመድ (ሰለላሁአለይሂ ወሰለም))፤ ሷሊሆችም ይሁኑ (አልይ፤ ፋጢማ፤ ሁሴን፤ ሀሰን፤ ዘይነብ (ረድየላሁ አንሁማ)) 
የነብያችንን እና የቅን መሪዎችን (አቡበክር፤ ኡመር፤ ኡስማን፤ አልይ (ረድየላሁ አንሁም)) ሱና እንያዝ ቢድዓ የተባለ ሁሉ በጠቅላላ እንራቅ ሲባልሸይጧኖች አዛኝ እና የሷሊሆችን መብት አስከባሪ እና ጠበቃ በመምሰል ሰውን ዘላለም እሳት ውስጥ ወደሚያኖረው እሳት ውስጥ ይጠሩታል፡፡
አላህ ግን እንዲህ ቀጥተኛው መንገድ ምን እንደሆነ ሸይጧን ግን ግልፅ ጠላታችን መሆኑን እንዲህ ሲል አስቀምጦት ነበር۞ أَلَمْ أَعْهَدْ إِلَيْكُمْ يَٰبَنِىٓ ءَادَمَ أَن لَّا تَعْبُدُوا۟ ٱلشَّيْطَٰنَ ۖ إِنَّهُۥ لَكُمْ عَدُوٌّ مُّبِينٌየአደም ልጆች ሆይ! ሰይጣንን አትገዙ፤ እርሱ ለእናንተ ግልጽ ጠላት ነውና በማለት ወደእናንተ አላዘዝኩምን?وَأَنِ ٱعْبُدُونِى ۚ هَٰذَا صِرَٰطٌ مُّسْتَقِيمٌእኔን ተገዙኝም፤ ይህ ቀጥተኘ መንገድ ነው፤ (በማለትም)፡፡
ይህ ነው እውነታው፡፡ ሰዉ ያለውን ቢል አላህን በብቸኝነት ማምለክ ይህ ነው ቀጥተኛው መንገድ፡፡ ከዚህ ውጭ ያሉት ሸይጧን የሰውን ልጅ ወደ እሳት የሚጣራባቸው መንገዶች ናቸው፡፡አላህ በትምህርቱ የምንጠቀም፤ እሱን በብቸኝነት የምናመልክ እና የመልክተኛውን ሱና ከሚከተሉት ያድርገን፡፡ ከአላህ ውጭ በሃሰት ከሚመለኩት እና ቢድዓ ከተባለ ሉላ እኛንም ዝርያዎቻችንም ይጠብቀን፡፡የአላህ ሰላት እና ሰላም በመልክተኛው፤ በቤተሰባቸው፤ በሰሃባዎቻቸው እና ሱናቸውን ሁሉ በተከተለ ላይ ይሁን፡፡