Abu Ibrahim Mohammed Ibrahim
ታላላቆች ሲናገሩ ሌሎች ሊያደምጡ ይገባል!
ታላላቅ ዑለማዎች ማህበር/ጀምዒያ ማቋቋም የሚፈቀድ እና ለመልካም እስከዋለ ድረስ የሚወደስ መሆኑን መግለፃቸውን በተለያየ ግዜ በተለቀቁ ፓስቶች አይተናል። ሰብሰብ ለማድረግና በቀላሉ ለማግኘት እንዲመች በማለት የሰማሐቱ ሸይኽ አብዱልዓዚዝ ኢብን ባዝ፣ የፈዲለቱ ሸይኽ ሙሐመድ ቢን ሷሊህ አል-ዑስይሚን እና የኢማም ሙሐመድ ናሲሩዲን አል-አልባኒ ገለፃዎችን በአንድ ላይ እዚህ ያገኙታል ...
______________________________________
ሸይኽ ኢብኑ ባዝ ስለ ጀምዒያ/ማህበር ምን አሉ ...
ሽይኽ ኢብን ባዝ እንዲህ አሉ ፦ "በሙስሊሞች መካከል መልካም ለመዋል፣ ለመረዳዳት፣ በበጎ ነገር እና አላህን በመፍራት ላይ ለመደጋገፍ በየትኛውም ኢስላማዊ ሀገር ማህበራት ቢበዙ የአባላቱ ስሜት እስካልተቃረነ ድረስ በረካውና ጥቅሙ የበዛ ኸይር ነገር ነው። ነገር ግን እያንዳንዳቸው ሌላውን የሚያጠሙ ስራቸውንም የሚያፈርሱ ከሆነ በነርሱ የሚመጣው ጉዳት ከፍተኛ ነው። መጨረሻውም አደጋ ነው።" መጅሙዕ አል-ፈታዋ 5/202
______________________________________________
ሸይኽ ዑሰይሚን ስለ ጀምዒያ(ማህበራት) ምን አሉ? ...
ሸይኽ ኢብኑ ዑሰይሚን በሸርህ ሪያዱ-ሷሊሂን ላይ ይህን ሐዲስ አስከትለው እንዲህ ይላሉ ...
አቢ-ሙሳ አል-ዓሽዓሪይ(ረ.ዓ) የአላህ መልእክተኛ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል አሉ ...
"አሽዓሪዮች(ከየመን የመጡ ጎሳዎች ናቸው) በዘመቻ ላይ ስንቅ የቀለለባቸው ግዜ ወይም በከተማ ሳሉ የቤተሰባቸው መብል ባነሰ ወቅት ያላቸውን ሁሉ በአንድ ጨርቅ ላይ ይሰበስቡና በአንድ እቃ እኩል እኩል ይካፈላሉ። እነርሱ ከኔ ናቸው እኔ ተነሱ ነኝ" ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል
ይህንን ሐዲስ ታላቁ የዘመናችን ዓሊም ሸይኽ ሙሐመድ ሷሊህ አል-ዑሰይሚን(ረሂመሁላህ ) ሲያብራሩ እንዲህ አሉ ...
"አቡ-ሙሳ አል-አሽዓሪይ እና ጓዶቹ(ረዲየላሁ ዓንሁም) ከየመን ጎሳዎች ነበሩ። እነርሱ በጉዳዮቻቸው ላይ ይረዳዱ ነበር። ከገንዘብ ጥቂት የመጣላቸው ግዜ ባንድ ያደርጉትና እኩል ይካፈሉት ነበር። ታዲያ ነቢዩ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) "እነርሱ ከኔ ናቸው እኔም ከነርሱ ነኝ" አሉ። ይህን ያሉት ለሚሰሩት ስራ ማበረታቻ ነበር።
ይህ ሐዲስ ዛሬ አንዳንድ ሰዎች ለሚያደርጓቸው የመረዳጃ ማህበራት መሰረት ነው። አንድ ቡድን ይሰባሰብና የቻሉትን ያህል ገንዘብ የሚያሰባስቡበት ሳጥን አበጅተው ወይ በድርሻ አሊያም እንደጥረቱ እንደችሮታው ያዋጣል። ለምሳሌ ሁለት ከመቶ የሚሆነውን ከደመወዛቸው ወይም ከትርፋቸው ወይም ይህን ከመሰለው ላይ ለማዋጣት ይስማማሉ። በዚህ ሳጥን ያለው ከነርሱ መሀል አደጋ እና ችግር ለሚደርስበት ሰው ይውላል። ይህ የአቢ-ሙሳ(ረ.ዓ) ሐዲስ መሰረቱ ነው። ለዚህ ተግባር በሱና ውስጥ መሰረት አለው ይህም ተግባር ሸሪዓዊ ነው" የሸይኽ ዑሰይሚን (ረሂመሁላህ) ንግግር አበቃ
ሸርሕ ሪያዱ-ሷሊሂን ሐዲስ ቁጥር 568
ሸይኽ ኢብኑ ዑሠይሚን በህይወት በነበሩበት ጊዜ በ1405 አመተ ሂጅራ የተቋቋመው "ጀምዒየቱል ተሕፊዘል ቁርኣኑል ከሪም አልኸይሪያህ" የተባለ ማሕበር መሪ ነበሩ። ሸይኹ እስከ እለተ ሞታቸውም ድረስ የዚህ ጀምዒያ ሃላፊ ነበሩ። ረሒመሁላህ
_______________________________________________________________
ታላቁ ሙሐዲስ ኢማም ሙሐመድ ናሲሩዲን አል-አልባኒ(ረሂመሁላህ) ስለ ጀምዒያ ምን አሉ ...
ሸይኽ አልባኒ ድሆችና ድጋፍ ፈላጊዎችን በመርዳት እንዲሁም በመልካም ስራዎች ላይ ስለምትቆም ማህበር ሁክም ተጠየቁ።
ሸይኹ ሲመልሱ እንዲህ አሉ ...
"ይህች በጎ አድራጎት ማህበር እንደምትላት ከሆነች ነገሩ እንዲህ እንድንል ያደርገናል፤ በሁሉም ኢስላማዊ ሀገር ላይ ያለው ጉዳይ አንድ ነውና። የበጎ አድራጎት ማህበር እናንተ ዘንድ አለ፤ እኛም ጋር በሶሪያም ብዙ በጎ አድራጎት ማህበራት ሊኖሩ ይመቻል። ምላሹ በሁሉም የዱኒያ ሀገራት ላይ ያሉ ማህበራትን በተለይ ደግሞ በኩፍር ሀገር በአውሮፓ፣ በአሜሪካ በሌላውም ... የሚኖሩትን ያጠቃልላል፤ እነዚህ ማህበራት በሸሪዓ ድንጋጌዎች ላይ እስከቆሙ ድረስ የተፈቀዱ ናቸው። ይህ በጥቅሉ የአላህ ቃል ውስጥ ይካተታል ...
﴿ﺃَﺭَﺃَﻳْﺖَ ﺍﻟَّﺬِﻱ ﻳُﻜَﺬِّﺏُ ﺑِﺎﻟﺪِّﻳﻦِ﴾، ﻭﻓﻴﻬﺎ ﺑﻌﺪُ : ﴿ ﻭَﻟَﺎ ﻳَﺤُﺾُّ ﻋَﻠَﻰ ﻃَﻌَﺎﻡِ ﺍﻟْﻤِﺴْﻜِﻴﻦِ﴾
"ያንን በምርመራው የሚያስተባብለውን አየህን? (ዐወቅከውን?)" ከዛም እንዲህ ይላል "ድኻንም በማብላት ላይ የማያግባባው ሰው ነው"
ይህችን አንቀፅ ሁልግዜ እናነባታለን። ስለዚህ ምስኪኖችን በማብላት ላይ ማነሳሳት ይህ በሸሪዓ የተደነገገ ነው" ሸይኽ አልባኒ ንግግራቸው አበቃ።
ሲልሲለቱል ሁዳ ወኑር ካሴት ቁጥር 358
___________________________________________________
ይህንን የመሰለ ግልፅ ማብራሪያ ከዑለሞቻችን እንድናገኝ ላደረገን አላህ ምስጋና ይገባው!
ታላላቅ ዑለማዎች ማህበር/ጀምዒያ ማቋቋም የሚፈቀድ እና ለመልካም እስከዋለ ድረስ የሚወደስ መሆኑን መግለፃቸውን በተለያየ ግዜ በተለቀቁ ፓስቶች አይተናል። ሰብሰብ ለማድረግና በቀላሉ ለማግኘት እንዲመች በማለት የሰማሐቱ ሸይኽ አብዱልዓዚዝ ኢብን ባዝ፣ የፈዲለቱ ሸይኽ ሙሐመድ ቢን ሷሊህ አል-ዑስይሚን እና የኢማም ሙሐመድ ናሲሩዲን አል-አልባኒ ገለፃዎችን በአንድ ላይ እዚህ ያገኙታል ...
______________________________________
ሸይኽ ኢብኑ ባዝ ስለ ጀምዒያ/ማህበር ምን አሉ ...
ሽይኽ ኢብን ባዝ እንዲህ አሉ ፦ "በሙስሊሞች መካከል መልካም ለመዋል፣ ለመረዳዳት፣ በበጎ ነገር እና አላህን በመፍራት ላይ ለመደጋገፍ በየትኛውም ኢስላማዊ ሀገር ማህበራት ቢበዙ የአባላቱ ስሜት እስካልተቃረነ ድረስ በረካውና ጥቅሙ የበዛ ኸይር ነገር ነው። ነገር ግን እያንዳንዳቸው ሌላውን የሚያጠሙ ስራቸውንም የሚያፈርሱ ከሆነ በነርሱ የሚመጣው ጉዳት ከፍተኛ ነው። መጨረሻውም አደጋ ነው።" መጅሙዕ አል-ፈታዋ 5/202
______________________________________________
ሸይኽ ዑሰይሚን ስለ ጀምዒያ(ማህበራት) ምን አሉ? ...
ሸይኽ ኢብኑ ዑሰይሚን በሸርህ ሪያዱ-ሷሊሂን ላይ ይህን ሐዲስ አስከትለው እንዲህ ይላሉ ...
አቢ-ሙሳ አል-ዓሽዓሪይ(ረ.ዓ) የአላህ መልእክተኛ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል አሉ ...
"አሽዓሪዮች(ከየመን የመጡ ጎሳዎች ናቸው) በዘመቻ ላይ ስንቅ የቀለለባቸው ግዜ ወይም በከተማ ሳሉ የቤተሰባቸው መብል ባነሰ ወቅት ያላቸውን ሁሉ በአንድ ጨርቅ ላይ ይሰበስቡና በአንድ እቃ እኩል እኩል ይካፈላሉ። እነርሱ ከኔ ናቸው እኔ ተነሱ ነኝ" ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል
ይህንን ሐዲስ ታላቁ የዘመናችን ዓሊም ሸይኽ ሙሐመድ ሷሊህ አል-ዑሰይሚን(ረሂመሁላህ
"አቡ-ሙሳ አል-አሽዓሪይ እና ጓዶቹ(ረዲየላሁ ዓንሁም) ከየመን ጎሳዎች ነበሩ። እነርሱ በጉዳዮቻቸው ላይ ይረዳዱ ነበር። ከገንዘብ ጥቂት የመጣላቸው ግዜ ባንድ ያደርጉትና እኩል ይካፈሉት ነበር። ታዲያ ነቢዩ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) "እነርሱ ከኔ ናቸው እኔም ከነርሱ ነኝ" አሉ። ይህን ያሉት ለሚሰሩት ስራ ማበረታቻ ነበር።
ይህ ሐዲስ ዛሬ አንዳንድ ሰዎች ለሚያደርጓቸው የመረዳጃ ማህበራት መሰረት ነው። አንድ ቡድን ይሰባሰብና የቻሉትን ያህል ገንዘብ የሚያሰባስቡበት ሳጥን አበጅተው ወይ በድርሻ አሊያም እንደጥረቱ እንደችሮታው ያዋጣል። ለምሳሌ ሁለት ከመቶ የሚሆነውን ከደመወዛቸው ወይም ከትርፋቸው ወይም ይህን ከመሰለው ላይ ለማዋጣት ይስማማሉ። በዚህ ሳጥን ያለው ከነርሱ መሀል አደጋ እና ችግር ለሚደርስበት ሰው ይውላል። ይህ የአቢ-ሙሳ(ረ.ዓ) ሐዲስ መሰረቱ ነው። ለዚህ ተግባር በሱና ውስጥ መሰረት አለው ይህም ተግባር ሸሪዓዊ ነው" የሸይኽ ዑሰይሚን (ረሂመሁላህ) ንግግር አበቃ
ሸርሕ ሪያዱ-ሷሊሂን ሐዲስ ቁጥር 568
ሸይኽ ኢብኑ ዑሠይሚን በህይወት በነበሩበት ጊዜ በ1405 አመተ ሂጅራ የተቋቋመው "ጀምዒየቱል ተሕፊዘል ቁርኣኑል ከሪም አልኸይሪያህ" የተባለ ማሕበር መሪ ነበሩ። ሸይኹ እስከ እለተ ሞታቸውም ድረስ የዚህ ጀምዒያ ሃላፊ ነበሩ። ረሒመሁላህ
_______________________________________________________________
ታላቁ ሙሐዲስ ኢማም ሙሐመድ ናሲሩዲን አል-አልባኒ(ረሂመሁላህ)