📙ፆም📙
🍃 ሼኽ ሳሊሕ አልፈውዛን እንዲህ ይላሉ:~
🍃 ሼኽ ሳሊሕ አልፈውዛን እንዲህ ይላሉ:~
🌴 የፆም መጀመሪያ እና ማብቂያን በተመለከተ ~
👉አላህ ሱብሐነሁ ወተዓላ እንዲህ ይላል: –
በጾም ሌሊት ወደ ሴቶቻችሁ መድረስ ለናንተ ተፈቀደላችሁ፡፡ እነርሱ ለናንተ ልብሶች ናቸው፤ እናንተም ለነርሱ ልብሶች ናችሁ፡፡ አላህ እናንተ ነፍሶቻችሁን የምትበድሉ መኾናችሁን ዐወቀ፡፡ በእናንተም ላይ ተመለሰላችሁ፡፡ ከእናንተም ይቅርታ አደረገ፡፡ አሁን ተገናኙዋቸው፡፡ አላህም ለናንተ የጻፈላችሁን ነገር (ልጅን) ፈልጉ፡፡ ከጎህ የኾነው ነጩ ክርም ከጥቁሩ ክር (ከሌሊት ጨለማ) ለእናንተ እስከሚገልጽላችሁ ድረስ ብሉ፤ ጠጡም፡፡ ከዚያም ጾምን እስከ ሌሊቱ ድረስ ሙሉ፡፡…" አልበቀራህ 187
📌ኢብኑ ከሲር ከላይ የተጠቀሰውን አንቀጽ ሲተረጉም~
➡ ይህቺ አላህ ለባሮቹ የፈቀዳት ማቅለያ (ሩኽሷ) ናት።
🔸በመጀመሪያ ጊዜ ጾም ሲደነገግ አንድ ሰው ካፈጠረ በኋላ የሚፈቀዱ ነገሮች እንደ ምግብ ፣ መጠጥ እና ጾታዊ ግንኙነት እስኪተኛ ወይም ከዛ በፊት ብቻ ነበር።
❎ አንድ ሰው ዒሻ ከሰገደ በኋላ እንቅልፉን ከተኛ ከምግብ ፣ መጠጥ እና ጾታዊ ግንኙነት እስከ ቀጣዩ ሌሊት ይከለከላል። ይህ ሁኔታ በሙስሊሞች ላይ ከባድ ችግር ሲፈጥርባቸው አላህ ይህንን ማቅለያ (ሩኽሷ) አወረደ።
👍 በዚህም ምክንያት ሙስሊሞች በጣም ተደሰቱ።
✅ በሌሊት ክፍለ ጊዜ ሁሉም ነገሮችን ( ምግብ ፣ መጠጥ እና ጾታዊ ግንኙነትን) እውነተኛ ጎህ እስኪገለጽላቸው ድረስ ፈቀደላቸው።
👆ከዚህ አንቀጽ የጾም መጀመሪያውና መጨረሻው ግልጽ አደረገው።
➡መጀመሪያው ~ እውነተኛው ጎህ መውጣት ሲሆን
➡መጨረሻው ~ ፀሐይ መጥለቅ ይሆናል።
📙ምንጭ:–
አልሙለኸስ አልፊቅህ (193)