Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

በኢስላም ስም መነገድ፡፡

በኢስላም ስም መነገድ፡፡
‹‹ምርትና አገልግሎቶን ያስተዋውቁ ጂሉ ሚድያና ኮሚኒኬሽን››
የኢኽዋኖቹ የቢዝነስ መሰብሰቢያ ልሳን፡፡
ኢኽዋኖች ተነቃቅተናል፡፡

ኢኽዋኖች የአፍጡር ፕሮግራም የሚሉት መጃጃያ ቢዝነስ መሆኑን ከማስታወቂያው ተገንዝበናል፡፡
የነ ያሲን ኑሩ የአፍጡር ሰዓት ፕሮግራም በዲን ስም ንግዳቸውን ሊያጧጡፉ መሆኑን በአላህ ፍቃድ ተረድተናል፡፡
አላማው ቢዝነስ መሆኑን በግልፅ አይነግሩንም ነበር? ፖለቲካውንም በዲን ስም አጧጡፈው ነበር ሰውን የሸወዱት፡፡ ለምን ይሆን ሁሌ ሃይማኖትን ሽፋን አድርገው የሚወስዱት? አላህ ይምራቸው፡፡
በዲን ስም መነገድ እኮ ሁኔታውን ይቀያይራል እንጂ የተለመደ የኢኽዋኖች እና የሌሎችም የቢድዐ ሰዎች ስራ ነው፡፡
ለምሳሌ
1) የሽርክ መንዙማቸውን ረመዳን ላይ ጠብቀው የሚለቁት ሰዎች ቢዝነሱ የሚደራው በረመዳን ስለሆነ ነው፡፡
2) የቀብር አፈር ቆንጥረው የሚቸረችሩት ቀብር አምላኪዎችም እንደዚሁ ቢዝነስ ነው፡፡ እነሱ ግን ወልዬች…. ምናምን እያሉ ሰውን ወደ እሳት ይጠሩታል፣ ገንዘቡንም ይዘርፉታል፡፡
3) ኢስላማዊ ድራማ፣ ኢስላማዊ ፊልም፣ ኢስላማዊ ነሺዳ እያሉ በረመዳን የሚለቁትም እንዲሁ በረመዳን ቢዝነሱ ስለሚደራላቸው ነው፡፡
4) ዳእዋ ብለው ሰው ያለበትን ችግር የማይዳስሱ፣ አገራችን ላይ ያለውን የሽርክና የቢድዐ ችግር የማያነሱ ቪድዬም ይሁን ድምፅ ፋይል የሚሰሩት ለቢዝነስ ሲሉ ነው፡፡
አሁን ግን ሰው ሲነቃ፣ ሲባንን ደግሞ በሌላ ፎርም መጡ፡፡ ስንቶች 11 ወር ሙሉ የሰለቻቸውን ዳኢ ተብዬዎች መተወንና ማሳቅ ከሚችሉት በላይ የሆነውን የእግር ኳስ ጨዋታ፣ ዳርት፣ ገመድ ጉተታ እና ሌላም ከሌሎች አክተሮች አይተው ጨርሰው አሁን ደግሞ ሙስሊሙ ወደ ጌታው ቶብቶ በቃን ረመዳንን እንፁም፣ ዱዓ እናድርግ ሲል እናዝናናህ ብለው ዳኢ ተብየዎቹ በዲን ስም ይሀው ከተፍ አሉ፡፡ እንዲህም ሲሉ
‹‹ምርትና አገልግሎቶን ያስተዋውቁ ጂሉ ሚድያና ኮሚኒኬሽን››
እስቲ አላህ ያሳያችሁ የአላህ ባርያዎች! እነዚህ አጥማሚዎች በረመዳን ኡማው ቁርዓን እንዳይቀራ አሳቢ መስለው፣ እየተቅለሰለሱ ህዝቡን ጌታውን ለምኖ ወደ አላህ እንዳይቃረብ ሊያጃጅሉት፣ ሳቅ አብዝቶ ልቡን እንዲያደርቅ ሊያደርጉት….
አልሃምዱሊላህ ተነቃቃን ማስታወቂያዋን ወደ መጨረሻ ነው ያደረጓት፡፡
ኢኽዋኖች ሆይ! አንዴ በሰው ህይወት ትነግዳላችሁ፣ አንዴ በሙስሊሙ ንብረት ተነግዳላችሁ፡፡ ግን አላህ ሁሉን ተመልካች ነው፡፡
አንዳንድ ምስኪኖች ‹‹ሀሜት በረመዳን›› ይላሉ አላህ እውቀት ለእኛም ለነዚህም ምስኪኖች ይስጠን፡፡ ወንድምና እህቶቼ ሆይ! ይሄ ሀሜት አይደለም፡፡ አህባሽ የሚሰራውን እርኩስ ተግባር ስናጋልጥ ምንም ካላላችሁ ለምንድን ነው የነ ያሲን እና ኢኽዋኖች ሲሆን ጥብቅና የምትቆሙት?
እውነት አህባሽን ለጥመቱ ከነበር የጠላችሁት አህባሾችም ይሁኑ ሌሎች የሚሰሩትን ጥመት ለአላህ ስንል ልንቃወመው ይገባል፡፡
ሌላው እኛ እነዚህን አጥማሚዎች ማጋለጣችን ‹‹ሀሜት›› ከሆነ እነዚህ ሰዎች በኡማው ላይ መነገዳቸው ምን ሊሆን ነው?
ያሲን እና ጓደኞቹ ትላንት ሙስሊሙን በሰላማዊ ሰልፍና በፖለቲካ ዜና ረመዳኑን አዘናግታችሁት ነበር አሁን ደግሞ ልትነግዱበት ነው፡፡ አላህ ሁሉን ተመልካች ነው፡፡ ተውበት አድርጉ፡፡ እምቤ ካላችሁ ይዘህ ላጠመምካቸው ሁሉ ትጠየቃለህ፡፡

የአላህ ባርያዎች ሆይ! ሰው አፍጥር ሰዐት ላይ ጌታውን ለምኖ ዱዓ አድርጎ፣ ከዛም አፍጥሮ፣ ወደ መስጂድ በጊዜ ሄዶ አላህን ያመልካል እንጂ ጣሽ ማጣሽም ይሁን የነ ያሲን ማጃጃያ ላይ አይኑን አይተክልም፡፡
አላህ ሆይ! ሙስሊሙን በዚህ በተከበረው ወር ከማንኛውም ካንተ መንገድ ከሚያዘናጉ ሚድያዎች፣ ግለሰቦች፣ ቡድኖች፣ በሀይማኖት ስም ነጋዴዎች ጠብቀው፡፡
የአላህ ሰላትና ሰላም በሙሐመድ፣ በቤተሰቦቻቸው፣ በባልደረባዎቻቸውና ሀቅን በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን፡፡