ወንድማዊ ምክር
ወንድም እህቶች በተለይም እንዳቅሚቲ የምናውቃትን በማስተማር ላይ የተሰማራን አደራ አደራ አደራ!!! ስናስተምር ተማሪዎቻችንን ከታላላቅ ዑለማዎች ጋር እናስተዋውቅ፡፡ በተለይም ደግሞ ከሞቱት ጋር፡፡ ኢብኑ መስዑድ ረዲየላሁ ዐንሁ እንዲህ ይላሉ፡- “የሞቱትን ተከተሉ፡፡ በህይወት ያለ ፈተናው አይታመንምና፡፡” [ጃሚዑ በያኒል ዒልም ወፈድሊሂ፡ 2/947] እናስተውል!! ይሄ የተባለው የኔ ብጤ ውሪ በነገሰበት ዘመን ሳይሆን ታላላቆች በህይወት ባሉበት ዘመን ነው፡፡ ስናስተምር በእያንዳንዱ አቋማችን ከዑለማ ኋላ መሰለፍ እንዳለብን አበክረን እናስታውስ፡፡ አንዳንዱ “ኢብኑ ባዝ እንዲህ አሉ፣ ኢብኑል ዑሠይሚን እንዲህ አሉ” እያልከውም የኡስታዙን ቃል ማጣጣምን ይመርጣል፡፡ ይሄ አደገኛ የተርቢያ ብክለት ነው፡፡ በዚህ አይነቱ ብልሹ የማስተማር ዘዴ ብዙ ሰዎች ለብዙ አደጋ ሲጋለጡ ይታያል፡፡ ከአደጋዎቹ ሁሉ ይበልጥ የሚከፋው አደጋ ደግሞ የሚያስተምራቸው ኡስታዝ ፈር የለቀቀ ጊዜ የሚታየው ነው፡፡ ብዙዎች ግራ ቀኝ ከማገናዘብ ይልቅ አይናቸውን ጨፍነው የሰፈር ኡስታዛቸውን ተከትለው ገደል ይገባሉ፡፡ ወንድሜ ሆይ! ዐብዱላህ ኢብኒ መስዑድ በነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም አንደበት “የኡሙ ዐብድ ልጅ (ኢብኑ መስዑድ) የወደደውን ለህዝቦቼ ወድጃለሁ” ተብሎ የተመሰከረላቸው ናቸው፡፡ [አስሶሒሐህ፡ 1225] ታዲያ ይሄ ታላቅ ሶሐባ ምን እንደሚሉ ተመልከት፡- “አዋጅ!! ማንም ሰው በዲኑ ጉዳይ ሌላውን በጭፍን አይከተል። እንዲያ የሚያደርግ ከሆነ ሰውየው ሲያምን ያምናል፣ ሰውየው ሲከፍር ይከፍራል።” [አጥጦበራኒ: 9/152] ለሚያስተውል ሁሉ ይሄ እጅግ ወሳኝ መልእክት አለው፡፡ አዎ ሰው ከተከተልክ የሚከተልህ ይሄው ነው፡፡
በታሪክ በማይገመት መልኩ ወደ ኩፍር ወይም ወደ ቢድዐ በመጓዝ ለአደጋ የተጋለጡት ብዙ ናቸው፡፡ ወደ ሐበሻ ከተሰደዱት ሶሐቦች ውስጥ አንዱ የነበረው ዑበይዱላህ ኢብኒ ጀሕሽ ወደ ክርስትና በመግባት አፈንግጧል፡፡ ተመልከቱ በሃይማኖቱ ሳቢያ ስንት ተንገላቶ፣ አደገኛ የሆነውን የባህር ጉዞ አጠናቆ ግና በሚያሳዝን ሁኔታ መጨረሻው ክህደት ሆነ፡፡
የዐልይ ገዳይ የሆነው ዐብዱርረሕማን ኢብኒ ሙልጂም ቀድሞ አስደናቂ ጀብዱዎችን ሲፈፅም የኖረ ባለመልካም ዝና ሰው ነበር፡፡ እንዲያውም ኸሊፋው ዑመር ኢብኑል ኸጣብ ዘንድ የተከበረ ሰው እንደነበር ይነገራል፣ በጣም ቁርኣንን የሚቀራ፡፡ ዐምር ኢብኑል ዓስ ረዲየላሁ ዐንሁ ለዑመር የቁርኣን አስተማሪ ወደ ግብፅ እንዲልኩ ሲጠይቋቸው ለዚህ ትልቅ ተልእኮ ተመልምሎ የተላከው ይሄው ዐብዱርሕማን ኢብኒ ሙልጂም ነው ይባላል፡፡ መጨረሻው ግን በጀነት የተመሰከረለትን፣ የነብዩን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የአጎት ልጅ፣ የፋጢማን ባል፣ አራተኛውን ምርጡን ኸሊፋ ዐልይን ገደለ፡፡ ምን ፍለጋ? ጀነት ፍለጋ፡፡ የጀነትን ሰው እየገደሉ ጀነትን ፍለጋ፡፡ ይሄ ሰውየ ቀድሞ ጥሩ ሰው ቢሆንም መጨረሻው ግን አደገኛውና በመልእክተኛው ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም አንደበት “የጀሀነም ውሾች” የተባሉት የኸዋሪጅ ቢድዐ ሆነ፡፡ የፅናቱ ፅናት አካሉን እየቆራረጡት ቁጭ ብሎ ዚክር ያደርግ ነበር፡፡ ከዚህ ታሪክ ብዙ ቁም-ነገሮችን ልንማር እንችላለን፡፡ ከነዚህም አንዱ ኢኽላስ ብቻውን በቂ እንዳልሆነ ነው፡፡ ይሄ ሰውየ ዐልይን የገደለው ጀነትን ፍለጋ ቢሆንም ሙታበዐው ስለጎደለ፣ ቢድዐ ውስጥ ስለተነከረ ሁለቱንም አለሙን ከሰረ፡፡ በተጨማሪም ፅናት ብቻውን የሐቅ መለኪያ እንዳልሆነ እንረዳለን፡፡ ይሄ ሰውየ እስከመጨረሻ እስትንፋሱ በአቋሙ ፀንቶ ቀጥሏል፡፡ አቋሙ ግን ብልሹ ስለነበር ፅናቱ አልፈየደውም፡፡ በጥፋት ላይ ሆነው ፅናት በሚያንፀባርቁ ሰዎች ውጫዊ ገፅታ እንዳትሸወድ፡፡ ምን ቢፀኑ ከኸዋሪጅ በላይ አይፀኑም፡፡ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዴት እንደገለጿቸው ተመልከት፡- “(ብታነፃፅሩት) ሶላታችሁን ከሶላታቸው፣ ፆማችሁን ከፆማቸው፣ ስራችሁን ከስራቸው ትንቁታላችሁ፡፡” [ቡኻሪና ሙስሊም] እነዚህ አፈንጋጭ ኸዋሪጅ ሶሐቦች እንኳን የራሳቸውን ዒባዳ የሚንቁበት ፅናት ነበራቸው፡፡ ግና ሐቅ ላይ ነበሩ? ለማንም ስለማይሰወር ትቼዋለሁ፡፡
ለመሆኑ ኪታቡ ተውሒድን በስንት ሙጀለድ ሸርሕ አድርጎ ያፈነገጠ ሰው እንዳለ የምናውቅ ስንቶቻችን ነን?! አላሁል ሙስተዓን!!! አላህ ኻቲማችንን ያሳምረው፡፡ የዚህ ሰውየ እውቀት እኮ ከብዙ የሰፈር ኡስታዞች እጅግ የላቀ ነበር፡፡ ግና ተውሒድን ማወቁም፣ መረዳቱም፣ ማስተማሩም፣ ለምርጡ የተውሒድ ኪታብ ሸርሕ ማዘጋጀቱም ቅንጣት ሳይፈይደው መጨረሻው ማፈንገጥ ሆነ፡፡ ከዚህ ምን እንማራለን?! ከታሪክ ልንማር ይገባል፡፡ ከታሪክ ያልተማረ ሁሌ እንደዋለለ ይኖራል፡፡
ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከሳቸው በኋላ “ነብይ ነኝ” እያሉ የሚሞግቱ በርካታ ሀሰተኞች እንደሚነሱ ተናግረዋል፡፡ ግን ይስተዋል እነዚህ አታላዮች በአንድ ሌሊት ድንገት ተነስተው “ነብይ ነኝ፡፡ ተከተሉኝ” አይሉም፡፡ ይህን ቢያደርጉማ ማን ይሰማቸዋል? ይልቁንም ቀድመው ትሁት፣ አስተዋይ፣ አስተማሪ፣ አርቆ አሳቢ፣ ተቆርቋሪ ሆነው ይኖራሉ፡፡ ህዝባቸው ዘንድ የሚኖራቸውን ተሰሚነት በየጊዜው ይፈትሹና መብሰሉን ሲያዩ ያፈነዱታል፡፡ ቢድዐም ላይ ያሉ ሰዎች እንዲህ ናቸው፡፡ በዘመናችን አህሉስሱንና መስለው ሲያስተምሩ ኖረው ለብጥበጣ የማያንሱ ተከታዮችን እንዳፈሩ ሲያረጋግጡ ግን ጭንቅላታቸውን ከቀበሩበት አውጥተው መናደፍ የሚጀምሩ ብዙ ናቸው፡፡ የቢድዐቸው አይነት ፅንፍ መውጣት ወይም ፅንፍ ማርገብ ሊሆን ይችላል፡፡
አዎ ዘመኑ ተከረባባቾች የበዙበት ዘመን ነው፡፡ የማወራህ ስለኔ ብጤ አይደለም፡፡ ስንት “አዋቂዎች” የፊትና ነፋስ ሲያወዛውዛቸው እያየን ነው፡፡ ሰው የሚፈተነው እንዳቅሙ ነውና በኔ ብጤ በሰፈር ሰው የሚወዛወዘውም ቀላል አይደለም፡፡ ግን አንርሳ፡፡ ጌታችን እንዲህ ይላል፡- “ከፊላችሁን ለከፊላችሁ ፈተና አደረግን፡፡ ትታገሳላችሁን?” [አልፉርቃን፡ 20] የምትጠላው ሰው ከክህደት ወደ ኢስላም፣ ከቢድዐ ወደ ሱንናህ ሊመጣ ይችላል፡፡ ልክ እንዲሁ የምትወደውም ሰው ከኢስላም ወደ ኩፍር፣ ከሱንና ወደ ቢድዐ ሊዞር ይችላል፡፡ ከፊትናው ትምህርት ውሰድበት እንጂ ከማንም ጋር አትፍሰስ፣ በትንሽ በትልቁ አትልፈስፈስ፡፡ ለአላህ ብለህ የጠላሀው ሰው ሲያምን፣ ወደ ሱንና ሲዞር ልትወደው ግድ እንደሚልህ ሁሉ፤ የምትወደው ሰው የፈለገ ባለውለታህ እንኳን ቢሆን ሲከፍር ወይም ቢድዐን መንገዱ ሲያደርግ አለያም ደግሞ በሙስሊሙ መካከል ፊትናን ሲያቀጣጥል በጥፋቱ ልክ ልትጠላው ግድ ይልሃል፡፡ ያለበለዚያ ወጥ መርህ የሌለህ ወላዋይ የዲን ነጋዴ ነህ ማለት ነው፡፡ በዚያም ሙልል በዚህም ሙልል የሚል ውሃ በፌስታል ነገር፡፡ ታላቁ ሰለፍ ዛኢዳ ኢብኑ ቁዳማ ረሒመሁላህ ምን እንደሚሉ ተመልከት፡- “አንድን ሰው ለአላህ ብለህ ወደኸው፣ ከዚያም በኢስላም ውስጥ ቢድዐን ሲያመጣ ካልጠላሀው፣ ቀድሞ ለአላህ ስትል አልነበረም የወደድከው፡፡” [ሒልየቱል አውሊያእ፡ 7/37]
ይሄ ለአስተዋዮች ሁሉ ትልቅ ቁም ነገር አለው፡፡ ነፍስያ የምትጎተጉትህ፣ ውለታ የሚወተውትህ ከሆነ ቆም ብለህ አስተውል፡፡ ውለታም፣ ጥቅምም፣ ዝምድናም፣ ሌላም ነገር ቢስብህ ኡስታዝህ ካጠፋ አጥፍቷል፡፡ ስለዚህ ከሐቅ እንጂ ካጥፊ ኡታዝህ አትወግን፡፡ ሐቅ ከማንም በላይ ነውና፡፡ ሙሪድነት በሱፍያ እንጂ በሰለፊያ አለም የለም፡፡ ቦታም የለውም፡፡ ስንቶች ቀድሞ ጠላቶቻቸው በነበሩ ሰዎች ውዴታ ከንፈዋል፡፡ ስንቶች ያስተማሯቸውን ሸይኾች ለሐቅ ሲሉ አንቅረው ተፍተዋል፡፡ አንዳንዱ ግን ቀድሞ የሚጠላው ሰው ወደ ሱንና ቢመጣም ጥላቻው ከልቡ አይፋቅም፡፡ ሰበብ እየፈለገ ከማጠልሸትም አይመለስም፡፡ እጅግ የሚያስጠላው ግን በልቡ ያረገዘውን የጥላቻ መንፈስ ኢስላማዊ ቅብ ሲቀባው ነው፡፡ ሌላው ደግሞ ቀድሞ የሚወደው ሰው - ምናልባት አስተማሪውም ሊሆን ይችላል- የፈተና ሰበብ ሲሆንም አብሮ የሚከንፍ አለ፣ በፈሰሰበት የሚፈስ፡፡ ወንድም እህቶች እኛስ ከየትኞቹ ነን?
ኡስታዝህ ቢድዐውም ሺርኩም የማይጎረብጠው የላሸ የላሸቀ ሊሆን ይችላል፡፡ የራሱ መላሸት አልበቃ ብሎት አንተንም ልሽት፣ ልሽቅ ሊያደርግህ ይችላልና ተጠንቀቅ፡፡ ኡስታዝህ “ጭር ሲል አልወድም” ባህሪ የተፀናወተው በየሄደበት አቧራ የሚያስነሳ “ሙበጥቢጥ” ሊሆንም ይችላል፡፡ በቃ አመላችን እንደ መልካችን ብዙ አይነት ነው፡፡ በሙብተዲዑም በሱኒውም መደነቅ የሚሻ አግበስባሽ እንዳያስተኛህ እንደምትጠነቀቀው ሁሉ የሱንና ሰዎችን በመደዳ እያጨደ ታዋቂዎችን በመተቸት ታዋቂ መሆን የሚሻ አጉል ግብዝ በሱንና ስም፣ በሰለፊያ ስም ከማትወጣበት መቀመቅ እንዳይነክርህ ተጠንቀቅ፡፡ ምናልባት በዚያ ማዶ መንሸራተቱን እንደ ጥበብ የሚቆጥር ሰው ሊያጋጥምህ ይችላል፡፡ በሌላ ማዶ ደግሞ “እከሌ ሙብተዲዕ ነው! እሱን ሙብተዲዕ ያላለም ሙብተዲዕ ነው፣…” እያለ ሰንሰለታማ የተብዲዕ ዘመቻ የሚከፍት ሰነፍ “የሂሳብ አዋቂ” አለ፡፡
በምድር ላይ ብዙ አይነት ዋልጌዎች አሉ፡፡ ከዋልጌነትም የከፋው በዲን ስም፣ በሱንና ስም የሚፈፀም ዋልጌነት ነው፡፡ ግና ተጠንቀቅ!! የዋልጌዎች ዋልጌነት ዋልጌ አያድርግህ፡፡ ከቻልክ ምከር፡፡ ካልቻልክ ባንተና በዋልጌዎች መካከል የብረት አጥር ይኑር፡፡ ከዋልጌ ጋር እየተወራወርክ ወደ ሰፈራቸው አትውረድ፡፡
ፊትና ሲነሳ አቋም ከመያዝህ በፊት ቆም ብለህ ተመልከት፡፡ አንድን አካል “እቃወማለሁ” ብለህ ሌላ ፅንፍ እንዳትረግጥ፡፡ ካጥፊ “እሸሻለሁ” ብለህ የእውር ድንብር ስትሮጥ ሌላ መልክ ያለው የአጥፊዎች ወጥመድ ጠልፎ እንዳያስቀርህ ተጠንቀቅ፡፡ ከሺዐዎች ለመሸሽ ከናሲባዎች መጠጋት መፍተሄ አይሆንም፡፡ ከኸዋሪጅ የጥፋት ዶፍ ሸሽቶ ከሙርጂኣ ጣሪያ ስራ መጠለል ከድጡ ወደማጡ ነው፡፡ ከኢኽዋን “እሸሻለሁ” ብለህ ከሐዳዲያ የመንደር ውሪ ጋር የጥፋት ኩሬ ውስጥ እንዳትንቦጫረቅ፡፡ “ሐዳዲያ ኢትዮጵያ ውስጥ የለም” የሚል ካለ ወይ በማያውቀው የሚቀባጥር ሳይጠራ አቤት የሚል ጭልጥ ያለ መሀይም ነው፡፡ ወይ ደግሞ ሽወዳን እንደ እድሜ ማራዘሚያ የሚጠቀም ከራሱ በስልት የሚከላከል የነጋበት “ብልጣብልጥ” ነው፡፡ የነዚህኞቹ አፀፋ ገፋፍቶትህ ሌላ ፅንፍ በመያዝ በአንዳንድ ርእሰ-ጉዳዮች ላይ ያለምንም ተብዲዕ የተለየ ሀሳብ ስለያዘ ብቻ ማንንም በሐዳዲይነት ከመፈረጅም ተጠንቀቅ፡፡ ሐቁ ያለው ከመሀል ነው፡፡
ብቻ ካንዱ የቢድዐ አንጃ ወደሌላው ሲከረባበት የኖረ ፅንፍ የረገጠ ጥሬ ሁሉ እየተነሳ “ከኛ ጋር ያልሆነ ከጠላት ነው” የሚል ሰይፍ መዝዞ ሲያስፈራራህ አትንቦቅቦቅ፡፡ ማንም ምንም አያመጣም፡፡ የማንም ውዳሴ ወደ ሱንና እንደማይስገባህ ሁሉ የማንም ቀረርቶም ከሱንና አያስወጣህም፡፡ ኢስላም ክርስትና አይደለም፡፡ ማንም “ውግዝ ከማሪዎስ” ብሎ አያስወጣህም፡፡ ስለሆነም የማንም ፍረጃ አያስፈራህ፡፡ የማንም ሙገሳም አይሸውድህ፡፡ ደግሞ ተጠንቀቅ፡፡ ለፈታኞች አጋዥ አትሁን፡፡ ከቻልክ በግልፅ መልስ፡፡ ካልሆነ በግልፅ ራቅ፡፡ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ በየትኛውም መልኩ አጥፊዎችን በሚያስተዋውቅ ስራ ላይ አትሰማራ፡፡ ሌላው ቀርቶ በፌስቡክ ጓደኝነት እንኳን ለአጥፊዎች አጋር እንዳትሆን ተጠንቀቅ፡፡ የጭቅጭቅ በር እየከፈትክ ፔጃቸውን አታስተዋውቅ፡፡ እያንዳንዷ ኮሜንትህ ለተቃውሞ እንኳን ቢሆን የአጥፊዎችን የጥፋት ገፅ የማስተዋወቅ ሚና እንዳላት አስተውል፡፡ ለእያንዳንዱ ጩኸታቸው መልስ አትስጥ፡፡ ዝንብ “ጢንንንን” ባለ ቁጥር እጅህን እያነሳህ ክብር አትስጥ፡፡ ከነጭራሹ ዝም በል ማለቴ አይደለም፡፡ ሲያስፈልግ ካልተንቀሳቀስክ የዝንብ ቀፎ ትሆናለህ፡፡
ሸይኽ ፈውዛን በክፉ አንጠረጥራቸውም፡፡ ግና ለማንም እንደማይሰወረው የሳቸውም መጨረሻ አይታወቅም፡፡ ቀጥተኛ በሆነ መልኩ ለመናገር ያክል፣ አይደለም በሱንና ስም የሚነግድ የመንደር ኡስታዝ ይቅርና ፈውዛን ቢንሸራተቱ ልንንሸራተት አይገባም፡፡ ነገሩን ይበልጥ ለማጉላት የተጠቀምኩት ምሳሌ ነው፡፡ መንሸራተት ማለት መርገብ ፣ መላላት፣ መዋለል ብቻ አይደለም፡፡ ጠርዘኝነትም ከሱንና መንሸራተት ነው፡፡ ጠባብነትም መንሸራተት ነው፡፡ በሱንና ስም ሰዎችን ከሱንና ማስወጣትም መንሸራተት ነው፡፡ የነገር ሁሉ ቀንጮው ኢስላም ነው፣ ሱንና ነው፡፡ ከዚያ በመለስ ያለ ሁሉ በየትኛውም አቅጣጫ ይውረድ፣ ወጠረም ረገበ ተንሸራቷል፡፡ የሙርጂአዎች ለጥፋት ቁንጮዎች ሁሉ በሙሉ ኢማን መመስከር መንሸራተት እንደሆነው ሁሉ የኸዋሪጆች በኢስላም ስም ሰዎችን ከኢስላም ማስወጣትም መንሸራተት ነው፡፡ የኢኽዋኖች በኢስላም ስም እየነገዱ ሁሉን ማግበስበስ መንሸራተት እንደሆነው ሁሉ የተኻለፋቸውን ሁሉ “ኢኽዋን” እያሉ የሚያስፈራሩ በጥባጮች አካሄድም ያለጥርጥር መንሸራተት ነው፡፡ ስለሆነም ኢኽዋኑ የተለያዩ ቅፅሎች ሲለጥፍልህ ያልደነገጥከውን ሌላው ትላንት እራሱ በነበረበት ማንነቱ “ኢኽዋኒ” እያለ ከኋላ በኩል በነገር ጩቤ ቢወጋህ አትደናገጥ፡፡ ይህ የአላህ ሱንና ነው፡፡ መቼም ቢሆን ከተቺዎች አትተርፍም፡፡ በርግጠኝነት መሀል ላይ ስትቆም ማዶና ማዶ ባሉት አንጃዎች በሌላኛው ማዶ ትፈረጃለህ፡፡ ሰለፊያ ቁርኣንና ሱንናን በቀደምቶች ግንዛቤ መረዳት እንጂ የነ እንቶኔ ጎጠኛ ስብስብ አይደለም፡፡
ትላንት ሰለፎቻችን፣ ዛሬም ታላላቅ ዑለማዎቻችን አንዳቸው በቢድዐ የፈረጁትን አካል ሌላቸው ሲከላከሉለት ያጋጥማል፡፡ ግና “እንዴት እኔን ተከትለህ አልፈረጅክም” ብለው አንዳቸው በሌላው ላይ አልዘመቱም፡፡ ለዚህ አንድ ሁለት አይደለም፣ አስር ሃያ አይደለም እጅግ በርካታ ምሳሌዎችን መዘርዘር ይቻላል፡፡ ለናሙና ያክል ታላላቅ የሱንና ተራራ የሆኑት እነ አቡ ዙርዐ፣ እነ ዙህሊ ታላቁን የሐዲሥ ሊቅ ኢማሙ ቡኻሪን በቢድዐ ወንጅለዋቸዋል፡፡ በአንፃሩ እነ ኢማሙ ሙስሊም ግን ለቡኻሪ ተከላክለውላቸዋል፡፡ ሆኖም ግን አንዳቸው በሌላው ላይ በመዝመት በዚህ ሳቢያ ጎራ ለይተው አልተናቆሩም፡፡ የቅርብ ታሪክ ብንመለከት ሸይኽ ሙቅቢል በሸይኽ ሙሐመድ ረሺድ ሪዳ ላይ በታዩ ከባባድ ጥፋቶች ሳቢያ በጥመት ገልጸዋቸዋል፡፡ በሌላ በኩል አልኢማም አልባኒ ረሒመሁላህ ይህንን የሙቅቢልን አቋም ተችተዋል፡፡ ይህም ከመሆኑ ጋር ግን ዛሬ በአንዳንድ ቂላቂሎች እንደሚታየው “ከሙብተዲዕ የተከላከለ ሙብተዲዕ ነው” በሚል ስሌት ሙቅቢል አልባኒን ከሱንና አላስወጡም፡፡ ሊዳፈሩም አይቻላቸውም፡፡ እርግጥ ነው ከሙብተዲዕ የሚከላከለው ሙብተዲዕ ነው፡፡ ግና “ሙብተዲዕ” የሚባለው ሰው ላይ የሚሰጠው ብይን አነታራኪ ሊሆን ይችላል፡፡ ወይም ለሱ የሚከላከለው አካል መዕዙር ሊሆን ይችላል፡፡ ይህን ስሌት የሚሰራው ደግሞ የመንደር ጎረምሳ ሳይሆን አርቆ አስተዋይ የሆነ ዐሊም ነው፡፡
ወላሂ ድሮ ለዐሊሞች ጭፍን ተከታይ እንዳይኮን ነበር የሚመከረው፡፡ ዛሬ ግን በዲን ስም ትንሽ ላንጎራጎረ ሁሉ ጭፍን ተሟጋች የሚሆነው በሽ ነው፡፡ ይሄ ሲበዛ ግብስብስነታችንን የሚያጋልጥ ነውር ነው፡፡ ብቻ ሳጠቃልል ደግሜ ደጋግሜ የምለው ማንም ይሁን ምን ሰው ላይ ጥገኛ አንሁን ነው፡፡ ያለበለዚያ የሚከተለን አስፈሪ አደጋ ነው፡፡
ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዳሉት “የአደም ልጅ ልቦች ልክ እንደ አንድ ልብ ሁሉም በአርረሕማን ጣቶች መካከል ነው ያሉት፡፡ እንዳሻው ይገለባብጠዋል፡፡” [ሙስሊም] ለዋዛ እንዳይመስልህ አብዛሀኛው የነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ዱዓእ “አንተ ልቦችን ገለባባጭ የሆንከው ጌታዬ ሆይ! ልቤን በዲንህ ላይ አፅናልኝ” መሆኑ፡፡ ምክንያቱን ሲጠየቁ ደግሞ “ልቡ ከአላህ ጣቶች በሁለቱ ጣቶቹ መካከል ያልሆነ ሰው የለም፡፡ የፈለገውን ያቃናዋል፤ የፈለገውን ያጠመዋል” አሉ፡፡ [አስሶሒሐህ፡ 2091] እኛም ይህን ዱዓእ እናብዛ፡፡ እንጠቀምበትም፡፡ ይህን ነብያዊ ዱዓም አንዘንጋው፡- “አንተ የጀብራኢል፣ የሚካኢል፣ የኢስራፊል ጌታ የሆንከው ጌታዬ ሆይ! የሰማያትና የምድር ፈጣሪ የሆንከው፣ የሩቁንም የቅርቡንም የምታውቀው ሲወዛገቡበት በነበረው ነገር አንተ ታውቃለህ፡፡ ከሐቅ ለሚወዛገቡበት ነገር ምራኝ፡፡ አንተ የፈለግከውን ወደ ቀጥተኛው መንገድ ትመራለህና፡፡” [ሙስሊም]
አሚን
(ኢብኑ ሙነወር፣ ሰኔ 10/2008)