Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ፆም ክፍል ሶስት (3) የረመዳን ፆም ወር ግዴታ መግባቱ የሚታወቅባቸው ሶስት መንገዶች

📙ፆም📙
📩 ክፍል ሶስት (3)
🍃 ሼኽ ሳሊሕ አልፈውዛን እንዲህ ይላሉ:~
🌴 የረመዳን ፆም ወር ግዴታ መግባቱ የሚታወቅባቸው ሶስት መንገዶች~
🔵1ኛ· ጨረቃን በማየት
👉አላህ ሱብሐነሁ ወተዓላ እንዲህ ይላል:–
"…ከእናንተም ወሩን ያገኘ ሰው ይጹመው፡፡…"
👉ነቢዩም ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም
"ጨረቃን አይታችሁ ጹሙ…" ብለዋል።
አንድ ሰው ጨረቃን ካየ መጾም ግዴታ ይሆንበታል።
🔵 2ኛ· ጨረቃን ያየ ሰው በመመስከር ወይም ማየቱን በመናገር፣ ይህ ሰው ፍትሀኛና ለአቅመ–አዳም/ ሄዋን የደረሰ በመሆኑ ማየቱ ብቻ ለመጾም በቂ ማስረጃ ነው። ምክንያቱም ኢብኑ ዑመር ሰዎች ጨረቃን ማየታቸው እርስበርሳቸው ተናገሩ እና አኔም ለነቢዩ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ማየቴን ነገርኳቸው እሳቸውም ጾሙ እና ሰዎችንም እንዲጾሙ አዘዙ ይላል።
📙አቡዳውድ እና ሌሎች ዘግበውታል ኢብኑ ሒባንና አልሐኪም ዘገባው ትክክል ነው ብለዋል።
🔵3ኛ· የሻዕባንን ወር ሰላሳ ቀን መሙላት ያም የሚሆነው ሰላሳኛው ሌሊት (29ኛ ቀኑን ውሎ 30 ሊሆን የተቃረበ) ላይ በዳመና፣ ጨለማ እና ሌሎች ነገሮች እዳይታይ ምክንያት ከሆነ ማለት ነው።
ምክንያቱም ነቢዩ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም
"ወር ሲባል 29 ነው ጨረቃን ሳታዩ እንዳትጾሙ ፤ ስታፈጥሩም ጨረቃን ሳታዩ አታፍጥሩ ጨረቃ ከተጋረደባችሁ ገምቱለት" ብለዋል። ገምቱለት ማለት የሻዕባንን ወር 30 ሙሉት ማለት ነው። በአቡሁረይራ ሐዲስ ላይ እንደተገለጸው:– ከተጋረደባችሁ ሻዕባንን 30 ሙሉት…
📙ምንጭ:–
አልሙለኸስ አልፊቅህ (191)