Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ፆም ክፍል አራት (4)

📙ፆም📙
📩 ክፍል አራት (4)
🌴 የረመዳን ፆም ግዴታ ስለመሆኑና ጊዜው
🍃 ሼኽ ሳሊሕ አልፈውዛን እንዲህ ይላሉ:~
የረመዳን ወር ጾም ግዴታ የሚሆነው:–
1· ሙስሊም በሆነ ሰው ላይ፣
2· ለአቅመ አዳም/ ሄዋን የደረሰ/ች
3· አቅም/ችሎታ ያለው/ት
በከሀዲ ላይ ግዴታ አይሆንም ቢጾምም ተቀባይነት አይኖረውም።
በጾም ጊዜ ቢሰልም ቀሪውን ሰዓት ይጾማል።
ከሐዲ በነበረበት ጊዜ ያለፈውን ጾም እንዲጾም ግዴታ አይሆንበትም።
🔵 በህጻን ልጅ ላይም መጾም ግዴታ አይሆንበትም።
እንዲሁም በእብድ ሰው ላይ ግዴታ አይሆንበትም ምክንያቱም ቁርጠኛ የሆነ ዉሳኔ ( ኒያ) ስለሌለው~
በሽተኛ/ህመም ያለበት እና መንገደኛ በሆኑ ሰዎች ላይ መጾም ግዴታ የለባቸውም። ነገርግን በሽተኛው ከበሽታው ሲድን እና መንገደኛው ወደ አገሩ ሲመለስ ያለፋባቸውን ጾም መተካት (ቀዷእ ማውጣት) ይኖርባቸዋል።
አላህ ሱብሐነሁ ወተዓላ እንዲህ ይላል:–
"…ከእናንተም ውሰጥ በሽተኛ ወይም በጉዞ ላይ የኾነ ሰው ከሌሎች ቀኖች ቁጥሮችን መጾም አለበት፡፡…"
👉 ጾም ግዴታ የሚሆንባቸው:–
1· መንገደኛ በሆነ እና መንገደኛ ባልሆኑ
2· ጤነኛ እና በሽተኛ
3· ንጹሀን፣ በወር አበባ እና በወሊድ ደም ላይ ያሉ
4· ራሱን በሳተ ሰው ላይ
👆ከላይ በተጠቀሱ ሰዎች ላይ መጾም ግዴታ የተደረገ መሆኑን ማመን እና ሁኔታዎች ሲመቻቹ መተግበር ይኖርባቸዋል።
🔵የአጿጿሙም ሁኔታ:–
👉 ወዲያው በጊዜው በመጾም (አዳአን) ወይም
👉 በሌላ ጊዜ በመተካት (ቀዷእ በማውጣት) ሊጾሙ ይችላሉ።
ከእዚህም መካከል:–
👉 ወዲያው በጊዜው መጾም (አዳአን) እንዳለባቸው የሚታዘዙ አሉ ።እነሱም:–
1· ጤነኛ እና
2· መንገደኛ/ ጉዞ ላይ ያልሆነ
👉 በሌላ ጊዜ በመተካት (ቀዷእ ማውጣት) ብቻ ያለባቸው:–
1· በወር አበባ ላይ ያለች ሴት
2· በወሊድ ደም ላይ ያለች
3· በሽተኛ ሆኖ መጾም የማይችል ነገርግን ሲድን መተካት የሚችል
👉 ከሁለቱ አንዱ ምርጫ የሚሰጠው:–
መንገደኛ እና በሽተኛ ሆነው እየከበዳቸው ሊጾሙ የሚችሉ ከሆኑ –እራሳቸውን ጉዳት ላይ በማይጥል ሁኔታ– ምርጫ አላቸው።
🔵 አንድ ሰው በምክንያት (ዑዝር) ያፈጠረና ከዛ በኋላ አ ንዳይጾም ያገደው ምክንያት በጾም መሐል ( ቀን ክፍለ–ጊዜ ላይ) ቢነሳ ወይም ቢወገድ:–
ለምሳሌ:–
1· መንገደኛ በቀን ክፍለ ጊዜ ቢመለስ
2· በወር አበባ ወይም በወሊድ ደም ላይ ያሉ ቢጠሩ
3· ከሀዲ የሆነ ሰው ቢሰልም
4· እብድ ጤነኛ ቢሆን
5· ህጻን ለአቅመ አዳም ቢደርስ
👆እነዚህ ሁሉ በቀረው ቀን ላይ ከመብላት ይታቀቡና በሌላ ቀን መተካት ይጠበቅባቸዋል።
👉እንዲሁም የረመዳን ወር መግባቱ ቀን ላይ ከታወቀ በኋላ ሙስሊሞች በቀሪው ሰዓት መታቀብ እና ረመዳን ከወጣ በኋላ ያንን ያፈጠሩበትን ቀን መተካት (ቀዷእ ማውጣት) ይኖርባቸዋል።
📙ምንጭ:–
አልሙለኸስ አልፊቅህ (192–193)
👆ትርጉም:–
አቡሐምዛ ጀማል ያሲን
ሻዕባን 19/1436ሂ