Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ይህን ያውቁ ኖሯል? ከሃገራችን ዑለማዎች ውስጥ የመስጂድ አንነበዊ ኢማም

ይህን ያውቁ ኖሯል?
ከሃገራችን ዑለማዎች ውስጥ የመስጂድ አንነበዊ ኢማም፣ የሳዑዲ ታላላቅ ዑለማዎች ምክር ቤት አባል የነበረ ዓሊም ያውቃሉ?!
ሸይኽ ዐብዱል መጂድ ሐሰን አልጀበርቲ ይባላሉ፡፡ የጂማ ተወላጅ ናቸው፡፡ በ 1332 በሐበሻ ተወለዱ፡፡ (አቆጣጠሩ በሙሉ በሂጅራ እንደሆነ ከግምት ይግባ፡፡) በ 1345 ወደ መካ ተጓዙ፡፡ ከበርካታ ታላላቅ ዑለማዎች ላይ በመካና በመዲና ኢስላማዊ እውቀትን ገበዩ፡፡ የተለያዩ ትምህርት ቤቶች ላይ ሰርተዋል፡፡ ርእሰ መምህር ሆነው የሰሩበትም ጊዜ ነበር፡፡ ከብዙ የደረጃ እድገቶች በኋላ የመስጂደ አንነበዊ ረዳት ኢማም እና ኸጢብ ሆነው በ1372 ተመደቡ፡፡ … ከዚያም የከፍተኛ ፍርድ ቤት መማክርት አባል ሆኑ፡፡ ከዚያም የታላላቅ ዑለማዎች ምክር ቤት አባል ሆኑ፡፡ በዚህም ላይ እስከ 1412 ድረስ ዘለቁ፡፡ ከዚያም የመስጂድ አንነበዊ ኢማም ሆነው ዳግም ወደ መዲና ተመለሱ፡፡
በመጨረሻም በ 17/10/1418 ከዚች አለም በሞት ተለዩ፡፡ ረሒመሁላህ፡፡