Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ነሺዳን ማዘጋጀት ለምን አስፈለገ ??


ነሺዳን ማዘጋጀት ለምን አስፈለገ ??
በአቡ ቢላል
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው።
በመጀመሪያ የዘመናችን ታላቁ አሊም ሸይህ ሳሊህ አል ፈውዛን ሀፊዘሁላህ ስለነሺዳ ተጠይቀው ሲመልሱ ።
"ይህ ጉዳይ የሱፍዮች መገለጫ ነው" በማለት ነበር የመለሱት ።
.
ታዲያ ይህ የሱፍዮች መገላጫ የሆነው ነሺዳ የሚዘጋጀው ምንን ታሳቢ በማድረግ ነው ።
1. "ሰዎችን ለመምከር ?" ይህ ፈፅሞ የነሺዳ አላማ ሊሆን አይችልም ።ከአላህ በላይ ንግግሩ ያማረ የለምና የአላህ ቃል ያልመከረው ነሺዳ ፈፅሞ ሊመክረው አይችልም ።
ሀያሉ ጌታችን እንዲህ ይላል።
"(ይህ) ወደ አንተ የተወረደ መፅሀፍ ነው። በደረትህም ውስጥ ከእርሱ ጭንቀት አይኑር።(የተወረደውም) በእርሱ ልታስፈራራበትና ለምእመናን መገሰጫ እንዲሆን ነው ።"
ሙእሚን ለመመከር ለመገሰፅ የጌታው ቃል ይበቃዋልና ።
ከአላህ በላይ መካሪ ገሳጭስ ከቶ ከየት ይመጣል።
.
2.."ቀልብን ለማረጋጋት" ብዙዎች ነሺዳ ቀልባቸውን እንደሚያረጋጋላቸው ያወራሉ ።በነሺዳም ተመስጠው ሲሄዱም ይስተዋላሉ ።በርግጥ ልቦች በነሺዳ ይረጋጋሉን ።
"አላህን በማስታወስ ልቦች ይረጋጋሉ ። "
.
ታዲያ ነሺዳ ከአላህ ቃል ይልቅ የተሻለች ሆና ነው ልብን የምታረጋጋው ፤የምታስመስጠን ??
አላህን በማስታወስ መረጋጋትን ያጣችስ ልብ ከቶ በምን ልትረጋጋ ።
.
3.."ዘፈን ከመስማት ነሺዳ እንሰማለን"
እስኪ ለዚህችኛዋ ምክንያት መረጃዋ ምንድነው ? ዘፈን ከምትሰሙ ነሺዳ ስሙ ያለውስ ማነው ?
እኛ ነን እንዴ ለራሳችን የሚመቸንን የምንወስነው ? ይህ አጉል ፍቅረኛሞች ነን ከሚሉ ሰዎች የሚቀርበው አይነት ግራ የገባው ምክንያት ነው ። ምን ይላሉ በእስልምና ቦይ ፍሬንድ ገርል ፍሬንድ ሚባል የለም ከወደድካት ኒካህ አስረህ አግባት ሲባሉ ከካፊር ጋር ከምትጨማለቅ ብዬ ነው ይላል ።
አሁንም ዘፈን ላለመስማት ነው ይላል ። ዘፈንን በነሺዳ መለወጥ ሽንትን በሽንት እንደማጠብ ነው ያሉት ማን ነበሩ ? ሸይህ ፈውዛን መሰሉኝ ካልተሳሳትኩ ።
ታዲያ ጉዳዩ እንዲህ ከሆነ ነሺዳ መስራት ለምን አስፈለገ ከተባለ ከሁለት አንዱ ምክንያት ሊሆን ነው ማለት ነው ።እነሱም ፦
1.ሰውም ከኢባዳ ለማዘናጋት ።
.
2.ገንዘብን ለመሰብሰብ ።
እነዚህን ምክንያቶች ይበልጥ አሳማኝ የሚያደርገው የሚከተሉት ጉዳዮች ናቸው ።
1.ሰውን ከኢባዳ ለማዘናጋት ። ይህንን ምክንያት እውነተኝነት ከሚያሳዩን ነገሮች ውስጥ ዋነኛው የነዚህ ነሺዳዎች የሚጎርፉበት ጌዜ ነው ፤ይህም ጊዜ ታላቁ ወር ረመዳን ነው ።አዎ ነሺዳዎች ሁላ ግር ብለው የሚመጡት ረመዳንን ጠብቀው ነው ።የቁርአን ወር ፤የኢባዳ ወር የሆነውን ረመዳን ጠብቆ ነሺዳ ማጉረፍ መቼም ከኢባዳ ለማዘናጋት እንጂ በኢባዳ ለማበርታት አይደለም ።
የነሺዳዎች ባህርይ ሰውን ተመስጦ ውስጥ መክተት እንጂ ማነቃቃት አይደለምና ።
2.ገንዘብ ለመሰብሰብ ። ይህንንም ምክንያት ይበልጥ የሚያጎላው ነሺዳ ምረቃ እየተባለ ቲያትር ቤት ከሚጠራው ሰው የሚሰበሰበው ገንዘብና አሁንም ረመዳንን ጠብቀው መጉረፋቸው ።ሙስሊሙ በአላህ ፀጋ ዘፈን ምናምን የሚባሉትን ትቶ ወደዲኑ በሚመጣበት የረመዳን ወር ነሺዳ መቸብቸብ የሚያዋጣ ገቢያ መሆኑን እነሱም ስለሚያቁት ረመዳንን ጠብቆ መቸብቸብን ይመርጣሉ። በሌላ ጊዜ የሚወጣ ነሺዳ እንብዛም ገቢ እንደሌለው ጠንቅቀው ስለሚያውቋት አይሞክሯትም ።
.
የአላህ ባሮች ሆይ ዲናችን ሙሉ ነው ምንንም ጭማሪ አይፈልግም ።ይህ የሱፍዮች መንገድ የሆነው ነሺዳም ልባችንን ቢያደርቀው እንጂ አያረጥብልንም ።ልባችን የሚረጋጋው አላህን በማስታወስ ብቻ ነው ።
የአላህ ባሮች ኸይረኛው ወር ረመዳን ወደ�ኛ እየቀረበ ነው ።ይህንን ወር አላህ ብሎ ከደረስን ከሚያዘናጉን ነገሮች ሁላ ተጠንቅቀን ከቁርአን ጋር ያለንን ቁርኝት ይበልጥ አጠንክረን በኢባዳም ጠንክረን ኸይር ስራን መሸመት ይኖርብናል ።
አላህ ሆይ ረመዳንን በሰላም ከሚደርሱት አርገን ፤ደርሰውም ከሚጠቀሙበት አድርገን።