የሰው አይን (ቡዳ) የበላው ሰው እንዴት ይፈወሳል?
የሰው አይን (ቡዳ) ያለና የሚያጋጥም ነው። የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፤
(الْعَيْنُ حَقٌّ) «በአይን (መጎዳት) ያለ እውነታ ነው»
(ቡኻሪና (5740) ሙስሊም (2187)ዘግበውታል)
ይህ ሰው የሚታወቅ ከሆነና ፍቃደኛ ከሆነ ውዱእ እንዲያደርግ ወይም ገላውን እንዲታጠብ ተደርጎ ውሀውን ለፈውስ መጠቀም ይቻላል። ማንኛውም ሰው እይታው የጎዳውን ሰው ካወቀ ወይም ከጠረጠረ ውዱእ እንዲያደርግለት የመጠየቅ መብት አለው።
ሸይኽ ኡሰይሚን አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ ብለዋል፤
«የሰው አይን ለጉዳት የዳረገው ሰው ሊወስድ የሚገባውን እርምጃ ምንድነው? ቁርአን በመቅራት ይታከማል፤ በእይታው የጎዳው ሰው ከታወቀ ውዱእ እንዲያደርግ ይጠየቅና ውዱእ ሲያደርግ የተንጠባጠበውን ውሀ ለበሽተኛው ይሰጣል። ጀርባውና ራሱ ላይ ይደፋበታል። እንዲጠጣም ይደረጋል። በአላህ ፍቃድ በዚህ ይፈወሳል።
ለኪታቡ ተውሂድ በሰጡት ማብራሪያ ላይም እንዲህ ብለዋል፤
«ሌላም መንገድ አለ እሱንም ከመጠቀም ምንም የሚከለክል ነገር የለም። እሱም፤ እንደ ኮፍያ ከነቴራና የውስጥ ሱሪ ያሉ ከሰውነት ጋር የሚነካኩ የውስጥ ልብሶችን ወይም በባዶ እግሩ የሄደበትን ንፁህ አፈር ተወስዶ ዉሀ ይነከርና በዛ ውሀ የታመመው ሰው ላይ ይረጫል ወይም ይጠጣዋል፤ ይህም የተሞከረ ነው።»
መጅሙእ ሙአለፋት ኢብኑ ኡሰይሚን 9/88
ይህ የመጨረሻው መፍትሄ ይበልጥ ጠቃሚ የሚሆነው ይህ ሰው ውዱእ ለማድረግ ወይም ለመታጠብ ዝግጁ ካልሆነ ወይም ካፊር ከሆነ ወይም ደግሞ ከዚህ ሰው ጋር ያለንን ግንኙነት የሚያበላሽ መስሎ ከተሰማን ሰውየው በማያውቅበት መልኩ መፈፀም ስለሚችል ጥሩ አማራጭ ነው።
#ሺፋእ
ቁርዓናዊ ፈውስ ለጂን እና ሲህር !
ፔጁን ላይክ ለማድረግ፡-
https://www.facebook.com/
ሼር በማድረግ ሙስሊሙን ዑማ በብዛት እየጎዳ ያለውን የሲህር በሽታ ለመከላከል የበኩሎን አስተዋፅዖ ያበርክቱ