ለወድ እህቴ!
By.. Haider Khedir
ዛሬ ተመሳሳይ ይዘት ያላቸው አንዳንድ እህቶች የፃፉትን ፅሁፍ ተመለከትኩ!
በዲን ስም የተግባባናቸው ወንድሞች እንዲህ አደረጉን ፤ እንዲህ በደሉን የመሳሰሉት…
ይህን ነገር በተደጋጋሚ ሰማነው ይሁንና እንደ ፈንጂ አምካኝ ከስህተታችን መማር አልቻልንም!
ተደጋጋሚ "ጥቃቶች" እንደቀጠሉ ነው!
አሁንም ለሰሚ ጆሮዎች ይህንን ራሴንም የምገስፅበት እናንተንም የማስታውስበት ወንድማዊ ማስታወሻ እንካችሁ ብያለሁ
የራሳችንን ክብር ማስጠበቅ ምንችለው ራሳችን ነን! በተለይ በአሁን ጊዜ! ራስን ሰብሰብ ማድረግ የመሰለ የለም ፡፡
ብዙ ጊዜ የሚታየው ችግር በተለያዩ ሶሽል ኔት ወርክ ፖስት ያደረገ ሁሉ "ዓሊም" መስሎሽ ያራሀማን ይህን ሳሊህ ለኔ … እያልሽ አላህን የምትለምኚ ፤ አንተም (እኔንም ጨምሮ) እንዲሁ እህታችንም ፖስቶቿን ተመልክተህ እቺንማ ያ ረዛቅ … ብለህ ምትቋምጠው ስለተቅዋ ፣ ስለ ሱናህ ስለ ሚስት ሀቅ ስለፃፈ ተቅይ የሚመስልሽ ፣ ስለ ባል ሀቅ ስለ ሂጃብ ስለ ሀያእ የፖሰተች … ከመሰለህ አንቺም ከመሰለሽ ሁላችንም ከመሰለን ተበልተሻል ፣ ተበልተሃል ፣ ተበልተናል!
ከኑግ የተገኘህ ሰሊጥ አብረህ ተወቀጥ ማለቴ አይደል ሁሌም የአላህ መልካም ባሮች ተግባራቸው ንግግራቸውን የቀደመ አሉ ጥቂት ቢሆኑም!
ዋና ሀሳቤ እህቴን ማስታወስ ነውና!ወደ ርዕሴ ተመለስኩ
አትሸወጂ! ለዲን ባለሽ ፍቅር ብቻ ተነሳስተሸ ሳሊህ የመሰለሽን ሁላ ለመተዋወቅ ላይ እታች አትበይ! ራስሽን ሰትሪ! በተቻለሽ አቅም ከወንዶች ጋር ያለሽን ግንኙነት ቀንሽ! ትኩረትሽን ዒልም ላይ አድርጊ ‹እውቀት ከተግባርም ሆነ ከንግግር ይቀድማል› ይሰራበት!
ዲን እንዴት ነው? ፣ ቂርዓትስ?፣ ዳዕዋ ስራውን እንዴት አየሽው? ፣ ፖስቶቼ እንዴት ናቸው? ፣ ፖስትሽ በጣም ጠቃሚ ነው፣ እንዴት ነው የእነ ፉላን እና አላን ነገር? ፣ በሚል የመግቢያ ትኬት ቆርጦ ከገባ በኃላ የሚፈልገውን የባጥ የቆጡን ከሚያዘረግፍ ዲንሽን ሀያሻን ከሚገፍ በዲን ስም ከሚያሳስትሽ መጨረሻም ቀይ ካርድ ከሚያሳይ ወንድ ራስሽን ጠብቂ!
የማግባት ጉጉትሽን ብደግፍም ፣ ያላገባ ጀነት አይገባም አልተባለም! በየጊዜው አገባሻለሁ ብሎ ጉድ ሰራኝ ፣ እንዲህ አደረገኝ እያልሽ በየፌስ ቡክ ፖስት ከማድረግ በአላህ ላይ ሙሉ እምነት ኖሮሽ ከእንደዚህ አይነት ግንኙነቶች ራስሽን መቆጠብ ይሻላል ባይ ነኝ! ምክንያቱም በእንደዚህ አይነት ግንኙነት ካሰቡት የደረሱ ጥቂቶች ናቸው (መሰለኝ) !
አንተም ወንድሜ!
ከሴት አልተፈጠርክም ! እናት ፣ እህት ፣ በዘራችሁ ሴት የለም እንዴ???
ምን አይነት ጨካኝነት ነው ፣ ሳትፈልግ ፍለጋ አትውጣ (ቃሉ ካልገባህ ልተርጉመው) ለትዳር ሳትዘጋጅ ሚስት ፍለጋ አትውጣ ነው ያልኩት!
እህቴ ጉዳትሽን ሳልረዳ ቀርቼ አይደለም! አላህ ፅናቱን እና ሰብሩን ይስጥሽ!
ግን አንቺም ላይ የማየው ጥፋት አለ መቼም ቅር አይልሽም ስለነገርኩሽ!
አንቺም ለወንድ "አየር" አትስጪ ልክ ፖስት ላይ ሀይለኛ እንደሆንሽው ሜሴጅ ላይም ሀይለኛ ሁኚ! በእርግጥ አሁን ፖስት ላም ሀያእ ጠፍቷል ይህን ሀቂቃ አንድ ቀን ፖስት ማድረግ አቁመሽ ሌሎችን ብትመለከቺ የምታረጋግጪው ነው፡፡
አንተም ወንድሜ (እኔንም ጨምሮ) ፖስት ላይ ነብር ሜሴጅ ላይ በግ አትሁን!
አላህ ለሚወደው ሁሉ ይግጠመን! ከመልካሞቹ ያድርገን!
ሀይደር ኸድር ግንቦት 8/2008!