የኑሕ (ዐለይሂ ሰላም) አራት ልጆች
ሸይኽ ሷሊሕ አሉ ሸይኽ (ሐፊዘሁላህ) እንዲህ አሉ:-
1) ሳም (በዐረብኛው سآمٓ ፣ በግዕዝኛ ሴም) ተብሎ የሚታወቀው የኑሕ ወንድ ልጅ የዐረቦች፣ የሮማኖች (ባዛንታይን) እና የፋርሳውያን (ፐርሺያ) አባት ነው። ከዚህም በመነሳት እነዚህ አራቱም የሳማውያን (የሴም) ህዝቦች በመባል ይጠራሉ። ቋንቋቸውም ደግሞ የሳማውያን (የሴም) ቋንቋ ተብሎ ይታወቃል። በሰሜን አፍሪቃ እና በእሲያ አብዛኛው ክፍል ኖረዋል።
2) ሓም (በዐረብኛው حآمٌ ፣ በግዕዝኛ ካም) ተብሎ የሚጠራው የኑሕ ልጅ ደግሞ የሱዳን አባት ማለትም በአፍሪቃ እና በሌሎች ቦታዎች ያሉ የጥቁር ዘሮች አባት ነው።
3) ያፊሥ (በዐረብኛው يآفِثُ ፣ በግዕዝኛ ያፌት) ተብሎ የሚጠራው የኑሕ ልጅ የቱርኮች፣ የስላቫውያን፣ እና ቻይናውያን አባት ነው። (እዚህ ጋር) ቱርካውያን ሲባል ሩሲያውያንን እንጂ (ዛሬ ያለችዋን) ቱርኪያህ አይደለም። ምንም እንኳን "ቱርካውያን" እያሉ ቢጠሩም። ምክንያቱም የኦቶማዊያን መሰረት ከሩሲያ ነው።
------ የሸኹ ንግግር እዚህ ጋር ተቋጨ ------
4) ታላቁ ዐሊም ኢማም ኢብኑ ከሢር (ረሒመሁላህ) ተከታዩን የቁርኣን አንቀፅ ሲያብራሩ :-
(( እርሷም እንደ ተራራዎች በሆነ ማዕበል ውስጥ በእነርሱ (ይዛቸው) የምትንሻለል ስትሆን (በአላህ ስም ተቀመጡባት) ፡፡ ኑሕም ልጁን ከመርከቢቱ የራቀ ሆኖ ሳለ «ልጄ ሆይ! ከኛ ጋር ተሳፈር ከከሓዲዎቹም አትሁን» ሲል ጠራው፡፡))
[ሱረቱል ሁድ 42]
" ((ኑሕ ልጁን ጠራው)) ይህ የኑሕ አራተኛ ልጁ ነበር። መጠሪያውም ከነዓን ወይንም ያም (በዐረብኛው كنعان يقال له أيضا َيام) ነበር። ከሓዲ ነበር። አባቱ ኑሕ ልጁ እንዲያምን እና ከነርሱም ጋር በመርከቡ ላይ እንዲሳፈር ከከሓዲያን ጋር እንዳይሰጥም ጠራው። (ልጅ ግን "እምቢ" አለ።)
--- የሸኹ ንግግር አለቀ ---
እዚህ ታሪክ ላይ አንዲትን ማስታወሻ ልጨምር። ታላቁ ነቢይ ኑሕ ዐለይሂ ሰላም የአባትነት አንጀት አላስችል ብሎት ይህ ከሓዲ ልጁ እንዳይሰጥምበት አላህን እንዲህ ሲል ለምኖት ነበር።
(( ኑሕም ጌታውን ጠራ፡፡ አለም «ጌታዬ ሆይ! ልጄ ከቤተሰቤ ነው፡፡ ኪዳንህም እውነት ነው፡፡ አንተም ከፈራጆች ሁሉ ይበልጥ ዐዋቂ ነህ፡፡»))
አላህም እንዲህ ሲል ለኑሕ መለሰለት
(( (አላህም) «ኑሕ ሆይ! እርሱ ከቤተሰብህ አይደለም፤ እርሱ መልካም ያልሆነ ሥራ ነው፤ በርሱ ዕውቀት የሌለህንም ነገር አትጠይቀኝ፤ እኔ ከሚሳሳቱት ሰዎች እንዳትሆን እገስጽሀለሁ» አለ፡፡)) [ሱረቱል ሁድ 45-46]
ከላይ ያለውን በነቢይና በጌታ መካከል የተደረገ ንግግር ልብ ያለ አለን? አባት ለ950 አመታት ተውሒድን ሲያስተምር ልጅ በአባት እያፌዘ ሽርክ ላይ ቀርቶ ነበር። ጭራሽ "ልጄ ሆይ! ና ተውሒድን ተቀበልና ከእኛ ጋር ወደ መርከቡ ላይ ውጣ።" ብሎ አባት የአባትነት ፍፁም ምክሩን ለልጅ ቢሰጥም በሽርክ ልቡ ያበጠው ይህ የነቢይ ልጅ ግን "እንደምትለው ውሃ ምድርን ቢያጥለቀልቃትም ተራራ ላይ ወጥቼ እድናለሁ" ነበር መልሱ። አባት ልጁን ማሸነፍ ቢያቅተው ጌታውን በተማፅኖ የልጁን ደህንነት ለምኖ ነበር። አላህ ግን በርሱ ሐቅ ላይ፣ በተውሒድ ላይ ድርድር የለውምና ነቢዩ ኑሕን "(ይህ የሽርክ ሰው) ልጅህ አይደለም" አለው።
(አታስተነትኑም?)
ተውሒድ ብርሃን ነው ፤ ሽርክ ጨለማ ነው !!