ሐሰን
ታጁ የመፅሀፉ መጨረሻ ላይ “የመረጃ ምንጮች” በሚል ርእስ ስር ከ 120 በላይ መፅሀፍት ዘርዝሯል። “ይህን ሁሉ
ተጠቅሜ ነው ጥልቅ ጥናት ያካሄድኩት” ነው ነገሩ። “እከሌ የሚባለውን መፅሐፍ ስፅፍ ይህን ያክል መፅሀፍት
አገላብጫለሁ” እያለ የፃፈበት ከአሁን በፊት አጋጥሞኛል። ነገር ግን እያደረገ ያለው በሌሎች ስራዎች ውስጥ የሚገኝን
አንድ ሀሳብ ሲወስድ ምንም ሳያመሳክር የተጠቀሙትንም ምንጭ አብሮ ይገለብጣል። ይህንንም ያስባለኘ የሚከተሉትን
ነጥቦች ማስተዋሌ ነው፦
⒈ አቡ ለሃብ በነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) መወለድ ተደስቶ ሡወይባህ የተሰኘችዋን ባሪያውን ነፃ እንዳወጣትና በዚህም ሳቢያ ዘወትር ሰኞ ቅጣት እንደሚቀልለት የሚያወሳው ዘገባ ቡኻሪ ውስጥ እንደማይገኝ አሳልፈናል። ይሁን እንጂ አይናቸውን ግንባር አድርገው “ቡኻሪ ውስጥ ይገኛል” ብለው የፃፉ አሉ። ለምሳሌ ሐሰን ታጁ ደጋግሞ ያጣቀሰው ሙሐመድ ኢብኑ ዐለዊ አልማሊኪ በዚህ ረገድ ተጠቃሽ ነው። [ሐውሉል ኢሕቲፋል፡8] ሐሰን ታጁ ሶሒሕ ቡኻሪን ገልጦ ከማመሳከር ይልቅ የሌሎች ሰዎችን ጥፋት እንደወረደ አስፍሯል። ይህም የሚያሳየው ለማስመሰል ያክል የሚያጣቅሳቸውን ኪታቦች በተጨባጭ እንዳላያቸው ይልቁንም ከሌሎች እንደሚገለብጥ ነው።
⒉ ሌላው አጥኚ ሳይሆን ገልባጭ እንደሆነ የሚጠቁመው በተራ ቁጥር አንድ ላይ የተጠቀሰውን ዘገባ የዘገቡ ሙሐዲሶች ብሎ ኢብኑ ሐጀርን፣ ሶንዐኒን፣ በይሀቂን፣ ኢብኑ ከሲርን፣ ኢብኑ ደይበዕ አልሸይባኒን፣ በገዊን፣ ኢብኑ ሂሻምን፣ አልሱህይሊን እና አልዐሚሪ መዘርዘሩ ነው። ደግሞ እኮ የሚደንቀው ኪተቦቻቸውን ከነ ገፆቻቸው ይጠቅሳል። በየገፁ ስትገቡ ግን ከብዙዎቹ ዘንድ እሱ ያሰፈረውን ሀሳብ አታገኙትም። ይልቁንም እሱ ለመውሊድ ደሊል ያደረገው ቃል የማይገኝበት ቡኻሪ ውስጥ ያለውን ዘገባ ነው ይዘውት የምታገኙት። ቀሪዎቹም የዘገባውን ቡኻሪ ውስጥ አለመገኘት ወይም ደካማ መሆን ጠቁመዋል። ኪታቦችን በተግባር ቢያመሳክር ኖሮ ስህተት ላይ ባልወደቀ ነበር። ነገር ግን ከኢብኑል ዐለዊ ኪታብ ነው ከነ ስህተቱ የኮረጀው [ሐውሉል ኢሕቲፋል፡ 9] ቅደም‐ተከትል እንኳን አልቀየረም። ያኛው ምንጭ የጠቀሰበትን ሲጠቅስ የዘለለውን ዘልሏል። ኮፒ ፔስት። ከዚያ ግን ኪታቦቻቸውን እንዳገላበጠ ሰው የተጠቀማቸው የመረጃ ምንጮች ጋር ይዘረዝራቸዋል። አሳፋሪ!! “የለም በራሴ አጥንቼ የደረስኩበት ነው” ካለ ያለ ጥርጥር ውሸታም ነው። ምክንያቱም ብዙዎቹ እነዚህ ሙሐዲሶች እሱ የጠቀሰውን ዘገባ አላካተቱምና።
⒊ አሁንም ቆርጦ ቀጥል ኮራጅ እንደሆነ የሚያሳየው በተራ ቁጥር አንድ ላይ የተወሳው ዘገባ “ዐባስ ሕልማቸውን ለነቢዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) አወጉ። እርሳቸውም በዝምታ አፀደቁት” የሚል ሀሳብ መሰንቀሩ ነው። ይህን ሃሳብ የኮረጀው ከኢብኑል ዐለዊ ኪታብ ነው [አልኢዕላም፡ 48] ይሄ ሀሳብ በቡኻሪ ቀርቶ በሌሎችም በዘረዘሯቸው ምንጮች ውስጥ አይገኝም።
ይህን “ሰምተው አፀደቁት” የሚለውን አረፍተ‐ነገር ለማግኘት ብዙ ደክሜያለሁ። በመክተበተ አሽሻሻሚላና በጎግል እየተጋዝኩ ባስስም ሊሳካልኝ አልቻለም። ቡኻሪ፣ ሙስሊም፣ አቡ ዳውድ፣ ነሳኢይ፣ ቲርሚዚ፣ ኢብኑ ማጃህ፣ ሙስነድ አህመድ፣ ሙስተድረክ ሐኪም፣ ሶሒሕ ኢብኑ ሒባን፣ ሙስነዱ አሽሻሚይንና አልመጅሙል ከቢር ሊጠበራኒ፣ ሹዑበል ኢማን፣ አስሱነኑል ኩብራ ወስስሱግራ ሊልበይሀቂ፣ መስተኽረጅ አቢ ዐዋናህ፣ ሙሶነፍ ዐብዱራዛቅ፣ መሶነፍ ኢብኑ አቢ ሸይባህ፣ ሙስነድ አቢ የዕላ፣ አስሱንናህ አልበገዊ፣ አስሱንናህ ሊልመርወዚ፣ አልጃሚዕ ሊብኑ ወህብ፣ አልሙንተቃ ሊብኑ ጃሩድ፣ አጥጠበቃት ሊብኑ ሰዕድ፣ ሙሰነድ አሽሻፊዒይ፣ ሙሰነድ አልሑመይዲ፣… አንዳቸውም ውስጥ አላገኘሁትም። የመውሊድ ደጋፊ ከሆኑት ውስጥም ከ 20 ያላነሱ ሪሳላዎችንና ኪታቦችን ተመለክቼ ከኢብኑል ዐለዊ ኪታብ ውጭ አላገኘሁትም። ሰውየው ከየት እንዳመጣው እንጃ። ምናልባት “አንተ ስላላገኘኸው የለም ይባላል ወይ?” ከተባለ እንደዛ አልወጣኝም። ግን በቡኻሪ ስም የዋሸ ሰው ጭራሽ የሌለ ሀሳብ አይሰነቅርም ብየ አልተማመንም። ሶሒሕ ሆኖ ቢያገኙት ኖሮ በርግጠኝነት ሌሎችም የመውሊድ ዘጋቢዎች ያራገረቡት ነበር።
⒋ ሌላው ቆርጦ የሚቀጥል ገልባጭ እንደሆነ የሚጠቁመው የሚጠቅሳቸውን ሙሐዲሶች ስም እንኳን በትክክል አለማስፈሩ ነው። “ሐዳኢቁል አንዋር” የተሰኘውን ኪታብ የኢብኑ ደይበዕ አሸሽይባኒ እንደሆነ አስፍሯል። ኪታቡ የሳቸው ሳይሆን የኢብኑ በሕረቅ ነው። ዝርዝር መረጃ የፈለገ በ 1429 ዓ.ሂ ዳሩል ሚንሃጅ ያሳተመውን የኪታቡን መግቢያ ይመልከት። ሐሰን ይህን ስህተት የኮረጀው ከኢብኑል ዐለዊ ኪታብ ነው ።ሰውየው ስህተቱን ተረድቶ በሌላ ኪታቡ ላይ ቢያርምም ኮራጁ ግን አልባነነም፣ [አልኢዕላም፡ 44]
⒌ ዐብደላህ አትቱወይጂሪን ደጋግሞ የወነጀላቸውም ኪታባቸውን አይቶ አይመስለኝም። መጨረሻ ላይ የተጠቀማቸውን የመረጃ ምንጮች ሲዘረዝር “ቢድዐቱል ኢሕቲፋል ቢል መውሊዲንነበዊ” ብሎ ነው ከስማቸው ጋር ኪታባቸውን የጠቀሰው። የሳቸው ኪታብ ስም ግን “አልቢድዑል ሐውሊያህ” የሚል ሲሆን በ 1406 ዓ.ሂ በአልኢማም ሙሐመድ ኢብኑ ሱዑድ ዩኒቨርሲቲ የማስትሬት ዲግሪያቸውን ለማሟላት የፃፉት ጥናት ነው። ኪታባቸውን እንዳላየው የሚያሳብቀው እሳቸው በኪታባቸው ያሰፈሩትን የኢብኑ ሐጀር ንግግር “ሆን ብለው ቆርጠው አስቀሩት” እያለ ማብጠልጠሉ ነው። ኪታባቸውን ቢያመሳክር ግን በቀላሉ ሻሚላ ላይ እራሱ ያገኘው ነበር። እሱ በስማቸው የሚጠቅሰውን መውሊድ ላይ የተፃፉ የደጋፊም የነቃፊም ኪታቦችን ባስስም አላገኘሁትም።
⒍ ሌላው ሳያመሳክር የሚገለብጥ እንደሆነ የሚጠቁመው የኢብኑ ተይሚያን ኢቅቲዷኡ አስሲራጦል ሙስተቂም ኪታብ ከተጠቀማቸው ምንጮች ማጣቀሱ ነው። ከዚያም በዚህ ኪታባቸው ውስጥ መውሊድ የሚያወጡ ሰዎች “ለነብዩ ባላቸው ፍቅር በድርጊታቸው አጅር (ምንዳ) ያገኛሉ” የሚል መልእክት እንደሚገኝ ጠቅሷል። ኪታቡን ቢያነበው ኖሮ “በድርጊታቸው” የሚል ቃል አያካትትም ነበር። ነገር ግን እንደተለመደው ይህንንም የኮረጀው ከኢብኑል ዐለዊ ኪታብ ነው። [ሐውሉል ኢሕቲፋል 22]
⒎ አሁንም ሳያመሳክር ቆርጦ ቀጥል እንደሆነ የሚያሳየው እንዲህ ማለቱ ነው፦ “የአላህ መልእክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ቤተልሔም ውስጥ እንዲሰግዱ ጅብሪል አዘዛቸው። ሁለት ረከዐ ሰገዱ። የት እንደሰገድክ ታውቃለህ? ሲልም ጠየቃቸው። አላውቅም አሉት። የሰገድከው ዒሳ ከተወለደበት ስፍራ ላይ ነው። ቤተልሔም ይባላል።” ከዚያም ይቃጥልና “የዚህን ሐዲስ አስተላላፊዎች አልሀይተሚ ሶሒሕ ብለዋቸዋል።… ” ይላል [መውሊድ፡ 86]
ይህንን ቅጥፈት የወሰደው ከኢብኑል ዐለዊ ኪታብ ነው። [ሐውሉል ኢሕቲፋል፡ 15] እሱ ግን የሀይሠሚን ኪታብ ያየ ሊመስል ስሙን ከነ ገፁ አስፍሯል። ኪታባቸውን ቢያመሳክር ኖሮ ኢብኑል ዐለዊ እንደዋሸ ያረጋግጥ ነበር። ሀይሠሚ በዚህ ሐዲስ ስር ያሉት እንዲህ ነው፦ “በሰነዱ ውስጥ ኢስሓቅ ኢብኑ ኢብራሂም ኢብኑል ዐላእ አለበት። የሕያ ኢብኑ መዒን ‘ታማኝ ነው’ ሲሉት ነሳኢ ግን ‘ደካማ ነው’ ብለውታል።” [መጅሙዕ አዝዘዋኢድ፡ 1/73] ሀይሠሚ አስተላላፊዎቹን “የሶሒሕ ዘጋቢዎች” ናቸው ያሉት በዚህ ሳይሆን ቀጥሎ ባለው ሰነድ ውስጥ የሚገኙትን ነው። እሱም ውስጥ የመውሊድ ሞጋቾች የሚያጣቅሱት መልእክት አይገኝበትም።
ያላየውን ያላመሳከረውን ኪታብ እየጣቀሰ ማቅረቡ፣ ከተጠቀማቸው የመረጃ ምንጮች ውስጥም ማካተቱ እንደ ጥናት ስርቆት ነው። እንደ አደብ ያወቀበትን ሰው የሚያሸማቅቅ ቆሻሻ ምግባር ነው። ሳይኖረው እንዳለው፣ ሳያውቅ እንደሚያውቅ እያስመሰሉ መቅረብ በዲናችን የተወገዘ ምግባር ነው። እስኪ ይህን ሐዲስ እናስተውል፦ የሆነች ሴት “የአላህ መልእክተኛ ሆይ! ለኔ ጣውንት አለችኝ። ባሌ ያልሰጠኝን እንዳደረገልኝ መስየ ብቀርብ ወንጀል አለብኝን?” ስትል ጠየቀቻቸው። ነቢዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ታዲያ “ባልተሰጠው እንዳለው የሚመሳሰል ሰው ሁለት የቅጥፈት ልብሶችን አንደለበሰ ነው!” አሉ።
[ቡኻሪ፡ 5219፣ ሙስሊም፡ 5705]
ዑለማዎች ከዚህ ሐዲስ በመነሳት የራሱ ባልሆነ ወይም በሌለው ነገር እንዳለው መስሎ የሚኮፈስን በከባድ ይኮንናሉ። እናም በጥናት ላይ የሌላን ስራ እየገለበጡ ሰፊ ምርመር ያደረጉ መስሎ መቅረብ ልክ በሐዲሱ እንደተገለፀው ሁለት የተውሶ ልብስ ለብሶ የራሱ አስመስሎ እንደሚዘንጥ ሰው ነው።
[መውሊድ፡ ታሪክ ፤ ግድፈት ፤ እርምት ከሚለው የኢብኑ ሙነወር መፅሀፍ ከገፅ 296‐299 የተወሰደ ]