Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የድግምት ህክምና መንገዶች

የድግምት ህክምና መንገዶች

ድግምትን ከተደገመበት ግለሰብ ላይ መፍታትና ማከም “አል-ኑሽራ” ተብሎ ይጠራል፡፡

ሸይኽ ሱለይማን ቢን አብደላህ ቢን መሐመድ ቢን አብድልወሀብ ከአቢ አልሰዓዳት “ተይሲሩ አል አዚዝ አል ሀሚድ” ከተባለው መፅሐፍ ላይ በመውሰድ ሲያብራሩ፦

«አል ኑሽራ ጂን የተለከፈውን ግለሰብ የማከምና ሩቃ የማድረግ ሂደት ነው፡፡ አል ኑሽራ ተብሎ የተጠራበት ምክንያት በሽታው ለውጦት የነበረውን ግለሰብ ስለሚያስወግድለት ነው» ብለዋል፡፡

ሸይኽ መሐመድ ቢን አብድልወሀብ ከኢብኑ አልቀይም እንዳወሩት “አል ኑሽረቱ” ድግምትን ከተደገመበት ግለሰብ ማላቀቅ ነው፡፡

እሱም ሁለት አይነት ነው፡፡

አንደኛው፦

ድግምት በድግምት መፍታት ይህ የሰይጣን ተግባር ነው፡፡ የሀሰን ንግግርም “አል ኑሽራ ከድግምት ነው” የሚለውና “ድግምትን ደጋሚው እንጂ ማንም አይፈታውም” የሚለው ንግግር የሚተረጐመው በዚህ ነው፡፡ ድግምት አድራጊውና ድግምት የተሰራበት ግለሰብ ሰይጣን ወደሚወደው ነገር በመቃረብ ድግምቱ ውድቅ እንዲሆን ያደርጋሉ፡፡

የተፈቀዱ ንባቦችን መጠበቂያዎችንና መድሃኒቶችን በመጠቀም መፍታት የተፈቀደ ነው፡፡ የመጀመሪያው አይነት በጃቢር ሀዲስ የተጠቀሰውን ትርጉም የያዘ ነው፡፡

ነብያችን ﷺ ስለ አል ኑሽራ ተጠይቀው

«እርሱ የሰይጣን ተግባር ነው» ብለዋል፡፡
ይኸውም ድግምትን በድግምት መፍታት ነው። ይህ አይነቱ ድግምት ወደ ሰይጣን በመቃረብ ካልሆነ በስተቀር አይሟላም ምክያቱም ሰይጣናትና ደጋሚዎቹ እስካልታዘዟቸውና በአላህ እስካልካዱ እና በዚህ ተግባራቸው ወደ እነርሱ ካልተቃረቡ በስተቀር አይታዘዟቸውም፡፡

ስለዚህ አንድ ግለሰብ ድግምቱ እንዲፈታለት ወደ ደጋሚው ጋር ሲሄድ ለሰይጣን እንዲያርድ ወይም በማንኛውም መቃረቢያ ወደ ሰይጣን እንዲቃረብ ያዘዋል፡፡ ይህ አይነት ተግባር የተከለከለ ለመሆኑ ማንም አይጠራጠርም፡፡ ምክንያቱም በአላህ ላይ መካድና ማጋራት ነው፡፡

የአላህ መልዕክተኛ ﷺ እንዳሉት “እርሱ የሰይጣን ተግባር ነው” ይህም በሽታን እንጂ ሌላን አይጨምርላቸውም፡፡ ምክንያቱም ደጋሚ እርኩስ ነው እርኩስ የሆነ ደግሞ የሰውን ጉዳት እንጂ ማስተካከልን አያስብም፡፡

ደጋሚው የወንድሙን ድግምት መፍታት አይሆንለትም ምክንያቱም በወንጀል ላይ አንድ ናቸውና፡፡ ነገር ግን ግራ ሊያጋባውና ለሰይጣን ስለት የገባውን ይሞላ ዘንድ በሽታውን ረገብ ያደርግለታል፡፡ ከዚያም በድጋሚ ይመለስበታል፡፡

ሁለተኛ አይነት፡

የተፈቀደ ህክምና ሲሆን ይኸውም የተፈቀደ ሩቃ ከቁርአን፣ ከአዝካር፣ ከትክክለኛ ዘገባ ከነብያችን በተገኙ መጠበቂያዎች፣ የተፈቀዱ መድሃኒቶችን፣ የዘምዘም ውሃን የመሰለ፣ ጥቁር አዝሙድ፣ የዘይቱን ዘይት፣ የመዲና ተምር መጠቀም ይቻላል፡፡ እነዚህ መድሃኒቶች ሁሉ በትክክለኛ ዘገባ ከነብያችን ﷺ የተገኙ ናቸው፡፡

‪#‎ሺፋእ‬

ቁርዓናዊ ፈውስ ለጂን እና ሲህር !

ፔጁን ላይክ ለማድረግ፡-
https://www.facebook.com/nosihr
ሼር በማድረግ ሙስሊሙን ዑማ በብዛት እየጎዳ ያለውን የሲህር በሽታ
ለመከላከል የበኩሎን አስተዋፅዖ ያበርክቱ!