ድግምት በሙስሊሙ ህብረተሰብ ላይ ያለው አደገኝነት
ኢስላማዊ ማህበረሰብ ሀይሉን የሚያጠናክረው በአላህ ሃይማኖት ላይ ሲያያዝና ማህበራዊነትን ሲፈጥር ነው፡፡ ይህ ደግሞ ኢስላም ከተጣረበት መንገድ አንዱ ነው፡፡ አላህ I እንዲህ ብሏል
يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا اتَّقُوا اللَّهَ حَقَّ تُقَاتِهِ وَلَا تَمُوتُنَّ إِلَّا وَأَنتُم مُّسْلِمُونَ [٣:١٠٢]
وَاعْتَصِمُوا بِحَبْلِ اللَّهِ جَمِيعًا وَلَا تَفَرَّقُوا [٣:١٠٣]
‹‹እናንተ ያመናችሁ ሆይ አላህን ተገቢውን መጠንቀቅ ተጠንቀቁት እናንተም ሙስሊሞች ሆናችሁ እንጅ አትሙቱ የአላህንም ገመድ ሁላችሁም ያዙ፤ አትለያዩም›› (አል ዒምራን 1ዐ2-1ዐ3)
በሌላም አንቀጽ ላይ አላህ I እንዲህ ብሏል
((وَأَطِيعُوا اللَّهَ وَرَسُولَهُ وَلَا تَنَازَعُوا فَتَفْشَلُوا وَتَذْهَبَ رِيحُكُمْ )) الأنفال: ٤٦
‹‹አላህን ና መልዕክተኛውንም ታዘዙ: አትጨቃጨቁም:ትፈራላችሁና: ሃይላችሁም ትሄዳለችና›› (አል አንፋል 46)
የአላህ መልዕክተኛ ﷺ እንዲህ ይላሉ “የሙእሚን ምሳሌው በመዋደዳቸው፣ በመተዛዘናቸው፣ በርህራሄያቸው አንድ አካል ነው፡፡ከሰውነት ክፍል አንዱ ከተጐዳ ሌሎች የሰውነት ክፍል ትኩሳትና ህመም እንደሚሰማው” ቡኻሪና አህመድ ዘግበውታል
በሌላም ሀዲስ “ሙእሚን ለሙእሚን እንደ አንድ ግንብ ነው አንዱ ሌላውን ያጠነክረዋል፣ ጣታቸውን በማያያዝ አመለከቱ” ቡኻሪና አህመድ ዘግበውታል
ኢስላም መለያየትንና መወዛገብን እንዲሁም ለዚህ ምክንያት የሚሆኑ ነገሮችን ከልክሏል፡፡ ምቀኝነትን፣ መኮራረፍን፣ የወንድምን ገንዘብ ማስበላት፣ የሰውን ነውር መከታተልን፣ መፈላፈልን፣ መጥፎ ጥርጣሬን ከልክሏል፡፡ እንዲሁም ሀሜትንና በደልን ከልክሏል፡፡ ዝምድናን በመቀጠል፣ በመተዛዘን፣ ለጐረቤት በጐን በመዋል፣ በሰዎች መሀከል በማታረቅ አዟል፡፡ ይህ ሁሉ የሆነው ህብረተሰቡ የጠነከረ መያያዝ እንዲኖረውና አላህ I ያዘዘውን መልዕክት ይፈጽም ዘንድ ነው፡፡
ድግምት የኢስላም ጠላቶች ከጂንና ከሰው የሆኑ ሰይጣናትና ወዳጆቻቸው ቤተሰብን ለማፍረስ፣ በባልና በሚስት መሀከል ለመለያየት፣ በቤተሰብና በህብረተሰብ ውስጥ ጠላትነትን፣ ልዩነትንና መበታተን እንዲከሰት የሚደገፉበት የሆነ ተግባር ነው፡፡ባልና ሚስት የቤተሰብ ምሶሶ ናቸው፡፡ በእነርሱ መሀከል ጥላቻ፣ መቃቃርና ልዩነቶች ከተከሰተ የተረበሸና ያልተረጋጋ ቤተሰብ ይፈጠራል፡፡
በተጨማሪ ባልና ሚስት ግዴታ ለሆነባቸውን ኢስላማዊ አስተዳደግንና ቤተሰብን መገንባት ላይ መቆምን አይችሉም፡፡ ከዚህ ቤተሰብ የዲን ፅናትንና በጐ መሆንን የማያውቁ ትውልድ ይወጣል፡፡ ምክንያቱም ህብረተሰብ የሚገነባው ከቤተሰብ ነው፡፡ የቤተሰብ መበላሸት የህብረተሰብን መበላሸት ያስከትላል፡፡ ስለዚህ በሙስሊም መሪዎች፣ በምሁሮች፣ ወደጥሩ ነገር ተጣሪዎች (ዱዓት) ላይ ድግምትን በሁሉም መልኩ ሊዋጉት ግድ ይላል፡፡
እንደዚሁም ደጋሚዎችንና አጭበርባሪዎችን በከፍተኛ ሁኔታ መዋጋት ግዴታ ነው፡፡ በኢስላም ህብረተሰብ መሀከል የሚያደርሱት ጥፋት ከፍተኛ ነው።
#ሺፋዕ
ቁርዓናዊ ፈውስ ለጂን እና ሲህር !
ፔጁን ላይክ ለማድረግ፡-
https://www.facebook.com/nosihr
ሼር በማድረግ ሙስሊሙን ዑማ በብዛት እየጎዳ ያለውን የሲህር በሽታ ለመከላከል የበኩሎን አስተዋፅዖ ያበርክቱ!