Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

አማኝ ሴት ኒያዋን ካስተካከለች ከአማኝ ወንድ የበለጠ ኢባዳ ትፈፅማለች

ተንቢሀት - ሙስሊም ሴቶችን የተመለከቱ ህግጋት



አማኝ ሴት ኒያዋን ካስተካከለች ከአማኝ ወንድ የበለጠ ኢባዳ ትፈፅማለች፤

1) አማኝ ሴት ለባለቤትዋና ለቤተሰቦችዋ ምግብ ስታዘጋጅና ስታገለግላቸው አላህን እየታዘዘች የአምልኮ ተግባርም እየፈፀመች ነው። ይህም ሀሰናተዋን ያበዛዋል፣ አጅሯንም ከፍ ያደርገዋል።

2) አማኝ ሴትን በረመዳን የቀኑ ክፍል የምግብ ዝግጅት አላህን ከማወደስና ከማላቅ ሊከለክላት አይገባም። ሱብሀነላህ፣ ላ ኢላሀ ኢለላህ እያለች ጌታዋን እያወደሰች ምግብ ብትሰራ አጅሯ ከፍ ይላል።

☞ ደስ ይበላት፦ ኒያዋን አስተካክላ ባለቤቷንና ቤተሰቦችዋን የምታገለግልና ይህም በቻለችው ልክ በረመዳን የቀኑ ክፍል ኢባዳ ከማድረግና አላህን ከማወደስ ያልተዘናጋች አማኝ ስኬታማ ሆናለች!!

ከሸይኽ ሱለይማን አሩሀይሊይ ንግግር የተወሰደ

© ተንቢሀት