Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ለሴት ልጁ ጥሩ ሰፍ የቱ ነው?

🗒ለሴት ልጁ ጥሩ ሰፍ የቱ ነው?
ጥያቄ፦
የሴቶች ሰፍ ሑክሙ ምንድነው? በማንኛውም ሁኔታ ቢሆን የሴቶች ሰፍ የመጀመሪያ መጥፎ የመጨረሻው ጥሩ ነው ወይስ በሴቶችና በወንዶች መካከል የሚጋርድ ነገር ሳይኖር ነው?
መልስ፦
ሴቶች ከወንዶች ጋር አንድ ቦታ ላይ ከሆኑ ለሴቶች የመጨረሻው ሰፍ ከመጀመሪያው ይበልጥላቸዋል። ነቢዩ (ሰላሏህ አለይሂ ወሰለም)
«ከሴቶች ሰፍ በላጩ የመጨረሻው ሲሆን መጥፎው የመጀመሪያው ነው» ብለዋል።(ሙስሊም)
ይህም የሆነበት ምክንያት ለሴቶች የመጨረሻው ሰፍ ከወንዶች የራቀ ሲሆን የመጀመሪያው ደግሞ ለወንዶች ስለሚቀርብ ነው። በዛሬ ጊዜ እንደሚታወቀው በአብዛኛው መስጊድ ሴቶች የተለየ ቦታ አላቸው። ይህ ከሆነ ደግሞ ከመጨረሻው ይልቅ የመጀመሪያው ሰፍ ይበልጥላቸዋል።
📚【ሸኽ መሐመድ ኢብኑ ሷሊህ አልዑሰይሚን ረሂመሁላህ】
________
📝 06 ኤፕሪል 2016
https://www.facebook.com/tenbihat
©ተንቢሀት