አሰላሙ ዐለይኩም ወንድሞች እህቶች
ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን! በርካታ ወንድሞቻችን ከግብፅ ወደ
ጣሊያን ሲሻገሩ ጀልባው ተገልብጦ ህይወታቸው አልፏል፡፡ ሟቾቹን አላህ ይማራቸው ቤተሰቦቻቸውን አላህ ትእግስቱን
ይስጣቸው፡፡ እኛን ደግሞ የሆነ አደጋ በሰማን ቁጥር ወደ ጥፋት ከመሄድ ይጠብቀን፡፡
በሚገርም ሁኔታ በተከታታይ እየደረሱ ያሉ አደጋዎችን ተከትሎ
1. አንዳንዱ ዘግናኝ ፎቶዎችን፣ የሟች ምስሎችን ይለቃል፡፡ ይህም እንደ ፎቶው አይነት ብዙ ጥፋቶችን
ያስከትላል፡፡ በአሸባሪዎች የተፈፀሙ ዘግናኝ ድርጊቶችን የሚያሳዩ ፎቶዎችን በማሰራጨት ኢስላምን ለሚያጠለሹ
ፍርደ-ገምድሎች የቤት ስራ የሚሰራ አለ፡፡
2. ሌላው አስለቃሽ ግጥሞችን በመገጣጠም የሟች ቤተሰቦችን ስቃይና ሀዘንም ይጨምራል፡፡ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይ ወሰለም በሟች ላይ ሙሾ ማውረድን ከአራት የጃሂሊያህ ጥፋቶች አንዱ እንደሆነ ጠቅሰዋል፡፡
3. ሌላው ጊዜን የሚራገም አለ፡፡ የጊዜ ባለቤቱ አላህ ነው፡፡ እንዳሻው የሚገለባብጠው እሱ ብቻ ነው፡፡
በእንዲህ አይነት ሁኔታዎች ላይ ልናደርግ የሚገባን
1. ስለ ትእግስት መመካከር
2. ስለ ቀደር መተዋወስ
3. የሟች ቤተሰቦችን ስለሚያፅናኑ ነገሮች መነጋገር
4. ደካሞች ከሆኑ እና ከቻልን መርዳት
5. ክስተቱን ተከትሎ የሚጠበቁ ጥፋቶችን እንዳይፈፀሙ መመካከር፣ ከተፈፀሙም መተራረም
6. ሟቾቹ ሙስሊሞች ከሆኑ አላህ እንዲምራቸው ዱዐህ ማድረግ
7. የሚቻል ከሆነ ሌሎች ተመሳሳይ አደጋ ላይ እንዳይወድቁ ስለ አስፈላጊ ጥንቃቄዎች (ሰበቦች) መተዋወስ ነው፡፡
አላህ ከጥፋታችን ይቅር ይበለን፡፡ አሚን፡፡
ኢብኑ ሙነወር( በተመሳሳይ አደጋ ከሊብያ ወደ ጣልያን ሲሄዱ በደረሰ አደጋ ተፅፎ ከነበር የተኮረጀ)