Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ሸይኽ ሳሊህ አልፈውዛን ይመክሩሻል... ጆሮ ስጪ!!



ሸይኽ ሳሊህ አልፈውዛን ይመክሩሻል... ጆሮ ስጪ!!

ሙስሊሟ ሆይ!
ሒጃብ፤ ልባቸው የታመመ የሰው ውሾች ከሚወረወሯቸው የተመረዙ እይታዎች ይጠብቅሻል። የተነሳሱ መጥፎ ምኞቶችንም ያከስማል። ሒጃብሽን አጥብቀሽ ያዢ። ሒጃብን የሚዋጉና አስፈላጊነቱን አቅልለው የሚያቀርቡትን እኩይ ተልእኮ ያላቸው ሰዎች አሉባልታዎች አታዳምጪ። ላንቺ መጥፎ መንገድን እንጂ እንደማይፈልጉም አትጠራጠሪ። አላህ እንዳለው፤

ﻭَﻳُﺮِﻳﺪُ اﻟَّﺬِﻳﻦَ ﻳَﺘَّﺒِﻌُﻮﻥَ اﻟﺸَّﻬَﻮَاﺕِ ﺃَﻥ ﺗَﻤِﻴﻠُﻮا ﻣَﻴْﻼً ﻋَﻈِﻴﻤًﺎ
«እነዚያም ስሜቶቻቸውን የሚከተሉት (ከውነት) ትልቅን መዘንበል እንድትዘነበሉ ይፈልጋሉ፡፡» ኒሳእ 27

ተንቢሀት አላ አህካሚን ተኽተሱ ቢል ሙእሚናት ገፅ 46


© ተንቢሀት