Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ሸይኽ ሙሀመድ አሊ አደም አል ኢትዮጲ ማናቸው? ።




ሸይኽ ሙሀመድ አሊ አደም አል ኢትዮጲ ማናቸው? ።

እኚህ ታላቅ ዐሊም ሙሐዲስ ፣ ፈቂህ ፣ ዑሱሊ እና ነህዊይ ሙህመድ ኢብን አሽ፡ሸይኽ አል ዐላማ ዐሊይ ኢብን አደም ኢብን ሙሃመድ አል ኢትዮጲ አል ወልዪ ናቸው።
(هو الشيخ العلاّمة المحدث الفقيه الأصولي النحوي محمد بن الشيخ العلامة علي بن آدم بن موسى الأتيوبي الولّوي.)

ሃገራችን ላይ ከሚገኙ ታላላቅ ዐሊሞች ኢልምን የቀሰሙ ሲሆን ከነርሱም ውስጥ አባታቸው አሽ፡ሸይኽ ዐብዱል ባሲጥ ኢብን ሙሀመድ ኢብን ሀሰን አል ኢትዮጲ አል ቦረኒ አል ምናሢ እና ሌሎችም ዑለማዎች ተምረዋል።
(أخذ العلم عن كثير من علمـاء بلده ومنهـم والده والعـلاّمة الشيـخ عبـد الباسـط بن محـمد بن حسـن الإتـيوبي البُوَرَنّي المِـنَاسيّ وغيـره من العلماء.)

ብዙ የሆኑ የ አረብኛ ስነፅሁፍና ግጥሞችና ሌሎችም ዲናዊ ዘርፎችን በቃላቸው ሸምድ ደዋል ። ከነርሱም አልፊያ ኢማም ማሊክ (ባለ አንድ ሺህ ስንኝ) እና አልፊያ አስ፡ሱዩጢ (አንድ ሺህ ስንኝ በሙስጦለሃል ሃዲስ) እናም የመሳሰሉት ዘርፎች ላይ ጠለቅ ያለ ዕውቀትን አካብተዋል ። በነህው ፣ በሶርፍ ፣ በበላጛ ፣ በዑሱል ፣ በመንጢቅ ፣ በሕዲስ ፣ በፊቕ ፣ በሌሎች ኢስላማዊ ጥናቶች ላይ ላቅ ያለ ዕውቀት አላቸው።
(حفظ الكثير من متون العلم والمنظومات العلمية كألفية ابن مالك وألفية السيوطي في المصطلح وغيرها من المتون وبرع في علم المعقول والمنقول من نحو وصرف وبلاغة وأصول ومنطق وحديث وفقه وغيرها من علوم الإسلام.)

ከዚያም ወደ መከተል ሙከረማ ተጉዘው በመስጂደል ሐርም ውስጥ የማታ ትምሕርትን መስጠት ጀመሩ ። ሸኹ እራሳቸው በ አላህ ቤት ውስጥ ከፍተኛ ዕውቀትን ያካበቱ ሲሆኑ ብዙ ኩቱቦችንም በተለይም በሕዲስ ዘርፍ ላይ ፅፈዋል።

(ثم انتقل إلى بلد الله الحرام مكة المكرمة وهو الآن يدرّس نهاراً في دار الحديث الخيرية وفي مسجدها ليلاً . وقد بذل الشيخ نفسه للعلم ولطلبته في بلد الله الحرام وله الكثير من المؤلفات في فنون العلم وخاصةً في علم الحديث الشريف)

ከፃፏቸው ኩቱቦች ውስጥ
(فمن مؤلفاته..)

ሸርሑ አልፊያ አስ፡ሱዩጢ በሃዲስ «ዑሱሉል ፊቕህ አላ መንሕጁ አሕለል ሱንናህ ወልጀመዓ » ከሁለት ሺህ በላይ ስንኞች ያሉት ማብራሪያ የታተመ
(1)
(شرح ألفية السيوطي في الحديث المسمى “إسعاف ذوي الوطر بشرح نظم الدرر , في علم الأثر”ويقع في مجلدين وهذا هو الشرح المختصر على الألفية وله شرح موسع لم يطبع)

ሸርሁ (ማብራሪያ) ነሳዒ «ዘሒራ አል ዑቅባ ፊ ሸርሒል ሙጅተባ» በአርባ ጥራዝ ፤ ከነርሱም ከ አስራ ሶስት እስከ አስራ ሰባት ከሚሆኑ ጥራዞቻቸው ታትሞ ከዒልማቸው አስጠቅመውናል ።
(2)
(شرح سنن النسائي المسمى “ذخيرة العقبى في شرح المجتبى ويقع في أربعين مجلد , أبان فيه عن علم واسع واطلاع مذهل وقد طبع منه بضع عشر مجلد)

የኢብኑ ማጃህ ማብራሪያ «መሽሪቀል አንዋር አል ወሃጃ ወመጣሊል አስራር ወል ቡህጃ» ይህን ማብራሪያ ሸኹ እያገባደዱት ሲሆን ሲገባደድም በ አስርት የሚቆጠሩ ጥራዞች ይወጡታል ።
(3)
(شرح سنن ابن ماجه المسمى “مشارق الأنوار الوهّاجة ومطالع الأسرار البهّاجة ولا يزال الشيخ في صدد اكماله ولو أُكمِل لوقع في عشرات المجلدات)

አ «ቁረቱል ዐይን» የሁለቱ ሰሒሆች (ቡኻሪና ሙስሊም) ሃዲስ የሚዘግቡት ሰዎችን ታሪክ በ አንድ ጥራዝ
(4)
(قرة العين في تلخيص تراجم رجال الصحيحين ويقع في مجلد واحد.)

ግጥም «አል ጀዋሪሂል ነፍስ ፊ ነዝም አስማ ወመራቲብ አል ሙወሲፊን ቢተድሊስ» ሙደሊስ ዘጋቢዎችን የሚገልፅ የመቶ አስራስምንት ስንኝ ግጥም
(5)
(منظومة في بعض الرواة المدلسين المسماه “الجوهر النفيس , في نظم أسماء ومراتب الموصوفين بالتدليس” وعدَّتها مائة وثمانية عشر بيتاً)

(«ሸርሑል ሙስሊም ታትሞ ያልቀ» )
(6)
(شرح مقدمة صحيح مسلم وهي الآن تحت الطبع)

(ቭ «አል ጀሊሱ ሷሊህ አን፡ነፍዒ ቢተዋዲህ መዓኒል ከዋኪብ አስ፡ሳጢዒ» የኢማሙ ሱዩጢ ዑሱሉል ፊቕ ግጥም ማብራሪያ በ አንድ ትልቅ ጥራዝ
(7)
(الجليس الصالح النافع بتوضيح معاني الكوكب الساطع وهو شرح أصولي لمنظومة الإمام السيوطي في أصول الفقه ويقع في مجلد ضخم.)

ቭ «ዑሱሉል ፊቕህ አላ መንሕጁ አሕለል ሱንናህ ወልጀመዓ» ከሁለት ሺህ በላይ ስንኞች ያሉት ማብራሪያ የታተመ
(8)
(منظومة في أصول الفقه على منهج أهل السنة والجماعة تفوق الألفين بيت وله عليها شرح طبع بعضه في مذكرات.)

ቭ «ፈትሑል ቀሪብ አል ሙጂብ ፊ ሸርሒል ሙድባ አል ሃቢብ ሚመን ዩወሊ ሙጝኒ አልለቢብ» ሸኻቸው ዐብዱል ባሲጥ ሙሀመድ ያዘጋጁት የነህው ግጥም ማብራሪያ
(9)
(فتح القريب المجيب في شرح كتاب مدبي الحبيب ممن يوالي مغني اللبيب في علم النحو وهو شرح لمنظومة شيحه العلاَّمة عبد الباسط بن محمد البُوَرَنّي)

እና የመሳሰሉት እዚህ ያልተጥቀሱ ኩቱቦችንም ፅፈዋል እኚህ ታላቅ ኢትዮጵያዊ ሸኽ (አላህ ይጠብቃቸው)
(وغيرها من المؤلفات التي لم تر النور بعد.)

ሸኹ በአሁኑ ጊዜ በመስጂደል ሐረም (መካህ) የሚያስተምሩ ሲሆን በርካታ ከዐለም የተወጣጡ ተማሪዎች አሏቸው ።

ከሳቸው የተማሩ ተማሪዎችም በ አሁኑ ሰዐት ሸኹ ዕውቅና (ተዝኪያ) ሰጥተዋቸው በተለያዩ የዐለም ክፍሎች ላይ የተማሩት እያስተማሩና ፈታዋ እየሰጡ ይገኛሉ ።

ከዚህ በታች የሚገኘው ሸኹ በሃረም መስጂድ ዳሩል ሃዲስ የሚያስተምሩበት የትምሕርቱና የቀኑ ፕሮግራም ሲሆን አሁን ላይ ያለውን ግን እርግጠኛ መሆን አልችልም።
(وكما ذكرنا آنفاً فإن للشيخ دروس في المساء لازالت مقامة إلى الآن في مسجد) (دار الحديث الكائن بشارع أجياد جنوب الحرم المكي الشريف على مدار الأسبوع على النحو التالي) :
(*السبت : مصطلح الحديث , شرح ألفية السيوطي , بعد العشاء.)
(*الأحد : شرح سنن إبن ماجه , بعد العشاء.)
(*الإثنين : شرح سنن النسائي , بعد العشاء.)
(*الثلاثاء : شرح الكوكب الساطع , بعد العشاء.)
(*الجمعة : شرح منظومته في أصول الفقه , بعد المغرب.)
(فتح القريب المجيب في النحو, بعد العشاء.)

መረጃውን ያገኘሁት ከታች ይሚገኘው አስፈንጣሪ ውስጥ ነው ።
(http://www.ahlalhdeeth.com/vb/showthread.php?t=8297)

አላህ በህይወት ያቆያቸው ጤናንም ይስጣቸው ከዒልማቸው የምንጠቀምም ያድርገን

Post a Comment

0 Comments