Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ነጃሳ ስለመሆናቸው ማስረጃ ያላቸው ነገሮች!

ነጃሳ ስለመሆናቸው ማስረጃ ያላቸው ነገሮች!

1. የሰው ልጅ ሽንትና ፀያፍ ነገሮች ምግብ ያልጀመረ የህፃን ወንድ ሽንት ግን በላዩ ውሃ መርጨት ብቻ በቂ ነው፡፡ ለዚህ ማስረጃው ኡሙ ቀይስ ቢንት ሚህሰን ያስተላለፉት ሀዲስ ነው፦

«ምግም መብላት ያልጀመረ ህፃን ወንድ ልጅ ነብዩ (ﷺ) ዘንድ አመጣችና እሳቸውም በእቅፋቸው አደረጉት ህፃኑም በነብዩ (ﷺ) ልብስ ላይ ሲሸና ነብዩ (ﷺ) ውሃ እንዲመጣ አደረጉና ሳያጥቡት በመርጨት ብቻ ተብቃቁ፡፡»

ምግብ የጀመረ የህፃን ወንድና የህፃን ሴት ልጅ ሽንት ግን እንደ አዋቂ ይታጠባል፡፡

2. ስጋው ከሚበላ እንስሳ የሚወጣ ፈሳሽ ደም ነጃሳ ሲሆን ጉሮሮ ወይም ስጋ ላይ የሚቀረው ደም ግን ጦሃራ ነው፡፡

‹‹…ወይም ፈሳሽ ደም…››
(አል አንዓም 145)

3. የማንኛውም ስጋው የማይበላ እንስሳ ሽንትና ፈርስ፦ ለምሳሌ የድመትና የአይጥ::

4. በክት፦ ማለትም ሸሪዓዊ በሆነ መንገድ ሳይታረድ የሞተ እንስሳ ከዚህ ውስጥ ግን ዓሳ፣ አንበጣና ፈሳሽ ደም የሌላቸው ነገሮች ይለያሉ፡፡ እነዚህ ጦሃራ ናቸው::

5. “መዝይ” መዝይ ማለት ቀጭን ነፃ ያለ የዘር ፈሳሽ መሳይ ሲሆን አብዛኛውን ጊዜ በመተሻሸት ወይም ግብረስጋ ግንኙነትን በማሰብ የሚፈስ ነው፡፡ አፈሳሰሱ ግን በሀይልና በስሜት አይደለም፡፡ እንዲሁም ከፈሰሰ በኋላ ድካም ካለመሰማቱም በላይ መፍሰሱም ላይታወቅ ይችላል፡፡ ይህ ፈሳሽ ነጃሳ ለመሆኑ ማስረጃው ነብዩ (ﷺ) በዚህ ጉዳይ ላይ ለዓልይ እንዲህ ማለታቸው ነው:–

«ውዱእ አድርግ ሀፍረተ ገላህንም ውሃ አፍስስበት፡፡»

(ቡኻሪ ዘግበውታል)

እንዲታጠብ ያላዘዙት ይህን ፈሳሽ መራቅ ስለማይቻል ለማግራራት ሲሉ ነው፡፡

6. “ወድይ” ይህም ነጣ ያለና ወፈር የሚል ፈሳሽ ሲሆን ከሽንት ተከትሎ የሚፈስ ነው፡፡

7. የወር አበባ ደም፦
አስማእ ቢንት አቢበክር እንዳስተላለፉት

«አንዲት ሴት ወደ ነብዩ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) በመምጣት እንዲህ በማለት ጠየቀቻቸው “የወር አበባ ደም ልብሳችንን ሲነካው እንዴት ነው የምናደርገው?”
እሳቸውም እንዲህ ብለው መለሱ፦
“በደረቁ ትፈግፍገው ከዚያ በውሃ ቆንጠር አድርጋ ትሸው ከዚያ ሙሉ በሙሉ ትጠበውና ትስገድበት፡፡”

[ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል]

‪#‎ፊቅህን_ለመረዳት‬

የፌስ ቡክ ገፃችንን ለማግኘት…
www.facebook.com/easyfiqh
ሼር ማድረግ እንዳይረሱ!