Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

እህቶች ሆይ!! በሚጥል በሽታ የተጠቃች አንዲት ታላቅ ሴት ነበረች — በነብዩ صلى الله عليه وسلم ዘመን ።



እህቶች ሆይ!!
በሚጥል በሽታ የተጠቃች አንዲት ታላቅ ሴት ነበረች — በነብዩ صلى الله عليه وسلم ዘመን ።

ነብያችን ዘንድ በመቅረብ ያንገላታትን በሽታ በተመለከተ አላህን እንዲለምኑላት ጠየቀቻቸው ። መልእክተኛውም

إن شئت صبرت ولك الجنة وإن شئت دعوت الله أن يعافيك

" ከፈለግሽ ታገሺና ላንቺ ጀነት አለልሽ። ከፈለግሽ ደግሞ ጤና እንዲለግስሽ አላህን ልለምንሽ " አሏት ።
ይህቺ አኺራዋን ከዱንያዋ— ለዛውም አሳሳቢ ከሆነው ጤናዋ— ያስቀደመች ሴት በሽታዋን በተመለከተ
" እታገሳለሁ " አለች ።
ልብ በሉ እህቶች! ! "በበሽታው ምክንያት መውደቄን እታገሳለሁ" ነበር አባባሏ! — ይህንን ከባድ በሽታ እታጋሳለሁ ነበር ነገሯ ! !
ነገር ግን ልትታገሰው የከበዳት አንድ ጉዳይ ነበርና ነብዩን እንዲህ ስትል ጠየቀች ፣ " በምወድቅ (በሽታው በሚጥለኝ ግዜ) ሰውነቴ ይጋለጣልና አካሌ እንዳይራቆት አላህን ለምኑልኝ አለች ። አንዳንድ ዘገባዎች ላይ እንደተብራራው ይህቼ ሴት ከነብዩ ዱዓ በሇላ በሽታዋ ቢጥላትም ሰውነቷ በፍፁም አይጋለጥም ነበር— በነብዩ ዱዓ በረካ።
ይህች ታላቅ ሴት በበሽታዋ ምክኒያት መደበቅ ያለበት አካሏ ቢጋለጥ እንኳን ነገሩ በፈቃዷ የተከሰተ አይደለምና የምትጠየቅበት ወንጀል አይደለም ። ከዚህም ጋር ጉዳዩ ይህን ያህል አሳስቧት ነበር — አላህን መፍራት ማለት ይሄ ነው! ቀደምት ምርጦቻችንና ተምሳሌቶቻችን እንዲህ ነበሩ!!
ታዲያ ምን ነው?!.... አንዳንድ እህቶች በዳዕዋ ስም ተቀባብተው ለጅምላ እይታ መቅረባቸው? ! ምን ነው ታዲያ አንዳንድ እህቶች ተኳኩለውና መደበቅ ያለበትን አካል ገላልጠው አደባባይ መውጣታቸው? ! ኧረ አይበጅም እህቶች !! አላህን ፍሩ! ! ይሄ ገላ ከመፈራረሱ በፊት ይህንን ገላ ወደሰጣችሁ አላህ ተመለሱ! !


Post a Comment

0 Comments