Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

በደጋግ ቀደምቶች ዘመን ሴት ወንዶችን ታስተምር ነበርን ?

በደጋግ ቀደምቶች ዘመን ሴት ወንዶችን ታስተምር ነበርን ?
بسم الله الرحمن الرحيم وبه أستعين وصلاة ربي وسلامه على خير المرسلين وبعد.
🔸"ሴት ልጅ በድምጽ ሚዲያ ላይ መሳተፍ የለባትም" ሲባል ዓኢሻን رضي الله عنهما ጨምሮ በርካታ ሴቶች ወንዶችን ያስተምሩ አልነበር?! እያሉ በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ሐቅና ባጢልን ለማቀላቀል የሚፈልጉና አላዋቂዎችንም የሚያደናብሩ ሰዎች አሉ
💥ዓኢሻም ትሁን ሌሎች አደባባይ ላይ ሙእሚኑም ሙናፊቁም ባለበትና ሁሉም ድምጻቸውን በሚሰሙበት መልኩ አልነበረም የሚያስተምሩት፣በቋሚነትም ወንዶችን አያስተምሩም ነበር፣
እቤታቸው ውስጥ ተቀምጠው እውቀትና መረጃ የሚፈልግ ሰው መጥቶ ሲጠይቃቸው ነበር የሚያስተምሩትና ጥያቄን የሚመልሱት
🔹ሴት ልጅ ሴቶችን እንኳ በአካል ለማስተማር እያለች በብዛት ከቤት መውጣት እንደሌለባት ከዘመናችን ሊቃውንቶች አልባኒን ጨምሮ ዑለሞች በግልጽ አስቀምጠዋል
🔸ሴት ወንድን ስታናግር ድምጿ የሚፈትን ከሆነ አፏ ውስጥ ድምጿ የመፈተን ኀይሉን እንዲቀንስ የሚያደርግ ነገር ማድረግ እንደሚገባትም ኢማም አን`ነወዊይ ኪታቡል አዝካር ላይ እና ሌሎችም ጠቅሰዋል!
🔹ሴት ልጅ ሐጅና ዑምራ ላይ ተልቢያ (ለብይክ... ስትል)፣ እንዲሁም ተክቢር ስታደርግ፣ ወንድ ባለበት ሰላት ስትሰግድ ድምጿን ከፍ ማድረግ እንደሌለባት መላው የዲን ሊቃውንት ዘንድ የሚታወቅ ነገር ነው
🔸ሴት ልጅ እንደ ወንድ አዛን የማትለውና ኹጥባም የማታደርገው ለዚሁ ነው!
💥ዲኑ ይህን ሁሉ ከልክሏት ሳለ ሴት ልጅ ድምጿን እያሳመረች አንዳንዴም እየሳቀችና እየቀለደች ሚዲያ ላይ ትሳተፍ ይባላልን!!?
🔹ወንድና ሴት ለሓጃ ( ለጉዳይ ወይም ለግዴታ ነገር) እንጂ መነጋገር የለባቸውም!ዝም ብሎ ያለ በቂ ምክንያት ማናገር አይገባም የተባለው ድምጿን መስማቱ የፊትና በር ስለሚከፍት ነው
🔸በተለይ ዘመናችን ፆታዊ ፈተና እጅግ በጣም የተስፋፋበት፣ ሙናፊቅና የቀልብ በሽታ ያለባቸው ሰዎችም የበዙበት ዘመን ነው
💥በእንዲህ ዓይነቱ ዘመንና ሁኔታ ላይ ሴት ልጅ በድምጽ (አልፎም በቪዲዮ) ሚዲያ ላይ ትሳተፍ ማለት የሚያስከትለውን መዘዝ ያለማስተዋል ወይም የግዴለሽነት ምልክት ነው!
🔹ሁሉንም ፆታዎች ማስተማር በመሰረቱ የወንዶች ኀላፊነት ነው ለዚህም ነው ነቢያት በሙሉ ወንዶች የነበሩት! ሆኖም ሴቶችም ለሴት ወገኖቻቸው ሸርጡ ተሟልቶ ማስተማር ይችላሉ
💥ግን ሚዲያ ላይ ወጥተው በድምጽ ያስተምሩ ጋዜጠኛ ሆነው ከወንድ ጋር ቃለ-ምልልስ ያድርጉ (አርት!) ላይ ይሳተፉ ወዘተ ማለት በነቢዩ (ﷺ)ጎዳና ላይ አንገቱን ደፍቶ የሚጓዝ ሰው አስተሳሰብ የማይቀበለው ነገር ነው!
 ኡስታዘ አሕመድ ሼኽ ኣደም
27/7/1439ዓ.ሂ@ዛዱል መዓድ

Post a Comment

0 Comments