بسم الله الرحمن الرحيم
የምርጦች ምርጥ
አሰላሙ ዐለይኩም
ነቢዩ ሙሐመድን አላህ የነቢያት መደምደሚያ ለማድረግ አጫቸው በዚህም የትልቅ መልእክትና አደራ ተሸካሚ አደረጋቸው የሰው
ልጆች ከጭለማ ወደ ብርሃን ከመሀይምነት ወደ እውቀት እንዲወጡ ነቢዩ ሙሀመድን ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በስጦታነት አበረከተላቸው
የተላኩለት ዓለማም ይሳካ ዘንድም አላህ ነቢዩን ረዳ! ሰዎች እንዲቀበሏቸውም ባማሩ ስነምግባሮች አስዋባቸው በአደብም አነጻቸው ምንም
እንኳ ወላጅ አልባ ሆነው ቢያድጉም! የእናትን ፍቅር ቢያጡም! የአባትን ርህራሄና ክብካቤ ባያገኙም ሁሉ በእጁ የሆነው ጌታ በሁለት
ወላጆቹ መሀል ካደገ ጅል የተሻለን ጥበቃ አደረገላቸው! ወላጆች ልጆቻቸውን
አደብና ስርኣትን ከሚያስተምሩት በላቀ መልኩም አላህ ቀረጻቸው! በዚህም በጊዜያቸው ከነበሩ የባለባት ልጆች ሁሉ ተሽለው ተገኙ ሁሉም
ወደዳቸው ሁሉም አቀረባቸው ሁሉም አዘነላቸው…..አቀፋቸውም እንደ ትልቅ ሰውም አከበራቸው አድገው ከትልልቅ ሰዎች ተርታ መሰለፍ ሲጀምሩም ለሀገራቸውና ህዝባቸው ትልቅን
ነገር የሚያደርጉ ሰው እንደሚሆኑ በማመን ልዩ ትኩረት ሰጧቸው አብሯቸው ያደገውን መልካም ስነምግባር የበለጠ ተጠናክሮ መቀጠሉን
በማየታቸውም "አሷዲቁል አሚን" ብለው ሰየሟቸው (ፍጹም እውነተኛውና ታማኙ ) ማለታቸው ነው ይህንን ስያሜና ከፍተኛ
ማዕረግ ያሰጣቸው ሁሉም የሚወደውና የሚመኘውን ግን ጥቂቶች እንጂ የማይታደሉትን አላህ የሚወደውን ኢስላማዊ ባህሪይ በመላበሳቸው
ነበር፥ ሲናገሩ አይዋሹም፣ ቃላቸውን አያፈርሱም፣ እንግዳን ያከብራሉ፣ዝምድናን ይቀጥላሉ፣ አቅመ ደካማን በሚችሉት ሁሉ ይረዳሉ፣
የተጣላን ያስታርቃሉ፣ ታላቃቸውን ያከብራሉ፣ በዕድሜ ለሚያንሳቸው ይራራሉ፣ ዉለታን ይመልሳሉ፣ ጉረቤትን ይንከባከባሉ፣ ከኩራት የጸዱ
ናቸው፣ የግልም ይሁን ያከባቢ ንጽህናን መጠበቅ ይወዳሉ፣ ሽቶ ያዘወትራሉ፣ የጥርስ መፋቂያ አይለያቸውም፣ ነጭ ልብስን እንደሚወዱትና
እንደሚጠቀሙት ሁሉ ልባቸውም ነጭ -ንፀህ- ነው የንፁህ ልብ ባለቤቶችንም
ይወዳሉ፣ ከጌታቸው በቀር ማንንም አይፈሩም!፣ ከመሆኑም ጋር ለወገናቸው ይተናነሳሉ፣ ማንንም አይበድሉም፣ የጌታቸው ድንበር
ካልተጣሰ በስተቀር ለራሳቸው ክብር ብለው አይቆጡም!፣ በአላህ መንገድ
እየተፋለሙ ካልሆነ በስተቀር በእጃቸው ማንንም መተው አያውቁም፣ ፍትህን ይጠብቃሉ በዚህም እንደ ሁኔታው እራሳቸውም ላይ ይፈርዳሉ!፣
ሀቅን ከመናገር ማንንም ምንንም ፈርተው ወደ ኋላ አይሉም፣ ሰውን የሚያስቀይምና ትርፍ ንግግርን አይናገሩም፣ ንግግራቸውም አጠር
ያለና ግልጽ ነው፣ ከሰዎች ጋር ሲገናኙ እንደ ደረጃቸውና እንደ ሁኔታቸው ሳይበዛ ቀልድን ይጠቀማሉ ሆኖም ግን ለቀልድ ብለው አይዋሹም!፣
ሲስቁም የሳቃቸው ድምጽ አይሰማም፣ ለመላው ፍጡር ያዝናሉ፣ አንዲት እርግብ ካጠገባቸው ዝቅ ብላ ክንፏን እያርገበገበች ስትሽከረከር፥
ማነው ልጇን የወሰደባት? ብለው ሲጠይቁ አብረዋቸው ከነበሩ ሰሃቦች መሀል አንዱ እኔ ነኝ ብሏቸው እንዲመልስላት አዘዋል፣ ህጻን
ልጅ ሲስሙ ያየ አንድ ግለሰብም፥ እኔ 9 ልጆች አሉኝ ከነሱ መሀል እስከ ዛሬ የትኛውንም ስሜ አላውቅም ሲላቸው "እዝነት
ከልብህ ወጥታ ከሄደች እኔ ምን ላደርግልህ እችላለሁ?!" በማለት ተችተዋል፣ ለአረጋዊያንና ጠዋሪ ለሌላቸው ሴቶች በተለየ
መልኩ ያዝናሉ፣ ከሁሉም በላይ የጌታቸውን መመሪያ ለሚያክብሩ የአላህ ባሪያዎች ጌታቸው ባዘዛቸው መሰረት ልዩ እዝነትና ርህራሄ አላቸው፣
ለሁሉም የሚገባውን ክብር ይሰጣሉ፣ የታመመን ይጠይቃሉ፣ የሞተን ይቀብራሉ፣ ሞተው የተቀበሩ ወንድምና እህታቸውን ቀብር በየግዜው
ሄደው እየዘየሩ ምህርት ይጠይቁላቸዋል፣ መስጅድ ታጸዳ የነበረች ሴት ሞታ እሳቸው ሳያቁ ሰሃቦች ቀብረዋት በኋላ ሲሰሙ
" ለምን ሳትነግሩኝ?! ቀብሯን አሳዩኝ በማለት ሄደው ሰግደውባት ዱኣ አድርገዋል፣ ከሰዎች የተበረከተላቸውን ስጦታ ትንሽም
ቢሆን ይቀበላሉ፣ ሲመልሱ ግን በተሻለ መልኩ ይመልሳሉ፣ ምንም የሌለው
ደሃ እንኳ ቢሆን ጥሪን አክብረው ይሄዳሉ፣ሰውን ስያገኙ ቀድመው ሰላም ይላሉ፣ ሀብታሙንም ደሃውንም ይጨብጣሉ፣ ህጻናትን ያጫውታሉ
ታፋቸው ላይ በማስቀመጥም ያቅፋሉ፣ ከሰሃቦቻቸው ጋር በመሆንም እነሱ የሚሰሩትን ስራ አብረው ይሰራሉ፣ ምግብም አብረዋቸው ይበላሉ፣
ከእለታት አንድ ቀን አይቷቸው የማያውቅ ግለሰብ ወዳሉበት ደርሶ ከቅርበት ሲያያቸው ከነበራቸው ግርማ ሞገስ የተነሳ ሰውነቱ ሲንቀጠቀጥ
አይተው " እራስህን አረጋጋ እኔ እኮ የአንዲት ስጋን አድርቃ እያቆየች ትበላ ከነበረች ሴት የተወለድኩ ሰው ነኝ"
በማለት አረጋግተውታል፣ ከሰሃቦቻቸው ጋር ጉዞ ላይ ሳሉ በግ ማረድ ፈልገው ከነሱ መሀል አንዱ፥ እኔ አርዳለሁ ሲል ሌላኛው እኔ
እገፋለሁ እያለ ሌላኛው ደግሞ እኔ አበስላለሁ በሚልበት ሰኣት ታላቁ ሰው (ነቢዩ ሙሐመድ ሰለላሁ ዐለይሂወሰለም) እኔ ደግሞ እንጨት ለቅሜ አመጣለሁ ብለው እራሳቸውን ዝቅ አድርገዋል!!
በለዚህም አላህ ዘንድ ከፍ ብለዋል አማኞች ልብ ላይም ውዴታቸውን ዘርተዋል የሰው ልጆች ምርጥ እንደሆኑ፥ የሩቁም የቅርቡም፣ወዳጅ ዘመዱም መስክሯል
እነሆ እኚህ ናቸው ነቢያችን እንወዳቸዋለን! እናከብራቸዋለን! የሙስሊሞች አርኣያና ተምሳሌትም እሳቸው ናቸው
አላህ ሆይ፥ በፈጠርካቸው ነገሮች ልክ ነቢዩ ሙሀመድ ላይ ሰላትና ሰላምን አስፍን!
ወሰላሙ ዐለይኩም ወረህመቱላህ
አሕመድ ኣደም 21/4/1436