#ምነው_እሱን_ብቻ!!
እባካችሁ ወንዶች አደብ ይኑራችሁ
እንዲህ አታድርጉ እንዲህ እያላችሁ
ሴቶች ተበደልን ውስጣችን ተከፋ
የወንዶቹ ነገር መላ ቅጡ ጠፋ
•
መሰል ዝባዝንኬ ክስ ቀንሺና
እራስሽን ጠይቂ አንዴ መልሺና
•
ያኔ ከጠዋቱ ጨዋታው አፍዝዞሽ
ስታወሪው ነበር በቻት ፍቅር ይዞሽ
ቀኑ ተቀይሮ ላሽ ቢል አጅሬ
ተበደልኩኝ ብለሽ ትጮሂያለሽ ዛሬ??
•
ገና አ…ንድ በሎ ጅንጀናው ሲጀመር
ወሬው ተንሸራትቶ ሲወጣ ከመስመር
አደብ አልባ ሲኮን ሲታለፍ ከድንበር
ለምን ከጥንስሱ አላቆምሽም ነበር??
•
ከሄደ በሗላ ዉሻው ቢጮህ ደርሶ
ጅቡ እንደሁ እርቋል አይመጣ መልሶ
ምን ያደርግልሻል ዛሬ ብትወቅሺው
ግዜን ወደሗላ ስበሽ ላትመልሺው
•
ሰዉዬው ብቻውን ባላጠፋው ጥፋት
አንቺ ንፁህ ሆነሽ ጎልቶ የሱ ክፋት
ሀስቢየላህ እያልሽ ‘ምታማርሪበት
እርግማን ከዛቻ የምታዘንቢበት
ጉዳዩ ላይኮ ያንቺም እጅ አለበት!!!
ባይሆን ክትናንቱ ትምህርት ዉሰጂና
ዳግም እጅ አትስጪ ለ facebook ጅንጀና!!
•••√√√••••√√√••••√√√••••
እንዲህ አታድርጉ እንዲህ እያላችሁ
ሴቶች ተበደልን ውስጣችን ተከፋ
የወንዶቹ ነገር መላ ቅጡ ጠፋ
•
መሰል ዝባዝንኬ ክስ ቀንሺና
እራስሽን ጠይቂ አንዴ መልሺና
•
ያኔ ከጠዋቱ ጨዋታው አፍዝዞሽ
ስታወሪው ነበር በቻት ፍቅር ይዞሽ
ቀኑ ተቀይሮ ላሽ ቢል አጅሬ
ተበደልኩኝ ብለሽ ትጮሂያለሽ ዛሬ??
•
ገና አ…ንድ በሎ ጅንጀናው ሲጀመር
ወሬው ተንሸራትቶ ሲወጣ ከመስመር
አደብ አልባ ሲኮን ሲታለፍ ከድንበር
ለምን ከጥንስሱ አላቆምሽም ነበር??
•
ከሄደ በሗላ ዉሻው ቢጮህ ደርሶ
ጅቡ እንደሁ እርቋል አይመጣ መልሶ
ምን ያደርግልሻል ዛሬ ብትወቅሺው
ግዜን ወደሗላ ስበሽ ላትመልሺው
•
ሰዉዬው ብቻውን ባላጠፋው ጥፋት
አንቺ ንፁህ ሆነሽ ጎልቶ የሱ ክፋት
ሀስቢየላህ እያልሽ ‘ምታማርሪበት
እርግማን ከዛቻ የምታዘንቢበት
ጉዳዩ ላይኮ ያንቺም እጅ አለበት!!!
ባይሆን ክትናንቱ ትምህርት ዉሰጂና
ዳግም እጅ አትስጪ ለ facebook ጅንጀና!!
•••√√√••••√√√••••√√√••••