ስለ ታላቁ ሰሐቢ ጁለይቢብ ረዲየላሁ ዐንሁ መነበብ ያለበት ድንቅ ታሪክ
የታሪክ መዛግብት እንዳሰፈሩት ጁለይቢብ ረዲየላሁ ዐንሁ
- ቁመቱ አጭር
- መልከ ጥፉ
- ዘሩ የማይታወቅ
- ቤተሰቦቹ ማን እንደነበሩ ማንም የማያውቅ
- ከለላ የሚሰጠው ምንም ጎሳ የሌለው
- የትኛውም ጎሳ “የኛ ነው” ብሎ ያላስጠጋው
- የመዲና ህፃናት እንኳን የሚያሾፉበትና የሚቀልዱበት ባይተዋርነት ያጠቃውና ብቸኛ … ወዘተ …
ከላይ በተገለፁት ሁሉ ወዶና መርጦ ባላመጣው “ፍዳ” አማኻኝነት ማንም ከርሱ ጋር መቀማመጥን የማይመርጥ
ምስኪን ሰው ነበር።
የተቻለውን ሁሉ ጥረት አድርጓል። ነገር ግን ህዝቡ ዘንድ ተቀባይነት ለማግኘት የፈየደለት አንዳችም ነገር አልነበረም። በርካታ የብቸኝነትና የባይተዋርነት ሌሊቶችን የመዲና ጎዳናዎችን በተስፋ መቁረጥ እየተመለከተ አሳልፏል። በማንነቱ እየተገፋ የመኖር ህይወት ውስጥ የጁለይቢብ ጉንጮች ላይ እንባዎች ሲፈሱ ኖረዋል። አብሮት የሚያኗኑረው አንድም ወዳጅ ሊያገኝ አልተቻለውም። ፍቅርን ተርቦ፣ እንክብካቤን ተነፍጎ ለዘመናት አሳልፏል። ያለ አንድም የቤተሰብ አካል፣ ያለ አንድም ወዳጅ ! ረዲየላሁ ዐንሁ
በአጠቃላይ ህይወት ለርሱ የብቸኝነት ትግል ነበር!
ረሱል ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ወደ መዲና ሂጅራ አድርገው ከመጡ በኋላ የጁለይቢብ እጣፈንታ ተቀየረ።
ወደሳቸው በመሄድ አብሯቸው ይቀመጥና የሚሉትንም በጥሞና ያደምጥ ይከታተል ጀመር። በእፍረት አንገቱን ይዘቀዝቅ ነበር እንጂ ከጥቂት ቃላቶች በቀር አንዳችም አይተነፍስም ነበር።
አሁን ላይ የጓደኞች ሁሉ ምርጥ ጓደኛ ረሱል ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለምን አግኝቷል። ያ የብቸኝነት ዘመን! ያ የባይተዋርነት ጊዜ! በሰዎች ሁሉ ምርጥ በሆኑት የአላህ መልእክተኛ ወዳጅነት ተቀርፏል።
ጁለይቢብ አሁን ከአማኞች ጋር በመሆን የህብረተሰቡ አንድ ክፍል ሆኗል።
ከእለታት አንድ ቀን ጁለይቢብ ከረሱል ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ጋር በተቀማመጠበት የአላህ መልእክተኛ አንድ ጥያቄ ይጠይቁታል። እንዲህም ብለው ፦ «ጁለይቢብ ሆይ ያሻህን ጠይቅ! የምትፈልገው ነገር ይኖርሃልን?»
ጁለይቢብም አንገቱን በዝግታ ቀና በማድረግ በእፍረት ድምፅ ፦ «አንቱ የአላህ መልእክተኛ ሆይ! አላህ የርሶን ወዳጅነት አድሎኛል። ከእግሮት ግርጌ ቁጭ እላለሁ፤ የሚናገሩትንም የተቀደሰ ንግግር አደምጣለሁ፤ ከዚህ በላይ ምን እፈለጋለሁ? » አላቸው
የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም አስከትለው፡ «ውዴ ጁለይቢብ ሆይ! በምን አይነት መልኩ ማግባት (ጋብቻ) ትፈልጋለህን?» ሲሉት ጁለይቢብም እኔን ሊያገባኝ የሚችል ከቶ ከየት ይገኛል? በሚል የእፍረት ፈገግታ እየፈገገ «አዎን የአላህ መልእክተኛ ሆይ (ማግባት) እፈልጋለሁ።» አላቸው።
የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ወደ አንድ አንሷር የታወቀና የተከበረ ሰሓቢ ቤት ሄዱ።
እናም እንዲህ አሉ ፦ «የመጣሁት ልጃችሁን ለጋብቻ ልጠይቅ ነው። »
ሰሐቢዩም ፡ «የአላህ መልእክተኛ ሆይ! ከዚህ በላይ ከዚህ በላይ የተቀደሰ ነገር ምን ይኖራል?» አላቸው።
ረሱል ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለምም ፡ «የጠየቅኩት ለራሴ ሳይሆን ለጁለይቢብ ነው።» አሉት
ሰሓቢዩ በድንጋጤ «ለጁለይቢብ?» አለ። «አዎን ለጁለይቢብ» አሉት ረሱል ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም።
«እስኪ ባለቤቴን አማክሬ ልምጣ» አላቸውና ወደ ባለቤቱ ሄዶ ፡ «የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ልጅሽን ለትዳር ጠይቀዋላታል። ለርሳቸው ግን አይደለም። ለጁለይቢብ ነው።» አላት።
ማልቀስና ማጉተምተም ጀመረች። «ለጁለይቢብ አይሆንም በጭራሽ! ይህንንማ አልፈቅድም።» አለቻቸው።
ይህንን ግርግር ልጅቱ በሰማች ጊዜ መጣች። እንደሚባለው ልጅቱ በጣም ቆንጆ እና የአንሷር ሴቶች የማይወዳደሯት ውብ እንስት ነበረች።
“አይናፋር ፣ ጥብቅና ሰማይ እንኳን ራሷን ሳትሸፈን ያላያት” የሚባልላት ሴት ነበረች። በጣም ዓቢዳህ የነብረች ስትሆን ቀንና ሌሊቱን አላህን በመገዛት የምታሳልፍ ነበረች።
ምን እንደተፈጠረ ጠየቀች። የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ለጁለይቢብ አጭተዋት ሽምግልና እንደመጡ ተነገራት።
እናቷ እያለቀሰች እያጉተመተመች ባየቻት ጊዜ «እማዬ ይሆይ በምትናገሪው ነገር ላይ አላህን ፍሪ። የአላህ መልእክተኛ ላይ ፊትሽን ታዞሪያለሽን? እማዬ ሆይ! በአንድ ጉዳይ ላይ የአላህ መልእክተኛ ከወሰኑ በኋላ የራስን ውሳኔ ማስተላለፍ በአንድ አማኝ ላይ የተገባ አይደለም።
የአላህ መልእክተኛ ሰላላሁ ዐለይሂ ወሰለም ክብራችንን የሚቀንሱ ይመስልሻልን?
ጁለይቢብ ምን ያህል የተቀደሰ ቢሆን ነው። አላህ እና የርሱ መልእክተኛ ልጃችሁን ለትዳር የሚጠይቁለት?
አላህ እና መልእክተኛው ዘንድ ተወዳጅ የሆነ ሰው እግር ስር ያለውን አፈር እንኳን (ለመሆን) መላኢካዎች ሳይቀር እንደሚመኙ አታውቁም ኖሯልን?
ጁለይቢብን ወደኔ ይልኩት ዘንድ የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለምን ንገሩልኝ። በርግጥም ይህን የመሰለ ባል ከማግኘት በላይ የተቀደሰ ነገር የለም። የአላህ መልእክተኛ ይሄን ያህል ስጦታ ይዘውልን መጥተው እናቴ ግን ታለቅሳለች ብሎም ታጉረመርማለችን?» አለች።
እናቷም የልጅቱን ንግግር በሰማች ጊዜ ፡ «በቃሽ የኔ ልጅ! ሌላን ቃል አትጨምሪ። በርግጥም አጥፍቻለሁ ተፀፅቻለሁም። ንስሃም አድርጌያለሁ። አንድ ሺህ ጊዜ ንስሃ ገብቻለሁ። በዚህም ቅፅበት ለአንቺ ከጁለይቢብ የበለጠ የምመርጥልሽ ማንም የለም። » አለች
በቀጣዩም ቀን ኒካው ተፈፀመ።
ዑሥማንና ዐሊይ ረዲየላሁ ዐንሁም ለጁለይቢብ ወሊማ እና ለወጪዎቹ ይሆን ዘንድ ገንዘብ በስጦታ መልክ አበረከቱለት።
ጁለይቢብ ጋብቻ በፈፀመ ከጥቂት ቀናት በኋላ ጂሃድ ላይ ተሰዋ። ረዲየላሁ ዐንሁ
የተሰዋበት እለት ወደ ጂሃድ ሲወጣ አማቹ እንዲህ ሲል ወደ ጂሃድ እንዳይወጣ ተማፅኖት ነበር። «ጁለይቢብ ሆይ! ይህ ጂሃድ እንዲሁ ዘመቻ ነው። ይሄ የውዴታ ዘመቻ እንጂ የግዴታ አይደለም። አንተ ደግሞ አዲስ ሙሽራ ነህና(የጫጉላ ጊዜህን)ከሚስትህ ጋር አሳልፍ።»
በርካታ የባይተዋርነት ዘመን አሳልፎ በመጨረሻም ከአፍቃሪ ሚስት ጋር ትዳር አላህ የሰጠው ጁለይቢብ ግን ለአማቹ የሰጠው መልስ የሚደንቅ ነበር። «አባቴ ሆይ! እንግዳ የሆነ ንግግርን ተናገርክ። ውዴ የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከጠላት ፊት ዘመቻ ላይ ሆነው ከኢስላም ጠላቶች ጋር እየተጋፈጡ ሳለ እኔን ከሚስቴ ጋር ቤት ቁጭ በል ትለኛለህን? በጭራሽ! ደሜንንና ነፍሴን መስእዋት አደርጋለሁ እንጂ የአላህ መልእክተኛ ባሉበት ችግር ውስጥ ሆነው እኔ ቤቴ በቅንጦት ቁጭ አልልም።» አለ።
ጁለይቢብ ከቁመቱ ጋር የሚስተካከል ጦር ታጥቆ ማየት በርግጥም እንግዳ ነገር ነበር።
ቆፍጣናው ጁለይቢብ ድንገት ወደ አንበሳ የመቀየሩ ሂደት በርግትም ሶሓቦችን አስገርሟል።
«ማነው ደፋሩ የአላህ መልእክተኛ ላይ ጦር የሚያውጅ!?» እያለ ይፎክር ነበር።
ጦርነቱ እንደተገባደደ የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሶሓቦች ከቤተሰባቸውና ከጎሳቸው የተሰው ሰዎችን ጀናኢዛ እንዲፈልጉ ዘምቻው ወደ ተካሄደበት ቦታ ላኳቸው። ሁሉም ከየቤተሰባቸውና ከየጎሳቸው የሞቱባቸውን ሰዎች ቆጥረው ተመለሱ። የአላህ መልእክተኛ ግን አይናቸው እንባ አዝሎ «እኔ ግን ውዴ ጁለይቢብን አጥቼዋለሁ። ሂዱና ፈልጉት» አሏቸው።
ሄደው በፈለጉትም ጊዜ ሰባት ኩፋሮች ሬሳ መካከል ወድቆ ያገኙታል። (ሰባት ገድሎ እርሱም ተሰዋ)
የአላህ መልእክተኛ ሰላላሁ ዐለይሂ ወሰለም ቀብር እንዲቆፈርለት አዘዙና የጁለይቢብ ረዲየላሁ ዐንሁን ሬሳ ይዘው፡
« እርሱም ከኔ ነው። እኔም ከርሱ ነኝ።» አሉና ይህንን ሶስት ጊዜ ደጋገሙት።
ሶሓቦች ስቅስቅ ብለው እያለቀሱ ፡ «ጁለይቢብ ሆይ! አባቶቻችን እና እናቶቻችን ፊዳ ይሁኑልህ! ደረጃህ ምን ያህል ከፍ ያለ ነው አሉ። » ይሉ ነበር።
ይህ ነበር ጁለይቢብ! በርካታ የብቸኝነት ዘመናትን እንዳላሳለፈ የሰዎች ምርጥ የሆኑትን የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለምን ወዳጅነት ታደለ። በህብረተሰቡ እንዳልተገፋ በሶሓቦች አንደበት ከፍ ተደረገ። ውጫዊ ገፅታው መልከ ጥፉ እንዳልነበር ቆንጆ፣ ውብ የሆነች ሚስትን ሲሳይ ከአላህ ተለገሰ። ዘሩ የተቆረጠ እንዳልነበር የተከበረ የአንሷር ቤተ ሰብ ዝምድናን አገኘ። ከሁሉም በላይ ግን የአላህን እና የመልእክተኛውን ውዴታ ተጎናፀፈ።
በአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም አንደበት እርሱም የኔ ነው እኔም የርሱ ነኝ ተባለ።
የአላህ እና የመልእከተኛው ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ውዴታ ደረጃው ይህን ያህል ነው።
ከላይ በተጠቀሱት ስብእናዎች ውስጥ ራሳችንን እየተካን ነፍሳችንን እንፈት ሽ። ባርከላሁ ፊኩም
[ምንጭ፥ ሙስሊም, እና የተለያዩ የታሪክ መዛግብት እንደዘገቡት]
አላህ የርሱን እና የመልእክተኛውን ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ውዴታ ያድለን