Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ስለ ዓረፋ ቀን ዱዓእ ሁለት ነጥቦች


ስለ ዓረፋ ቀን ዱዓእ ሁለት ነጥቦች

[1] በኢድ ዋዜማው የዓረፋ እለት ዱዓእ ተቀባይነት እንዳለው የሚዘክሩ ሀዲሶች ሀጅ ላይ የሌሉ ሰዎችንም ይመለከታሉን??

የአላህ መልእክተኛ «ከዱዓዎች ሁሉ በላጩ (የኢድ ዋዜማ) የአረፋ ቀን ዱዓ ነው...» ማለታቸውን ቲርሚዚይ ከአብዱላህ ኢብኑ ኡመር የዘገቡ ሲሆን፤ ሌሎች ተመሳይ ይዘት ያላቸው ሀዲሶችም ይገኛሉ።


ታዲያ የዓረፋን እለት በዱአዕና በዚክር ያሳለፈ ሰው ታላቅ ክብርና ምንዳን የሚያገኘው ሀጅ ላይ ሲሆን ብቻ ነውን? በእርግጥ በዚህ እለት ክብር ባለው የዓረፋ ምድር የተገኘ ሰው የጊዜንም የቦታንም ክብር ተጎናፅፏልና በተሻለ ሁኔታ ላይ መገኘቱ እንዲሁም ዱአው ተቀባይነት ለማግኘት የቀረበ መሆኑ አያጠራጥርም። ይሁንና ሚዛን በሚደፋው የኡለማዎች አቋም መሰረት፤ እነዚህ ከአረፋ እለት ክብር ጋር ተያይዞ የዱአ ተቀባይነትን የተመለከቱ ሀዲሶች በማንኛውም ቦታ የሚገኙ ሙስሊሞችን ይመለከታሉ። በመሆኑም በሀጅ ስራ ላይ የሌሉ ሰዎችም በዱዓ ሊበረቱ ይገባል።

ታላቁ አሊም ሸይኽ ሳሊህ አልፈውዛን በዚህ እለት የሚባሉ በሀዲስ የተላለፉ ዱአዎችን አስመልክቶ ሀጅ ላይ ላሉ ሰዎች መሆኑን ተጠይቀው ተከተዩን መልሰዋል¹
«በምላሻችን እንደገለፅነው፤ ይህ ለሁጃጆችንም ይሁን ሌሎችን የተመለከተ ጥቅል መልእክት ነው። ነገር ግን ሀጅ ላይ ላሉ ሰዎች ይበልጥ የተገባ ነው። ምክኒያቱም ሁጃጆች በዚህ እለት በዓረፋ ምድር በኢህራም ውስጥ ስለሚገኙ ከሌሎች በበለጠ ዱዓቸው ተቀባይነት ለማግኘት የቀረበ ነው። ስለዚህም የዓረፋን እለት በሀጅ ተግባር ላይ የሌሉ ሰዎች እንዲፆሙት ተደንግጓል። እለቱ ብልጫ ያለወወ ስለሆነም አላህን በማስታወስ፣ ማርታን በመለመን እና ዱዓ በማድረግ ጊዜያቸውን ያሳልፋሉ፤ ሁጃጆችንም በኢባዳ ይካፈሏቸዋል ማለት ነው።» ከሸይኹ ድረገፅ የተወሰደ የድምፅ ፈትዋ

[2] በዓረፋ እለት ሁጃጆች በአረፋ ምድር እንደሚሰባሰቡት ለዱዓና ለዚክር መሰባሰብ "ታዕሪፍ"ን በተመለከተ፤

ይህ ተግባር አንዳንድ ሰለፎች እንደፈፀሙት የተረጋገጠ ነው። ከነሱም መካከል ኢብኑ አባስ ይገኙበታል፤ ኢማሙ አህመድም ባይተገብሩትም እንደሚቻል ተናግረዋል።
ነገር ግን ያወገዙትና ከቢድአ የመደቡትም አሉ። የኡለማዎቻችንን ማብራሪያዎች ስንፈትሽ ተከታዮቹ ድምዳሜዎች ላይ ያደርሱናል፤

1) "ታእሪፍ"ን መተግበር በራሱ ችግር የለውም። ተግባሩን እንደሱና ወይም ሙስተሀብ ነገር መውሰድ ግን አይገባም። ጉዳዩ የኢጅቲሀድ መስአላ ነውና ተግባሩ የሚወገዝ ተግባር አይሆንም። የፈፀመውም ሰው ቢድአ ሰራ አይባልም።

2) ታእሪፍ ስንል ከምድረ አረፋ ውጭ ባሉ የየሀገሩና የየከማው መስጂዶች መሰባሰብን የተመለከተ እነጂ ለዚህ ብሎ ጉዞ ማድረግ አይፈቀድም። አላህ የአረፋን ምድር ለዚህ ቀን ኢባዳ መሰባሰቢያ እንደመረጠው በየሀገሩ አንዳንድ ቦታዎችን፣ መስጅዶችንና ቀብሮችን በመምረጥ ወደነሱ ጉዞ አድርጎ መሰባሰብ በፍፁም አይፈቀድም። ይህ የነብዩ መስጂድንም ይሁን በይተልመቅዲስን ያካትታል።

3) ይህ መሰባሰብ ጩኸትና ሱና ያልሆኑ የጋራ አምልኮዎች ከታከሉበት ቢድአ እንደሚሆን አያጠራጥርም። በተመሳሳይ መልኩ ኢባዳ ያልሆኑ ግጥሞችና መንዙማዎችን ለዚህ መለያ ማድረግ ጥፋት ነው።

እነዚህን ነጥቦች በዝርዝር ለመረዳት የሚያስችሉ ማብራሪያዎችን ከኡለማዎች ድርሳናት እንደሚከተለው እናያለን።

☞ ታላቁ የፊቅህ ሰው ኢብኑ ቁዳማህ ተከታዩን አስፍረዋል² «አልቃዲ ኢያድ እንዳሉት የአረፋ እለት አመሻሹን ከአረፋ ክልል ውጪ ባሉ ቦታዎች ለዱዓ መሰባሰብ "ታእሪፍ" ችግር የለውም። አል አስረም እንዳሉት፤ አቡ አብዲላህ አል ኢማም አህመድን በአረፋ እለት በመስጂዶች መሰባሰብ "ታእሪፍን" አስመልክቶ ጠይቄያቸው "አንዳንዶች ፈፅመውታልና ችግር እንደማይኖረው ተስፋ አደርጋለው።" በማለት መለሱልኝ። እንደዚሁ ከሀሰን ባስተላለፉት ዘገባ በኢራቅ በስራህ ለመጀመሪያ ጊዜ ታእሪፍን የተገበሩት ኢብኑ አባስና ዓምር ኢብኑ ሁረይስ ነበሩ። እንደዚሁ በክር፣ ሳቢትና ሙሀመድ ቢን ዋሲዕ መስጂዶችን ይታደሙ ነበር። አል ኢማም አህመድ "ችግር የለውም፤ ዱዓእና አላህን ማስታወስ ነው" ሲሉ አርሶ ይፈፅሙታልን? ተብለው ተጠየቁ። እሳቸውም፤ እኔን በተመለከተ "አልፈፅመውም" በማለት መለሱ። የህያ ኢብኑ ሙዒንም እንዲህ አይነቱን መጅሊስ በመስጂድ እንደታደሙ ተዘግቧል። » አል ሙግኒ 2/129


አል ኢማም ኢብኑ ተይሚያህ በተለያዩ ፅሁፎቻቸው ስለነዚህ ጉዳዮች ጥልቅ ማብራሪያዎችን አስፍረዋል።

☞ በመጅሙእ አልፈታዋ 1/282 በተካተተው "ቃኢዳህ ጀሊላህ ፊትዐተወሱል ወልወሲላህ" በተሰኘው ፅሁፋቸው³ ባሰፈሩት መልእክት፤ በአረፋ እለት ኢብኑ አባስ በበስራ እንዲሁም ዓምር ቢን ሁረይስ በኩፋ ታእሪፍ ማድረጋቸው በሌሎች ሰሀቦች የሚተገበር አልነበረምና የተወደደ ሱና ነው ለማለት አያስችለንም። ምናልባት የምንለው፤ የኢጅቲሀድ አጀንዳ ነውና የሚተገብረው ሰው አይወገዝም ነው። በጥቅሉ "ታእሪፍ" ልክ እንደ ሱና ካልተወሰደ ቢተገበር ችግር የለውም። ይህም የታላላቅ ኡለማዎችና አኢማዎች ግንዛቤና አቋም ነው። እንደሁኔታው አንዳንድ ጊዜ መክሩህ ያደርጉታል አንዳንዴም ይፈቅዱታል። ቋሚ ሱና ተደርጎ ካልተያዘ ችግር የለውም።

☞ ጃሚኡል መሳኢል 5/364 ላይ በተካተተው
መሳኢል ፊል ሙራበጧቲ ቢስ'ሱጉር ወይም
ድንበሮችን መጠበቅን የተመለከቱ አጀንዳዎችን በሚዳስሰው ፅሁፋቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ፤⁴

ድንበርን ከጠላት ጥቃት ለመጠበቅ የሚደረግ ጉዞን ከጠቀሱ በኃላ፤ አንዳንድ ሰዎች እንደዚህ አይነት የተደነገጉላቸውን ኢባዳዎች በመፈፀም ፈንታ ያልተደነገጉ ጉዞዎችን እንደሚያደርጉ ገልፀዋፀዋል። በምሳሌነትም፤ በአረፋ ቀን ተሰባስበው ዱአ ለማድረግ "ታእሪፍ" ካሉበት ሀገር ተነስተው በይተል መቅዲስ መሄዳቸውን ኮንነዋል። ለዚህም ምክኒያቱን ሲገልፁ፤

1) የአረፋን እለት "ታእሪፍ" በማድረግ በይተልመቅዲስ ማሳለፍ ዋጂብም ይሁን የተወደደ ሙስተሀብ አለመሆኑ የሙስሊሞች ሁሉ ስምምነት ኢጅማእ በመሆኑ ለዚህ ቀን ወደ በይተልመቅዲስ ጉዞ ማድረግና ከሌሎች መስጂዶች በተለየ መልኩ ወደ አላህ ያቃርባል ብሎ ማሰብ ጥመት ነው።

2) በሀጅ ወቅት ጉዞ በማድረግ በይተልመቅዲስን እንደ አረፋ ምድር መመልከትና "ታእሪፍ" ማድረግ ጥመት በመሆኑ ይከለከላል። ታእሪፍ ለማድረግ ጉዞ የሚደረገው ወደ አረፋ ምድር ብቻ ነው።

አክለውም ወደ ነብያትና ሷሊሆች ወይም አህልበይት ቀብር ጉዞ በማድረግ መሰባሰብ እንኳን እንደ አረፋ ምድር መቁጠርና "ታእሪፍ" ታክሎበት ይቅርና ከታእሪፍ ውጭም ቢሆን ወደነዚህ ቦታዎች ጉዞ ማድረግ ከባድ ጥመት መሆኑ የሙስሊሞች ሁሉ ስምምነት እንዳለበት አብራርተዋል።

☞ ኢቅቲዷኡሲራጥ አልሙስተቂም በተሰኘው መፅሀፋቸው ቅፅ 2 ገፅ 149 ላይ በዚህ እለት የሚፈፀሙ ጥፋቶችን የዘረዘሩ ሲሆን በተለይም፤⑤
– ይህንን የተከበረ ቀን የተከበረ ቦታ ማሳለፍ ከሚለው መነሻ ወደ አንዳነድ ቀብሮች በመጓዝ የአረፋን ማሳለፍ ሰየተከለከለ ሲሆን የቢድአ ሀጅ ነው። ኢስላማዊዉን የሀጅ ክንዋኔም መፎካከር ነው ብለዋል።

– ለመስገድና ኢእቲካፍ ለማድረግ ወደ በይተል መቅዲስ ጉዞ ማድረግ የተወደደ ነው፤ ነገር ግን በሀጅ ቀናት ወደዛ፣መጓዝ ነው የተጠላው። ለበይተልመቅዲስ ዚያራ ጊዜን መገደብ አይፈቀድም። ይህ ሀጅን መፎካከርና በካእባ ጋር ማመሰል ነው። ብዙ ስህተትንም አስከትሏል፤ ለምሳሌ በይተልመቅዲስ የሚገኘውን ቋጥኝ ጠዋፍ ማድረግና አንዳነድ የሀጅ ተግባራትን መፈፀም ተስተዉሏል። ይህ ደግሞ ጥመት መሆኑን ገልፀዋል።

– በመስጂደል አቅሷ ከበሮ እየደበደቡ ነሺዳ ማለትን በተመለከተም ከከባባድ ጥፋቶች መሆኑን ጠቁመዋል። በሌላ መስጅዶችም የማይፈቀድን ነገር በተከበረው መስጂድ መፈፀም፣ በተከበረ ወቅት መሆኑና ባጢልን ዲን አድርጎ መቁጠር ጥፋቱን ይበልጥ እንደሚያጎሉት ተናግረዋል።

ኢብኑ ተይሚያህ ከዚህ በመቀጠል ያሰፈሩት ግልፅና ድንቅ ማብራሪያ ስለሆነ እንደመደምደሚያ በመውሰድ ቀጥተኛ ትርጉሙን አሰፍርና የዚህ ፅሁፍ መደምደሚያ ይሆናል፤

فأما قصد الرجل مسجد بلده يوم عرفة للدعاء والذكر فهذا هو التعريف في الأمصار الذي اختلف العلماء فيه، ففعله ابن عباس، وعمرو بن حريث من الصحابة وطائفة من البصريين والمدنيين، ورخص فيه أحمد، وإن كان مع ذلك لا يستحبه، هذا هو المشهور عنه.


وكرهه طائفة من الكوفيين والمدنيين: كإبراهيم النخعي وأبي حنيفة ومالك، وغيرهم. ومن كرهه قال: هو من البدع، فيندرج في العموم لفظا ومعنى.

ومن رخص فيه قال: فعله ابن عباس بالبصرة حين كان خليفة لعلي بن أبي طالب رضي الله عنهما، ولم ينكر عليه، وما يفعل في عهد الخلفاء الراشدين من غير إنكار لا يكون بدعة...

والفرق بين هذا التعريف المختلف فيه وتلك التعريفات التي لم يختلف فيها: أن في تلك قصد بقعة بعينها للتعريف فيها: كقبر الصالح، أو كالمسجد الأقصى، وهذا تشبيه بعرفات، بخلاف مسجد المصر، فإنه قصد له بنوعه لا بعينه، ونوع المساجد مما شرع قصدها، فإن الآتي إلى المسجد ليس قصده مكانا معينا لا يتبدل اسمه وحكمه، وإنما الغرض بيت من بيوت الله، بحيث لو حول ذلك المسجد لتحول حكمه، ولهذا لا تتعلق القلوب إلا بنوع المسجد لا بخصوصه.
وأيضًا، فإن شد الرحال إلى مكان للتعريف فيه، مثل الحج، بخلاف المصر، ألا ترى أن النبي صلى الله عليه وسلم قال: «لا تشد الرحال إلا إلى ثلاثة مساجد: المسجد الحرام، والمسجد الأقصى، ومسجدي هذا». هذا مما لا أعلم فيه خلافا. فقد نهى النبي صلى الله عليه وسلم عن السفر إلى غير المساجد الثلاثة، ومعلوم أن إتيان الرجل مسجد مصره: إما واجب كالجمعة، وإما مستحب كالاعتكاف به.

وأيضا فإن التعريف عند القبر اتخاذ له عيدا، وهذا بنفسه محرم، سواء كان فيه شد للرحل، أو لم يكن، وسواء كان في يوم عرفة أو في غيره، وهو من الأعياد المكانية مع الزمانية». اهـ.

«አንድ ሰው በአረፋ እለት በሀገሩ ከሚገኙ መስጂዶች ወደ አንዱ ለዱአና ዚክር መሄዱ "ታእሪፍ ፊል አምሷር" የምንለው ይህ ሲሆን፤ ኡለማዎች ተወዛግበውበታል። ከሰሀቦች ኢብኑ አባስ ና አምር ቢን ሁረይስ ሲተገብሩት ከመዲናም ይሁን ከበስራ ብዙ ሰዎች ፈፅመውታል። አል ኢማም አህመድ ዘንድ የተወደደ ባይሆንም ፈቅደውታል። ስለሳቸው በጣም የታወቀው መረጃ ይኸው ነው።

በሌላ በኩል እንደ ኢብራሂም አን’ነኸኢይ፣ አቡ ሀኒፋ እና ማሊክ ያሉ ብዙ የኩፋና የመዲና ኡለማዎችም ጠልተውታል። ያልወደዱት፤ ከቢድዓ ተግባር ይቆጠራል ብለዋል። ይፈቀዳል ያሉት ደግሞ፤ ኢብኑ አባስ በአሊይ ኢብኑ አቢ ጧሊብ በበስራ ተሹመው በነበረበት ወቅት ፈፅመውት ነበር። ማንም ሰው ስራቸውን አላወገዘውም። ቅን የሆኑት ተተኪ ኹለፋኦች በነበሩበት ዘመን ተተግብሮ ካለ ተቃውሞ ያለፈ ነገር ደግሞ ቢድአ አይባልም።

(ቦታ ለይቶና ጉዞ አድርጎ በሚደረገው) ለመከልከሉ ምንም አይነት ውዝግብ በሌለበት ታእሪፍና ኺላፍ ባለበት ታእሪፍ መካከል ያለው ልዩነት፤

– የተከለከለው ታእሪፍ፤ እንደ አል አቅሷ መስጂድ ወይም የቅዱስ ሰው የቀብር ቦታን ታእሪፍ ለማድረጊያነት ለይተው ማሰባቸው ሲሆን ይህም ከቅዱሱ ምድረ አረፋ
ጋር ማመሳሰል ይሆናል።

– በተቃራኒው ታእሪፍን በማሰብ ወደ ማንኛውም የሀገሩ መስጂድ የሚሄደው ሰው ያንን ቦታ የመረጠው በመስጂድነቱ ስለሆነ የአይነት ምርጫ እንጂ የቦታ ምርጫ ውስጥ አልገባም። መስጂዶች ሁሉ ደግሞ ኢባዳ የተደነገገባቸው ቦታዎች ናቸው። ወደ መስጂድ የሚመጣው ሰው ከአላህ ቤቶች አንዱን በማሰብ መስጅድነቱን ከጅሎ እንጂ ልቡ ከቦታው ጋር አልተሳሰረም። ለምሳሌ የመስጅዱ ቦታ ቢቀየር እርሱም ይቀይራል። ስለዚህም ነው በመስጅድነቱ ለኢባዳ ሄደ እንጂ የተለየ ስለመሆኑ እምነት አድሮበት አይደለም የምንለው።

– እንደዚሁ፤ ጓዝን ጠቅልሎ ለታእሪፍ ወደሌላ ቦታ መጓዝ ልክ እንደ ሀጅ መቁጠር ይሆናል። የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ምን እንዳሉ አስተውል፤ «ወደ ሶስት መስጅዶች ካልሆነ በቀር ጓዝን ቋጥሮ ጉዞ ማድረግ አይፈቀድም። መስጅደል ሀራም፣ መስጅደል አቅሷ እና ይህ መስጊዴ ናቸው» ብለዋል።

ይህንን አስመልክቶ የተነሳ ውዝግብ አላውቅም። የአላህ መልእክተኛ የከለከሉት ከሶስቱ መስጅዶች ውጭ የሚደረግን ጉዞ ነው። አንድ ሰው በሚኖርበት ከተማ ወዳለ መስጅድ ሲሄድ ወይ እንደ ጁምዓ ግዴታ ለሆነ ተግባር ነው ወይም ደግሞ እንደ ኢእቲካፍ የተወደደ "ሙስተሀብ" ተግባር ለመፈፀም ነው።

– እንደዚሁ ልብ ሊባል የሚገባው፤ ቀብርን የኢባዳ ቦታ ማድረግ ቀብርን መመላለሻ "ዒድ" ማድረግ መሆኑ ነው። ይህ ደግሞ በራሱ የተከለከለ ተግባር ነው። ጉዞ ይኑረውም አይኑረውም፤ በአረፋ እለት ይሁንም ብይኑ አይቀየርም።»
ኢቅቲዷኡሲራጥ አልሙስተቂም ቅፅ 2 ገፅ 149

––––––––––––

¹ السؤال: بالنسبة للدعاء المأثور لا إله إلا الله وحده لا شريك له، له الملك وله الحمد وهو على كلشيء قدير هل هو في يوم عرفة هل هو خاص بالحجيج فقط أم أن غير الحجيج يرددون ذلك؟

الجواب: كما ذكرنا في الجواب أن هذا عام للحجاج ولغيرهم إلا أنه للحجاج آكد من غيرهم لأن الحجاج كما ذكرنا في عرفة متلبسون بالإحرام فهم أرجى في قبول الدعاء وآكد. وغيرهم يشاركهم في هذا الأمر ولهذا يسن صيام يوم عرفة لغير الحجاج لمن هم في الآفاق يصومون هذا اليوم لأنه يوم فاضل ويشتغلون بالذكر بذكر الله والدعاء والاستغفار فيه.

(موقع فضيلة الشيخ الدكتور صالح الفوزان)
http://alfawzan.af.org.sa/sites/default/files/241.mp3">

² قال ابن قدامة رحمه الله :
قال القاضي : ولا بأس بـ " التعريف " عشية عرفة بالأمصار ( أي ِ: بغير عرفة ) وقال الأثرم : سألت أبا عبد الله – أي : الإمام أحمد - عن التعريف في الأمصار يجتمعون في المساجد يوم عرفة ، قال : " أرجو أن لا يكون به بأس قد فعله غير واحد " وروى الأثرم عن الحسن قال : أول من عرف بالبصرة ابن عباس رحمه الله وقال أحمد : " أول من فعله ابن عباس وعمرو بن حُرَيث " .

وقال الحسن وبكر وثابت ومحمد بن واسع : كانوا يشهدون المسجد يوم عرفة ، قال أحمد : لا بأس به ؛ إنما هو دعاء وذكر لله . فقيل له : تفعله أنت ؟ قال : أما أنا فلا ، وروي عن يحيى بن معين أنه حضر مع الناس عشية عرفة " انتهى .

" المغني " ( 2 / 129 ) .

³ قال ابن تيمية في «قاعدة جليلة في التوسل والوسيلة» ضمن «مجموع الفتاوى» 1/282 «وتعريف ابن عباس بالبصرة وعمرو بن حريث بالكوفة؛ فإن هذا لما لم يكن مما يفعله سائر الصحابة= ولم يكن النبي صلى الله عليه وسلم شرعه لأمته= لم يمكن أن يقال هذا سنة مستحبة؛ بل غايته أن يقال: هذا مما ساغ فيه اجتهاد الصحابة، أو مما لا ينكر على فاعله؛ لأنه مما يسوغ فيه الاجتهاد، لا لأنه سنة مستحبة سنها النبي صلى الله عليه وسلم لأمته، أو يقال في التعريف: إنه لا بأس به أحيانا لعارض إذا لم يجعل سنة راتبة.

وهكذا يقول أئمة العلم في هذا وأمثاله: تارة يكرهونه، وتارة يسوغون فيه الاجتهاد، وتارة يرخصون فيه، إذا لم يتخذ سنة..» اهـ.

⁴ قال ابن تيمية في كتاب «مسألة في المرابطة بالثغور» ضمن جامع المسائل 5/364 «وإذا تبين ما في الرباط من الفضل؛ فمن الضلال ما تجد عليه أقواما ممن غرضه التقرب إلى الله والعبادة له بما يحبه ويرضاه يكون في الشام أو ما يقاربها، فيسافر السفر الذي لا يشرع بل يكره، ويترك ما هو مأمور به واجب أو مستحب.

مثال ذلك: أن قوما يقصدون التعريف بالبيت المقدس، فيقصدون زيارته في وقت الحج ليعرفوا به، ويدعون المقام بالثغور التي تقاربه.

وهذا في غاية الضلال والجهل والحرمان من وجوه:
أحدها: أن التعريف بالبيت المقدس ليس مشروعا لا واجبا ولا مستحبا بإجماع المسلمين، ومن اعتقد السفر إليه للتعريف قربة= فهو ضال باتفاق المسلمين، بل يستتاب فإن تاب وإلا قتل، إذ ليس السفر مشروعا للتعريف إلا للتعريف بعرفات.

وأقبح من ذلك تعريف أقوام عند بعض قبور المشايخ والأنبياء وغير ذلك من المشاهد أو السفر لذلك، فهذا من أعظم المنكرات باتفاق المسلمين.

وقال: وأما السفر للتعريف بغير عرفة؛ فلا نزاع بين المسلمين أنه من الضلالات، لا سيما إذا كان بمشهدٍ مثل قبر نبي أو رجل صالح أو بعض أهل البيت؛ فإن السفر إلى ذلك لغير التعريف منهي عنه عند جمهور العلماء من الأئمة وأتباعهم». اهـ

⑤ قال شيخ الإسلام في «اقتضاء الصراط المستقيم» 2/149 «فصل: وقد يحدث في اليوم الفاضل، مع العيد العملي المحدث، العيد المكاني، فيغلظ قبح هذا، ويصير خروجا عن الشريعة. فمن ذلك: ما يفعل يوم عرفة، مما لا أعلم بين المسلمين خلافا في النهي عنه، وهو قصد قبر بعض من يحسن به الظن يوم عرفة، والاجتماع العظيم عند قبره، كما يفعل في بعض أرض المشرق والمغرب، والتعريف هناك، كما يفعل بعرفات فإن هذا نوع من الحج المبتدع الذي لم يشرعه الله، ومضاهاة للحج الذي شرعه الله، واتخاذ القبور أعيادا.

وكذلك السفر إلى بيت المقدس، للتعريف فيه، فإن هذا أيضا ضلال بين، فإن زيارة بيت المقدس مستحبة مشروعة للصلاة فيه والاعتكاف، وهو أحد المساجد الثلاثة التي تشد إليها الرحال، لكن قصد إتيانه في أيام الحج هو المكروه، فإن ذلك تخصيص وقت معين بزيارة بيت المقدس، ولا خصوص لزيارته في هذا الوقت على غيره.

ثم فيه أيضا مضاهاة للحج إلى المسجد الحرام، وتشبيه له بالكعبة، ولهذا قد أفضى إلى ما لا يشك مسلم في أنه شريعة أخرى، غير شريعة الإسلام، وهو ما قد يفعله بعض الضلال من الطواف بالصخرة، أو من حلق الرأس هناك، أو من قصد النسك هناك.

وكذلك ما يفعله بعض الضلال من الطواف بالقبة التي بجبل الرحمة بعرفة كما يطاف بالكعبة.

فأما الاجتماع في هذا الموسم لإنشاد الغناء أو الضرب بالدف بالمسجد الأقصى ونحوه، فمن أقبح المنكرات من جهات أخرى.

منها: فعل ذلك في المسجد؛ فإن ذلك فيه ما نهي عنه خارج المساجد؛ فكيف بالمسجد الأقصى؟! ومنها: اتخاذ الباطل دينا. ومنها فعله في الموسم». اهـ.

والله أعلم

አቡ ጁነይድ
9/12/1436