Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

#‎ትክክለኛ‬ ሰለፊይ መሆን ከፈልግክ የሚከተለውን በጥሞና አንብብ

‪#‎ትክክለኛ‬ ሰለፊይ መሆን ከፈልግክ የሚከተለውን በጥሞና አንብብ፦
ሸይኽ ሷሊሕ ፈውዛን (ሀፊዘሁላህ) እንዲህ ይላሉ፦
"… ከነርሱም መካከል "መንሐጅ ሰለፍ" ላይ ነኝ ብሎ ይሞግትና፦
ሲያግራራ፣
ብዙ ግዴታ የሆኑ ነገሮችን ሳይወጣ
እራሱን ወደ ሰለፊያ በማስጠጋት ብቻ የሚብቃቃ አለ።
ትክክለኛ "መንሐጅ ሰለፍ "ላይ ያለ ሰው የሚከተለውን ያሟላ ይገባል፦
👉 በድንበር ማለፍ፣(ፅንፈኝነት) እና ቸልተኛነት መካከል ሚዛናዊ፣ፍትሓዊ በመሆን ፅናት ላይ ያለ ሰው እርሱ ነው በትክክለኛ በሰለፍ መንገድ ላይ ያለው።
👉 "መንሀጅ አሰለፍ" አንዳንድ መሃይማን(ጁሃሎች) እራሳቸውን ሰለፊ ነን ብለው ፦
ከዚያም ሰልፍን የሚጣረሱ ሰዎች እንደሚያደርጉት አይደለም መንሀጁ።
እነዚህ ሰዎች ፦
ሀይለኝነት ይጎላባቸዋል፣
እነሱን ያልተስማማነው ሰው ያለ አግባብ ያከፍራሉ፣
ያለ ሐቁ ፋሲቅ ነው ይላሉ፣
ያለ ሸሪዓዊ ደንብና ስርዓት ሰዎችን ሙብተዲዕ ብለው ይፈርጃሉ።
ሰልፎች ከዚህ ተግባር የፀዱ ናቸው።
ሰልፎች ያከፍሩ፣ ወይም ፋሲቅ እና ሙብተዲዕ የሚሉት ከቁርኣን ማስረጃ ተመርኩዘው እንጂ በጅሕልና እና በባዶ ስሜት ላይ አልነበረም።

👉ትክክለኛ ሰለፊይ መሆን ከፈልግክ የሚከተለውን መከተል ይኖርብሃል፦
① መንሐጅ ሰልፍን በደንብ አድቅቀህ ልትማር ይገባል ።
② መንሐጅ ሰልፍን በዕውቀት ላይ ተመስርተህ ልታውቀው ይገባል።
③ ከዚያም ያለ ድንበር ማለፍ እና ያለ ቸልተኝነት ተግባራዊ ልታደርገው ይገባል።
👉ይህ ነው እውነተኛ የሰለፎች መንሐጅ፣ በባዶ ሰለፊይ ነኝ ብሎ መሞገት እና ያለ ሐቁ እራስን ወደ ሠለፊያ ማስጠጋት ይጎዳል እንጂ ምንም አይጠቅምም! !"
📚ምንጭ፦【"አተዕሊቃቱ አተውዲሒያ ዓላ ሙቀደመቲ አልፈትዋ አል ሐመዊያ" (ገፅ፤58–59)】
🔁https://telegram.me/sultan_54