Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ጥያቄ፦ ተማኢምና ሑጁብ (ከክፉ ነገር እንደሚከላከሉ የሚታመንባቸው ነገሮች) ማንጠልጠል እንዴት ይታያል? ሸይኽ መሐመድ ኢብኑ ሷሊህ አልዑሰይሚን ረሒመሁላህ


ጥያቄ፦ ተማኢምና ሑጁብ (ከክፉ ነገር እንደሚከላከሉ የሚታመንባቸው ነገሮች) ማንጠልጠል እንዴት ይታያል?
መልስ፦ ይህ ጉዳይ ማለትም ተማኢምና ሑጁብ ማንጠልጠል በሁለት ይከፈላል።
አንደኛው፦ የሚንጠለጠለው ነገር የቁርአን አንቀፅ ከሆነ ዑለሞች ሰለፎችም ሆነ ኸለፎች ተለያይተውበታል። ማንጠልጠል ይችላል ያሉ አሉ የሚከተለውን አንቀፅ ማስረጃ በማድረግ፦
❴ وَنُنَزِّلُ مِنَ ٱلْقُرْءَانِ مَا هُوَ شِفَآءٌۭ وَرَحْمَةٌۭ لِّلْمُؤْمِنِينَ ❵ۙ
ከቁርኣንም ለምእመናን መድኀኒትና እዝነት የኾነን እናወርዳለን፡፡ [አልኢስራአ፡ 17፥82]
❴كِتَٰبٌ أَنزَلْنَٰهُ إِلَيْكَ مُبَٰرَكٌۭ ❵
ِ
«(ይህ) ወዳንተ ያወረድነው ብሩክ መጽሐፍ ነው፤…»
[ሷድ፡ 38፥29]
እናም ከብሩክነቱ አንዱ ሰውነት ላይ ተንጠልጥሎ ክፉን ነገር መከላከል መቻሉ ነው ይላሉ።
የከለከሉም አሉ። የቁርአንን አንቀፅ በማንጠልጠል ክፉን ነገር ማስወገድ እንደሚቻል በሸሪዓው የተፈቀደ ለመሆኑ ከነቢዩ (ሰላሏህ አለይሂ ወሰለም) አልተገኘም በማለት። በመሠረቱ እነዚህን በመሳሰሉት ጉዳዮች መታቀብ (ተውቂፍ) ይመረጣል። ይህ ነው ሚዛን የሚደፋው (ራጂህ) አስተያየት። ከቁርአን አንቀፅም ቢሆን ተማኢምን ማንጠልጠል፣ በበሽተኛው ትራስ ሥር ማድረግ፣ በግድግዳ ላይ ማንጠልጠል፣ ወዘተ…አይቻልም። ነቢዩ (ሰላሏህ አለይሂ ወሰለም) ሲያደርጉት እንደነበረው ለበሽተኛው ዱዓ ተደርጎለት ይቀራበታል? እንጂ።
ሁለተኛው፦ የሚንጠለጠለው ነገር ከቁርአን አንቀፅ ውጭና ትርጉሙም የማይታወቅ ከሆነ በማንኛውም ሁኔታ አይቻልም። ምክንያቱም ምን እንደተፃፈ ስለማይታወቅ። አንዳንድ ሰዎች የተቆላለፉ ነገሮችን ማለትም ማወቅም ማንበብም የማይቻል የሆኑ የተቆላለፉ ፊደሎችን ይፅፋሉ። ይህ ቢድዓ ነው። ሐራም ነው። በማንኛውም ሁኔታ አይፈቀድም። ወላሁ አዕለም።
❨ሸይኽ መሐመድ ኢብኑ ሷሊህ አልዑሰይሚን ረሒመሁላህ❳