Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ጥንቃቄ ይወሰድ፡፡ =========== ልጆች ‹‹እንቆቅልሽ አገር ስጠኝ…›› ብለው ‹‹ሁሉ በእጄ ሁሉ በደጄ›› ሲሉ ይደመጣል

ጥንቃቄ ይወሰድ፡፡
===========
ልጆች ‹‹እንቆቅልሽ አገር ስጠኝ…›› ብለው ‹‹ሁሉ በእጄ ሁሉ በደጄ›› ሲሉ ይደመጣል፣ ብሎም ማስታወቂያ ላይ ‹‹ሁሉ በእጄ ሁሉ በደጄ ሲሉ›› እያየን እየሰማን ነው፡፡ መልካም ነገሮች ሁሉ በእጁ የሆነው ብቸኛው ብሉን ቻይ አላህ ነው፡፡ አላህ እንዲህ ይላል
قُلِ ٱللَّهُمَّ مَٰلِكَ ٱلْمُلْكِ تُؤْتِى ٱلْمُلْكَ مَن تَشَآءُ وَتَنزِعُ ٱلْمُلْكَ مِمَّن تَشَآءُ وَتُعِزُّ مَن تَشَآءُ وَتُذِلُّ مَن تَشَآءُ ۖ بِيَدِكَ ٱلْخَيْرُ ۖ إِنَّكَ عَلَىٰ كُلِّ شَىْءٍ قَدِيرٌ
(ሙሐመድ ሆይ!) በል፡- «የንግስና ባለቤት የኾንክ አላህ ሆይ! ለምትሻው ሰው ንግሥናን ትሰጣለህ፡፡ ከምትሻውም ሰው ንግሥናን ትገፍፋለህ፡፡ የምትሻውንም ሰው ታልቃለህ፡፡ የምትሻውንም ሰው ታዋርዳለህ፡፡ መልካም ነገር ሁሉ በእጅህ ነው፤ አንተ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነህና፡፡»
‹‹መልካም ነገር ሁሉ በእጅህ ነው፤ አንተ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነህና›› ብለን የምንለምነው አላህን ነው፡፡
የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰላም) የተላኩባቸው ከሃዲያንና የመካ ሙሽሪኮች እንኳን «የነገሩ ሁሉ ግዛት በእጁ የኾነ እርሱ የሚጠብቅ በእርሱ ላይ የማይጠበቅ ማን ነው᐀ የምታውቁ እንደኾናችሁ (መልሱልኝ)» በላቸው፡፡ ተብለው ቢጠየቁ «በእርግጥ አላህ ነው» ይሉሃል፡፡ «ታዲያ እንዴት ትታለላላችሁ᐀» በላቸው፡፡ ብለው እንደሚመልሱ አላህ እንዲህ ሲል ይነግረናል
قُلْ مَنۢ بِيَدِهِۦ مَلَكُوتُ كُلِّ شَىْءٍ وَهُوَ يُجِيرُ وَلَا يُجَارُ عَلَيْهِ إِن كُنتُمْ تَعْلَمُونَ
«የነገሩ ሁሉ ግዛት በእጁ የኾነ እርሱ የሚጠብቅ በእርሱ ላይ የማይጠበቅ ማን ነው᐀ የምታውቁ እንደኾናችሁ (መልሱልኝ)» በላቸው፡፡
سَيَقُولُونَ لِلَّهِ ۚ قُلْ فَأَنَّىٰ تُسْحَرُونَ
«በእርግጥ አላህ ነው» ይሉሃል፡፡ «ታዲያ እንዴት ትታለላላችሁ᐀» በላቸው፡፡
ልጆቻችን የሚናገሩትና የሚሰሩትን ነገር በደንብ ትኩረት ሰጥተን እንከታተል፡፡ መሰረቱ ሲያምር ነው ሌላው የሚያምረው፡፡ አላህ ልጆቻችንን በተውሂድና ሱና ላይ ኮትኩተው ከሚያሳድጉት ያድርገን፡፡ አላህን በእውቀት ከሚገዙት፣ የእሱን ልቅናና ክብር ከሚገነዘቡት ያድርገን፡፡ የአላህን ክብር፣ ጌትነት፣ ልቅና ከሚቃረኑ ማንኛውም ነገሮች አላህ ይጠብቀን፡፡