Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የአሹራ ፆም




Ilyas Awel

የአሹራ ፆም
የሙሀረም ወር የአላህ ወር በመባል ይታወቃል፡የሙሀረም ወር የተከበረና በኢስላም ትልቅ ወር ነው።በሒጅሪያ አቆጣጠር የአመቱ መጀመሪያ ወር ሲሆን አላህ ሱ.ወ ከአራቱ የተከበሩ ወሮች መድቦታል።
አላህ ሱ.ወ እንዲህ ይላል፦<<የወሮች ቁጥር አላህ ዘንድ በአላህ መፅሐፍ ውስጥ ሰማያትንና ምድርን በፈጠረበት ቀን አስራ ሁለት ወር ነው እነርሱንም አራቱ የተከበሩ ናቸው ይህ ቀጥተኛው ሃይማኖት ነው በርሱ ውስጥም ነፍሶቻቱን አትበድሉ።>>(አል ተውባህ)

አቡበከር (ረዲየሏሁ አንሁ) ረሱልም (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል አሉ<<አመት ማለት አስራ ሁለት ወሮች ናቸው ሶስቱ ተከታታይ ሱሆኑ እነርሱም ዙል ቂዳህ፣ዙል ሂጃህና ሙሐረም ፣ናቸው አንደኛው በጂማዲና በሻህባን መካከል ያለው ረጀብ ነው>> ብለዋል።(ቡኻሪ ዘግበውታል)

ኢብን አባስ(ረዲየሏሁ አንሁ) እንዳስተላለፉት ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ወደ መዲና በመጡ ጊዜ ዩሁዶች የአሹራን ቀን ሲፆሙ አገኝዋቸው።
ረሱልም (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ይህ የምትፆሙት ቀን ለምንድን ነው ብለው ጠየቋቸው፡
የሁዶችም ይህ ቀን የተከበረ ቀን ነው አላህ ሙሳንና ተከታዮችን አትርፎ ፊራኦንንና ተከታዮቹን ያሰጠመበት ቀን ስለሆነ ነው አላህን ለማመስገን ነበዩ ሙሳም ስለፆሙት እኛም እንፆመዋለን አሉ።
በዚህን ጊዜ ረሱልም (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እኛ ከናንተ የበለጥን ለሙሳ የቀረብንን ነን) ብለው መፆም ጀመሩ ።

አቢ ሁረይራ ባስተላለፉት የአላህ መልእክተኛ(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ይላለሁ፡
<<በላጩ ፆም ከረመዳን ቀጥሎ የአላህ ወር ሙሀረም ነው>>(ሙስሊም ዘግበውታል)

የአሹራን ቀን መፆም ትልቅ ምንዳን ያስገኛል፡ይህም በሀዲስ የተጠቀሰ ነው።
አቢ ቀታዳህ አል አንሳሪይ እንዳስተላለፉት የአላህ መልእክተኛ(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ስለ አሹራ ፆም ተጠይቀው እንዲህ አሉ፡
<<ያለፈው አንድ አመት ወንጀል ያስምራል>>(ሙስሊም ዘግበውታል)
የአሹራን ፆም በእንዲህ አይነት መልኩ መፆም ይቻላል
1.ሙሀረም አስር የአሹራ ቀን ብቻ መፆም
2.ሙሀረም ዘጠኝንና ሙሀረም አስርን መፆም
ኢማሙ ኢማሙ አህመድ እንደዘገቡት ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) <<መጪው አመት ድረስ ከቆየሁኝ ሙሀረም ዘጠነኛውና አስረኛውን ቀን እፆማለሁ>>ብለዋል።
3.ሙሀረም ዘጠኝ መሁረም አስረ(የአሹራ ቀን) እና ሙሀረም አስራ አንድን ሶስቱ ቀን መፆም ሌላው አይነት ነው።
በተጨማሪ የፈለገ ሙስሊም ሙሀረም አስረኛውን(የአሹራ ቀን) ሙሀረም አስራ አንደኛውን ቀን መፆም ይችላል።

ረሱልም (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) የአሹራን ቀን ፁሙ የሁዶችም ስለሚፆት ከነሱ ላለመመሳሰል ጭማሪ አንድ ቀን አስቀድማችሁ ወይም አስከትላችሁ ፁሙት>>ብለዋል።(አህመድ ዘግበውታል)
ይህን የአሹራ ፆም በተቻለን መጠን ሁላችን በመፆም ወደ አላህ እንቃለብ እላለሁ።
ወላሁ አእለም።

Post a Comment

0 Comments