Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ተቅዋ፡- ማለት አንድ ሰው በራሱና ...


ተቅዋ፡- ማለት አንድ ሰው በራሱና በሚፈራው ነገር መሀል ከእራሱ የሆነ መጠበቂያ ሲያደርግ ተቅዋ አድርጓል ይባላል፡፡
አንድ ሰው አላህን ፈርቷል ስንል፡- በእራሱና ከሚፈራው ነገር፣ ከቁጣውና ከጥላቻው የሚጠብቀውን ትዕዛዙን በመፈፀምና ክልከላውን በመራቅ መከላከያ ማድረግ ማለት ነው፡፡
ይኸውልህ ውድ ወንድሜ፡- ቀደምት ሳሊሆች የተቅዋን ትርጉም በማብራራት የተጠቀሟቸው ከፊል አባባሎች፡-
አብድላህ ኢብኑ አባስ (ከእሱ የሆነውን አላህ ይውደድለትና) እንዲህ ይላል ፡- “አላህን ፈሪዎች የሚባሉት እነዚያ አላህንና ቅጣቱን የሚጠነቀቁ ናቸው፡፡”
ጠልቅ ኢብኑ ሐቢብ ተቅዋን በማስመልከት እንዲህ ይላል ፡- ‹‹አላህን መፍራት ሲባል በአላህ ብርሃን የአላህን ትዕዛዝ ልትፈፅምና ከአላህ ምንዳ (ዋጋ) ልትፈልግ፤ እንዲሁም በአላህ ብርሃን የአላህን ክልከላ ልትርቅና ቅጣቱን ልትፈራ ማለት ነው፡፡››
አልይ(ረድየላሁ አንሁ) አንድን ሰው እንዲህ በማለት መከረ “እሱን ከመገናኘት ምንም ቅሮት የሌለውን ያንን ታላቁን አላህ በመፍራት እመክርሀለሁ፡፡ ከእሱ ሌላ መጨረሻም የለህም እሱም (አላህ) የቅርቢቱንና የመጨረሻይቱ ሀገር ባለቤት ነውና”