ዱዓኡል
ኢስቲፍታህ (የመክፈቻ ዱዓ) በፈርድም ሆነ በሱና ሶላት ውስጥ ሱና እንጂ ግዴታ አይደለም፡፡ ነብዩ <
ሲጠቀሙበት ከነበሩት ዱዓዎች -አንድ ጊዜ አንዱን በሌላ ጊዜ ደግሞ ሌላኛውን- እያፈራረቁ መጠቀም የተወደደ ነው፡፡
የነቢዩን < ሱና በሁሉም መልኩ መተግበር አስፈላጊ ነውና፡፡ አንዱን ብቻ እንጂ ሌላውን የማያውቅ ከሆነና ሁሌም
እሱኑ ብቻ የሚቀራ ከሆነም ችግር የለውም፡፡ ነቢዩ < በሶላት መክፈቻና በተሸሁድ ላይ የተለያዩ ዱዓዎችን
ይጠቀሙ የነበሩት ለተከታዮቻቸው (ኡመታቸው) ለማግራት ነው፡፡ እንደዚሁም ከሶላት በኋላ ነቢዩ < የተለያዩ
ዚክሮችን (ውዳሴዎችን) ያደርጉ ነበር፡፡ ይህም ለሁለት ጥቅም ነው፡፡
አንደኛው፡- ሰው በአንድ አይነት ዱዓ ወይም ዚክር ላይ እንዳይዘወትር ነው፡፡ ሰው በአንድ ዓይነት ዚክር ላይ ከዘወተረ ነገሩ የተለመደ ይሆናል፡፡ ከተለመደ ደግሞ ዚክሩን ለማለት ሳይፈልገውም ይለዋል፡፡ የተለመደ ስለሆነ ሳያስበው በምላሱ ሊዘክር ይችላልና፡፡ ዚክሮቹ የተለያዩ ከሆኑና ሰውየው አንድ ጊዜ አንዱን በሌላ ጊዜ ደግሞ ሌላውን ከዘከረ ግን ልቡም ነቃ ብሎና ትርጉሙንም እያስተነተነ ይዘክራል፡፡
ሁለተኛውን፡- ለኡመቱ ለማግራት ነው፡፡ ሰው እንዳስፈላጊነቱ እየለዋወጠ ዚክር ማድረግ እንዲችል ነው፡፡ ለነዚህ ሁለት ጥቅሞች ሲባል አንዳንድ ዒባዳዎች ለምሳሌ፡- የመክፈቻ ዱዓ፣ በተሸሁድ ላይ የሚደረግ ዱዓ እና ከሶላት በኋላ የሚደረጉ ዚክሮች በተለያየ መልኩ ነብዩ < ያደርጉ ነበር፡፡