Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ሁለቱ የምስክርነት ቃሎች (ሸሀደታን)


«አሽሀዱ አንላኢላሀ…» በሚለው ቃል ውስጥ፣ «ላ» የምትለው ቃል አፍራሽ ስትሆን፣ ከአላህ ውጭ ለማንም የሚፈጸም አምልኮትን የምታወግዝ ነች። «ኢለላህ» የሚለው ሀረግ ደግሞ በእውነት ሊመለክ የሚገባው አላህ ብቻ መሆኑን ያረጋግጣል። «ኢላህ» የሚለው ቃል ትርጉሙ «መዕቡድ» ወይም «የሚመለክ» ማለት ነው። ስለሆነም «ላኢላሀ ኢለላህ» ማለት «ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ የለም» ማለት ነው። ከአላህ ውጭ የሚመለክ ሁሉ የውሸት ተመላኪ በመሆኑ፣ ይህ የምስክርነት ቃል የውሸት ተመላኪን ሁሉ ውድቅ ያደርጋል።
በሌላ በኩል አሁን በአለንበት ዘመን «ላኢላሀ ኢለላህ» በማለት ከመሰከሩ በኋላ፣ ከአላህ ውጭ ያሉ አካላትን፤ የሞቱ ሰዎችን ጭምር መንፈሳዊ እርዳታ በመጠየቅ የሚያመልኩ ሰዎች አሉ። በሽርክ እድፍ ተበክለው እያለ፣ «ሙስሊም ነን» በማለት ይሞግታሉ። ስለዚህም ላኢላሀ ኢለላህን በተገቢው መንገድ አላሉትም፤ ለአፍ ያህል ቢሉም በሽርክ ተግባር አፍርሰውታልና።
«ሙሀመድ የአላህ መልዕክተኛ ናቸው» ብሎ መመስከር ማለት ደግሞ፣ «ሙሀመድ ወደ ሰዎችና ጅኖች አላህ መልዕክተኛ አድርጎ የላካቸው መሆኑን አረጋግጣለሁ» ማለት ነው። በዚህ የምስክርነት ቃል ሙሀመድ የአላህ መልእክተኛ መሆናቸውን ስናረጋግጥ በውስጥም፣ በውጭም መሆን አለበት። ይህም ማለት በልብ አምኖ በምላስ መናገር ማለት ነው። አንድ ሰው በምላሱ የአላህ መልዕክተኛ መሆናቸውን አረጋግጦ፣ በልቡ ተቃዋሚ ከሆነ ይህ ሰው «ሙናፊቅ» ይባላል