ይህ
ሀዲስ የሚያመላክተው ኢማን ልባዊ እምነት፣ ንግግር፣ ወይም ተግባር ብቻ ሳይሆን፡ የሶስቱም ማለትም ጥምር ውጤት
መሆኑን ነው። በሀዲሱ ውስጥ «በላጩ ላኢላሀ ኢለላህ» በማለት የተገለፀው ቃል፣ በአንደበት የመናገርን አስፈላጊነት
ያመላክታል። «እንቅፋት ሊሆን የሚችልን ነገር ከመንገድ ማስወገድ» የሚለው ቃል ደግሞ የተግባርን አስፈላጊነት
ያመላክታል። «ሀያዕም (ትህትና) ከኢማን ቅርንጫፎች አንዱ ነው» የሚለው ደግሞ የልብ ስራን ያመላክታል። ይህ ሀዲስ
«ኢማን» የነዚህ ሶስት ነገሮች ማለትም የንግግር፣ የልብ እምነትና የተግባር ጥምር ውጤት መሆኑን ይጠቁማል።
ስለሆነም አቅም እያለው ስራን ወይም ተግባርን ከነአካቴው አውቆ የተወ ሰው «ሙስሊም» ወይም «ሙእሚን» አይባልም። ከኢስላም ተግባራት ውስጥ የተወሰነውን የተወ፣ የእምነት ጉድለት ይኖርበታል፤ ወይም ከከሀዲ ሊፈረጅ ይችላል። ለምሳሌ አንድ ሰው ሶላትን ሆን ብሎም ይሁን በቸልተኝነት ከነአካቴው ከተወ፣ የአብዛኛው የአህሉሱና አቋም «ከኢስላም ጎዳና ይወጣል» የሚል ነው። ከሶላትና ከሸሀደተይን (ላኢላሀ ኢለላህ፣ ሙሀመድ ረሱሉላህ) ውጭ ካሉ ተግባራት መካከል አንዱን የአምልኮ ተግባር ግዴታነት ተቀብሎ ሳይፈፅም ቢቀር፣ እምነቱ ጎደሎ ይሆናል። ስለሆነም ከሽርክ በታች ያሉ ወንጀሎችን ለፈጸመ ግለሰብ የሚሰጠው አይነት ብይን ይሰጠዋል።
በመሆኑም ኢስላምንና ኢማንን ማጣመር ግድ ነው፤ትክክለኛ ኢማን የሁለቱ ድምር ውጤት ነው። አንድ ሰው በኢስላም ላይ ብቻ ተወስኖ፣ ኢማንን ከተወ ከሙናፊቆች ይፈረጃል። ይህ ሁኔታ ከዚህ በፊት እንደተገለፀው በረሱል ዘመን በነበሩ ሙናፊቆች ላይ ይታይ የነበረ ሀቅ ነው። ውጫቸው ሰልሞ ውስጣቸው ግን አልተቀበለውም ነበር። ለምሳሌ ይሰግዳሉ፤ ይ ፆማሉ፤ ጅሀድ ይወጣሉ፤ ወዘተ.. ነገር ግን እየሰሩት ያለውን ተግባር በውስጣቸው አያምኑበትም ነበር። ለዚህም ነው አላህ ከመጨረሻው የእሳት አዘቅት ውስጥ ለዘላለሙ ሊዘፍቃቸው ቀጠሮ የያዘላቸው፣ የማይሻር የከፋ ቀጠሮ።
በአንፃሩ አንድ ሰው ውስጡ ተቀብሎ፣ በይፋ ካልመሰከረና ካልተገበረ «ሙስሊም» አይባልም። የመካ ሙሽሪኮች፣ አይሁዶችና ነሷራዎች የሙሀመድን ትክክለኛ መልዕክተኛነት በልባቸው ያውቁት ነበር። ነገር ግን ይህን በይፋ ተናገሩ ወይም መስክሩ በተባሉ ጊዜ አልመሰከሩም። አላህ እንዲህ ይላል፤
«እነሆ ያ የሚሉህ ነገር እንደሚያሳዝንህ በእርግጥ እናውቃለን፤ እነርሱም (በልቦቻቸው) አያስተባብሉህም፤ ግን በዳዮቹ በአላህ አንቀጾች ይክዳሉ።» (አንዓም፣ 33)
የነብዩ አጎት -አቡጧሊብ- በበኩሉ ተከታዩን ገጥሟል ወደ አማርኛም እንዲህ መልሰነዋል፡-
وعرضت ديناً قد عرفت بأنّه ... من خير أديان البرية ديناً
لولا الملامة أو حِذار مسبّة ... لوجدتني سمحاً بذاك مبيناً
«አውቂያለሁ ያቀረብከዉን ሀይማኖት
መላቅ፣ መብለጡን ከሁሉም እምነት፣
ወቀሳና ስድብ ባልፈራ
ለክብር ለዝናዬ ባልራራ
ማን ነበር ከኔ ቀድሞ የሚመሰክር
የኢስላምን ታላቅነት፣ የኢስላምን ክብር።»
አቡጧሊብን «ላኢላሀ ኢለላህ፣ ሙሀመድ ه ረሱሉላህ» የሚለውን የምስክርነት ቃል ከመናገር ያገደው ከህብረተሰቡ ጋር የነበርው የጠበቀ የማህበራዊ ህይወት ትስስር መሆኑ ግልጽ ነው። በልቡ የመሰክረውንና በግጥም የገለፀውን ያህል በአንደበቱ «ላኢላሀ ኢለላህ፣ ሙሀመዱ ረሱሉላህ» ቢል ኖሮ፣የአካባቢው ማህበረሰብ ከሚከተለው እምነት ባገለለ ነበር። ተስፋ ያልቆረጡት ነብዩ «እስልምናን ሊቀበል ይችላል» በማለት፣ ሊሞት በተቃረበበት ወቅት ጭምር ‹‹አጎቴ ሆይ! ላኢላሀ ኢለላህ በል›› በማለት ተማጽነውታል። የሞት አፋፍ ላይ ባለበት በዚህ ወቅት ‘የክፉ ጓደኛ ምክሩም ክፉ ነውና’ የአቡጧሊብ የቅርብ ጓደኛ የሆነው አቡጀህል በበኩሉ፣ ‹‹የአብዱል ሙጦሊብን ሀይማኖት ትተዋለህን?›› በማለት ወትውተውታል። እናም አቡጧሊብ ‹‹እርሱ በአብዱል ሙጦሊብ ሀይማኖት ላይ መሆኑን ገልጾ›› ሞተ፤ እናም ይህች የክህደት ቃል የመጨረሻ ቃሉ ሆነች። በልቡ እየመሰከረ ነገር ግን በአንደበቱ «ላኢላሀ ኢለላህ» ባለማለቱ የእሳት ሆነ።
አቡጧሊብ የኢስላምን ትክክለኛነት ያለ ጥርጥር አውቋል። ከዚህም በተጨማሪ ላኢላሀ ኢለላህን በአንደበታቸው እያሉ፣ ትርጉሙን በውል እንደማይረዱት የዘመናችን በርካታ ሙስሊሞች ሳይሆን፣ የቃሉን ትክክለኛ ትርጓሜ ጠንቅቆ ተረድቶታል። «ላኢላሀ ኢለላህ» ብሎ መመስከር ማለት፣ ያለበትን ማህበረሰብ እምነት አውልቆ መጣል መሆኑን በሚገባ አውቋል። «ታዲያ ከፊቱ የቀረበለትን ሀቅ ከመቀበል ምን አገደው?» ከተባለ፣ መልሱ «ጃሂልያ» (ድንቁርና፤መሀይምነት) ነው። የጃሂልያ ወገንተኝነትና እልህ ወደ ክህደት (ኩፍር) ይገፋፋል። አላህ እንዲህ ይላል፡-
«እነዚያ የካዱት የመሀይምነቱን (የጃሂሊያ) እልህ በልቦቻቸው ውስጥ ባደረጉ ጊዜ (በቀጣናቸው ነበር)፤ አላህም በመልክተኛው ላይና በምእመናኖቹ ላይ እርጋታውን አወረደ...» (ፈትህ፣ 26)
ከላይ ሲል የቀረበው ማብራሪያ የኢማንን ምንነት የሚያስረዳ ነው። ኢማን በስድስት ማዕዘናት ማለትም በአላህ፣ በመላኢካዎቹ፣ በመፃህፍቱ፣ በመልእክተኞቹና በመጨረሻው ቀን እንዲሁም መልካምም ይሁን መጥፎ በአላህ ውሳኔ የሚከናወን መሆኑን በማመን ላይ የተገነባ ነው።