የማይሰግድ ሰው ሁክም
ጥያቄ፡- ቤተሰቦቹ ሙስሊም ሆነው ሳለ እሱ የማይሰግድ ሆኖ የሞተ ሰውን፡- ሬሳ ማጠብ፣ መከፈን፣ ሶላተል ጀናዛ በሱ ላይ መስገድ፣ መቅበር እና ለሱ ዱዓ ማድረግ እንዴት ይታያል?
መልስ፡- ለአቅመ አዳም ደርሶ እና እውቀቱ ኖሮት የማይሰግድ ሆኖ የሞተ ሰው ካፊር (ከሀዲ) ነው። ሬሳው አይታጠብም፣ አይሰገድበትም፣ በሙስሊሞች መቃብር ላይ አይቀበርም። የውርስ ገንዘቡንም ሙስሊም ቤተሰቦቹ ሊወርሱት አይችሉም። ገንዘቡን የሙስሊሞች ግምጃ ቤት (በይቱል ማል) ይወርሰዋል። ትክክለኛው የኡለሞች አቋም ይህ ነው። የሚከተሉትን መረጃዎች ከግንዛቤ በማስገባት። ሶሂህ በሆነ ሀዲስ መልዕክተኛው እንዲህ ብለዋል። «በሰውየውና በሽርክ ወይም ኩፍር (ክህደት) መሀል ያለው ልዩነት ሶላትን መተው ነው።» እንዲሁም ኢማሙ አህመድ በዘገቡት ሶሂህ በሆነ ሀዲስ መልዕክተኛው እንዲህ ብለዋል፡- «በኛና በነሱ (በከሀዲያን) መሀል ያለው (መለያ) ቃልኪዳን ሶላት ነው። ሶላትን የተወ በርግጥ ካደ።» ታቢዒይ የሆነው አብደላ ብን ሸቂቅ -አላህ ይዘንለትና- ቡረይዳን ጠቅሶ እንዲህ ብሏል፡- «የመልዕክተኛው ባልደረቦች ሶላት ሲቀር ማንኛውንም (ኢባዳ) መተው ክህደት ነው ብለው አያስቡም ነበር።» ይህን መሰል ሀዲስ እና የሰሃቦች ንግግር ብዙ አለ። ይህ ፍርድ የሶላትን ግዴታነት አምኖ በመሰላቸት ወይም በሌላ ምክንያት ሶላትን ለሚተው ሰው ነው። የሶላትን ግዴታነት የካደ ሰው ካፊር እና ከእስልምና ሙሉ በሙሉ ያፈነገጠ (ሙርተድ) መሆኑን ሁሉም የሙስሊም ምሁራን በአንድነት ተስማምተዋል።
አላህ የሙስሊሞችን ሁኔታ እንዲያስተካክለው፤ ወደ ቀጥተኛው መንገድ እንዲመራቸው እንለምነዋለን። እሱ ሰሚ እና ተቀባይ ነውና።